Get Mystery Box with random crypto!

🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ adis_zena — 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿
የሰርጥ አድራሻ: @adis_zena
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.96K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ዜና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us
ለማስታወቂያ ስራ @adis_probot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-26 23:48:31 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ፦
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ  https://t.me/eaesbot
ማየት ይችላሉ።

በኔትዎርክ መጨናነቅ ምክንያት በርካቶች ውጤታቸውን ለማየት እንደተቸገሩም እየገለፁ ይገኛሉ።
@Adis_zena
@Adis_zena
25.8K viewsedited  20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 21:33:28 ውጤት ሲለቀቅ ውጤት ማየት የምትፈልጉ እታች ያለው ግሩፕ ላይ Join አርገው Admission Number ይላኩ
https://t.me/+A-S9oS-LggpiZWM0
https://t.me/+A-S9oS-LggpiZWM0
24.6K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 20:17:52
ማስተካከያ ከአዲስ ማለዳ

የ2014 የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ከ980 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺ ነው ስትል መረጃዋን አስተካክላለች

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 130 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው የቅበላ አቅም የ2014 ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ከ20 በመቶ የማይበልጥ ነው ማለት ነው፡፡

ከፍተኛ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ማጋጠሙን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሰሙ ሲሆን፣ ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ምን ይደረግ በሚለው ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በውይይቱ የዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት አቅም ጋር የሚጣጣም ተማሪ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንን ተከትሎ፣ ዩኒቨርስቲዎች በመቀበል አቅማቸው ልክ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ አማራጭ እየተፈለገ ነው፡፡ በዚህም በልዩ ሁኔታ ለማለፊያ የቀረበ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ወስደው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረግ የሚለው አንዱ አማራጭ ሆኖ በመንግሥት በኩል እየታየ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያውቁት የተደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡
@Adis_zena
@Adis_zena
23.9K viewsedited  17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 18:29:27 ሰበር ዜና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

• ተማሪዎች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
@Adis_zena
@Adis_zena
22.6K viewsedited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 17:51:26 #ሰበር ዜና

ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው

ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኩረጃን ለማስቀረትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚል፣ በልዩ ሁኔታ ከተሰጠው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ውጤታቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከ28 ሺሕ እንደማይበልጥ አዲስ ማለዳ ከአስተማማኝ ምንጮቿ ሰማች፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲ በተሰጠው ፈተና ከ980 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባውን ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺሕ ገደማ መሆናቸው አዲስ ማለዳ ከትምህርት ሚኒስቴር ምንጮቿ ሰምታለች፡፡

ከፍተኛ ጥያቄ የሚነሳበትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል እና የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ላይ የሚስተዋለውን ኩረጃ ለማስቀረት ወሳኝ ነው የተባለለት ፈተና በጥብቅ ቁጥጠር ከ50 በሚበልጡ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

የፈተና ውጤቱ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በበይነመረብ ይፋ እንደሚደረግ፣ ተማሪዎችም በተሰጣቸው የመለያ ቁጥር ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ በውጤቱ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 130 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው የቅበላ አቅም የ2014 ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ከ20 በመቶ የማይበልጥ ነው ማለት ነው፡፡

ከፍተኛ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ማጋጠሙን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሰሙ ሲሆን፣ ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ምን ይደረግ በሚለው ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በውይይቱ የዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት አቅም ጋር የሚጣጣም ተማሪ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንን ተከትሎ፣ ዩኒቨርስቲዎች በመቀበል አቅማቸው ልክ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ አማራጭ እየተፈለገ ነው፡፡ በዚህም በልዩ ሁኔታ ለማለፊያ የቀረበ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ወስደው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረግ የሚለው አንዱ አማራጭ ሆኖ በመንግሥት በኩል እየታየ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያውቁት የተደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡

የ2014 የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ፣ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለውን ስብራት ለማከም እንደ አንድ የመፍትሔ አቅጣጫ ተወስዷል፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግበራዊ የተደረገው የፈተና ስርዓት፣ በዩኒቨርስቲ መምሀራን አማካኝነት፣ ተማሪዎችም ከተማሩበት አካባቢ ርቀው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢዎች ውስጥ የተሰጠ ነበር፡፡
@Adis_zena
@Adis_zena
22.7K views14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 13:57:25 የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀኑ  " ከነገ እንደማያልፍ " በዚገይ ደግሞ እስከ ቅዳሜ ሊሆን እንደሚችል ት/ት ሚኒስቴር ጠቁሟል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ930 ሺ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ውጤታችሁ ሊለቀቅ ስለሚችል በዚሁ @Adis_zena ቻናላችን ውጤት እደተለቀቀ ቀድመን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን። ሼር
@Adis_zena
@Adis_zena
21.4K views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 14:14:08
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና "ላልተገደበ ጊዜ" እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያገኙት ፈተናውን ወስደው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ተብሏል።

ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው መውሰድ የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሀመድ ለኢፕድ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየስድስት ወሩ ፈተናውን የሚወስዱበት ዕድል እንዳለ ኃላፊው ጠቁመዋል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ የፈተና ወጪያቸው እንደሚሸፈንላቸው ገልጸዋል።

በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ የሚሰጡ ከ300 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉ ያነሱት ኃላፊው፤ በየትምህርት መስኩ እየተደረገ በአስር ዙር ፈተናው ለመስጠት ታቅዷል። ሼር
@Adis_zena
@Adis_zena
23.9K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 10:56:55
ሰበር ዜና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት የሚያዩበት Website ተቀይሯል።

አምና የነበሩት አራት ውጤት የምታዩበት አማራጮች ተቀይሯል። በዚህ አመት የተማሪዎች ብዛት በእጥፍ ስለጨመረ አማራጮችን ወደ ስድስት አሳድገዋል።

የተማሪዎች ውጤት ወደ ሲስተም እየገባ መሆኑን እና የተማሪዎች ቁጥር ብዛት ስላለው ለመዘግየት አንዱ ምክንያት መሆኑን ተጠቅሟል።

ውጤት ልክ እንደወጣ ውጠታቹን የሚታዩበት websites እነዚህ ናቸው።

1. eaes.edu.et
2. eaes.gov.et
3. eaes.et
4. result.neaea.gov.et
5. Telegram @EAESbot
6. SMS 8046

ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ውጤታችሁ ሊለቀቅ ስለሚችል በዚሁ @Adis_zena ቻናላችን ውጤት እደተለቀቀ ቀድመን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን። ሼር
@Adis_zena
@Adis_zena
29.1K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 07:58:29 የ 12ኛ ክፍል ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ሊለቀቅ ይችላል

የ 2014 12ኛ ክፍል ከ ዛሬ ጥር 15 ጀምሮ እስከ ቀጣይ ባሉት ቀናት ይለቀቃል ተብሏል። በ 2014 የ 12ኛ ክፍል ፈተናን የወሰዱ ከ 947ሺ በላይ ተማሪዎች ሲሆኑ ውጤታቸውም ከጥር 15 ቡሃላ ይፋ እንደሚደረግ ተገልፆ ነበር።

በዚህ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ሊለቀቅ ስለሚችል በዚሁ @TIMIHIRT_MINISTER ቻናላችን ውጤት እደተለቀቀ ቀድመን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

#ሼር #Share
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER
37.8K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 20:30:09
የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ከጥር አጋማሽ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት እየተጠናቀቀ ይገኛል።

አጠቃላይ የፈተናው ውጤት ከዚህ ወር አጋማሽ ጀምሮ እንደሚገለጽ ይጠበቃል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና ከ900 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER
47.4K viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ