Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር 20 ደርሷ | 🌱መርጌታ መንግስቱ የባህል መዳኒት ቀማሚ🌿

ትላንት በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር 20 ደርሷል።

መምህራኑን ዩኒቨርሲቲው ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላ እያጓጓዘ የነበረው ተሸከርካሪ መንገድ ስቶ ገደል በመግባቱ በተከሰተው አደጋ እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አዳባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አህመድ ከሊል (ዶ/ር) ለኦቢኤን ተናግረዋል፡፡

በመኪና አደጋው ህይወታቸው ላለፈ መምህራን ዛሬ ጠዋት የአስክሬን ሽኝት በዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተደርጓል።
@Adis_Zena
@Adis_Zena