Get Mystery Box with random crypto!

🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የሰርጥ አድራሻ: @adis_zena
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.96K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ዜና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ለማስታወቂያ ስራ @adis_probot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-12 19:25:39
180 ሺህ የሚጠጉ ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና መዘጋጀቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና፣ ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወቃል፡፡

"የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል" ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱንም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
@Adis_zena
@Adis_zena
5.0K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 11:11:40
ይህ ቪድዮ በቀን 3 / 10 / 2015 በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተቀረፀ ስለመሆኑ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

ይህ ክስተት የተፈጠረው ተመራቂ ተማሪዎች " የመውጫ ፈተና የወደቀ መመረቅ አይችልም " የሚባለው ጉዳይ ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሞ ለማሰማት በወጡበት ወቅት የተፈፀመ ነው ብለዋል።

የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱት እርምጃ ፍፁም ህግን ያልተከተለ መሆኑ እሙን ነው ፤ ማንኛውም ሰው መጠየቅ ካለበት በህግ አግባብ መጠይቅ ሲገባው እንዲህ ያለው የድብደባ ተግባር መፈፀሙ ፍፁም ህግን የሚጥስ ተግባር ነው።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
1.5K viewsedited  08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 13:54:33
የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት :-

1. ቤንዚን ----- ብር 69.52 በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ ---- ብር 71.15 በሊትር

3. ኬሮሲን ---- ብር 71.15 በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---- ብር 65.35 በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 57.97 በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 56.63 በሊትር

መረጃው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።
@Adis_Media
@Adis_Media
3.4K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 10:04:37
በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ብሏል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
4.9K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 10:01:39
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ግንቦት 23/2015 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል፡፡
@Adis_Zena
@Adis_Zena
3.9K viewsedited  07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 09:30:29
በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 13 /2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረገውን ወይይት ተከትሎ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በዚህም፡-

➤ በሰኔ 2015 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

➤ የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

➤ ውጤት ከሐምሌ 09 እስከ 10/2015 ዓ.ም በተቋማቱ ይገለጻል፡፡ (ተማሪዎች ከሐምሌ 08 ጀምሮ የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት ኦንላይን ማየት ይችላሉ።)

➤ የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት
@Adis_Zena
@Adis_Zena
4.7K viewsedited  06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 10:37:00
ትናንት ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች መስጂዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በመርካቶ ዙሪያ በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ረብሻና ግርግር ህግ በማስከበር መደበኛ ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱንም አስታውቋል።

በተለይም በተለምዶ ጋዝ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ ግርግር ሁለት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉንም ነው የገለጸው።

በተጨማሪም አራት ግለሰቦች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ህግን ለማስከበር በተሰማሩ 37 የፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም 15 የሚሆኑ የተለያዩ የፖሊስ አጋዥ ሀይሎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና መላካቸውንም ገልጿል።

ረብሻውን ባስነሱት አካላት በተጨማሪ ንብረትነታቸው የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሆኑ ሁለት አውቶቡሶች ላይ ጉዳት መድረሱንም በመግለጫው አመላክቷል።

መነሻውን አንዋር መስጂድ ያደረገው ረብሻ በጋዝ ተራ፣ ቆርቆሮ ተራ፣ ሰባተኛ አካባቢ፣ አመዴ እና በተለያዩ አካባቢ ለማዛመት የተሞከረ ቢሆንም በፀጥታ አካሉ ጥረት ረብሻው ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏልም ነው ያለው
@Adis_Media
@Adis_Media
5.8K viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 21:17:35
የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ ወጣ።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ ከተማ አስተዳደሩ በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸፍን 3310 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 17/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም. ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ፣ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ እስከ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል መግዛት ይችላል ሲል ገልጿል።

የጨረታ ሳጥን ሰኔ 19/2015 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የጨረታ ሰነድ የት ነው የሚሸጠው ?

- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ

- ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4

- የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ

- አራዳ ክ/ ከተማ ግቢ ውስጥ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ቢሮ ቁ/G03

- 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት

- 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት
@Adis_Media
@Adis_Media
4.5K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 12:17:44
በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና የሚሰጠው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በቀን ግንቦት 15/2015 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰራጨው ደብዳቤ፤ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እንዲሰጡ አሳስቧል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena
4.7K viewsedited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 11:12:21
የሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት የሮቦት ዉሻን በፖሊስ ሥራ ላይ ለማሰማራት መወሰኑን ገለጸ።

በቦስተን ዳይናሚክስ ተነድፎ በሥራ ላይ የዋለው ይህ የሮቦት ዉሻ፣ ለፖሊሶች አዳጋች በሆኑ ቦታዎች እና ሕንፃዎች ላይ በመሰማራት የፖሊስን ሥራ ተክቶ እንደሚሠራ ተገልጿል።

የሮቦት ዉሻው የተለያዩ የምርመራ እና የማነፍነፊያ መሣሪያዎች የተገጠሙለት ሲሆን ፖሊስ ሊደርስባቸው በማይችልባቸው አካባቢዎች ላይ ይሰማራል።
@Adis_zena
@Adis_zena
5.0K viewsedited  08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ