Get Mystery Box with random crypto!

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @abiyahmedaliofficial
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 111.80K
የሰርጥ መግለጫ

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!
Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!
Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2022-11-02 18:57:26
በጋሞ ዞን የጨንቻ ወረዳ የአካባቢው አኗኗርና ባህል መለያ ከመሆን ባሻገር፣ በኅብረ ቀለማት ቅንብር እና በሸማኔ ጥበብ የኢትዮጵያን ብዝኃነት የሚገልጹ የሸማ እና የጥበበ ዕድ ውጤቶችን ተመልክተናል። በአነስተኛ ሥፍራ ውጤታማ በሆነ የመሬት አጠቃቀም የጨንቻ መለያ የሆነውን አፕል እና አትክልት የሚያመርቱ፣ እንዲሁም ከብት ርባታን የሚከውኑ ቤተሰቦችን ጎብኝተናል። አንድ የእምነት ተቋምም ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ በተጨማሪ፣ ከብት ርባታ ላይ ተሠማርቶ የአካባቢውን ነዋሪዎች የወተትና የወተት ተዋጽዖ ተጠቃሚ አድርጓል። የእምነት ተቋማት ከሃይማኖታዊ ተግባራት ጎን ለጎን የማኅበረሰብን የዕለት ኑሮ የሚደግፉ ሥራዎችን መከወናቸው፣ በፈጣሪም በሰውም ዘንድ የሚያስመሰግን፣ አርአያነት ያለው ተግባር ነው።

Godina Gaamootti haalla jireenyaafi aadaa Aanaa Cenchaa ittiin addatti beekaman gamatti, hojiisaanii haluuwwan walsimsiisuufi ogummaa woyyaa dhahuutiin bu'aawwan hojii huccuufi ogummaa harkaa daneessummaa Itoophiyaa mul'isan daawwanneerra. Bakka xinnaarratti ittifayyadama lafaa milkaa'aa ta'een appilii Cenchaan ittiin beekamuufi warra kuduraa hoomishan akkasumas maatiiwwan horsiisa looniirra jiran argineerra.
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0ZT4U4p3ksrcWZq5VTxuvmw4Bi346jV8pKxPqZ1mMeqbtjeErkvQTBEgs3FAHTXqPl&id=100044183688553
18.9K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 12:24:28
ሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋን በየፈርጁ መታደሏን ከሚያሳዩን ሥፍራዎች አንዱ የጎፋ ዞን ነው። ከዞኑ አልፎ ክልሉን ለማልማት የሚያስችል ያልተነካ ዐቅም አለው። ባለ ግርማ ሞገሱ ወይላ ተራራም በውስጡ የያዘው ብዝኃነት የሀገራችን የኢትዮጵያ ማሳያ ያደርገዋል። የዶጫ ደምበላ አርሶ አደሮች በ80 ሄክታር ላይ ያመረቱት ሰሊጥ፣ ማሾ፣ አኩሪ አተር፣ ጤፍ እና ፍራፍሬም አካባቢው የተፈጥሮ በረከት እንደተቸረው የሚያሳዩ ናቸው።

Gofa zone is one of several locations that demonstrate how Ethiopia is endowed with a range of natural resources. It has vast potential that could readily overflow to help the entire region develop. The diversity of Mount Weyila is yet another representation of our country. Farmers in Docha Dembela kebele have grown sesame, masho, soybeans, teff, and fruits on 80 hectares, showing how nature has blessed the region.
67.2K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 19:30:12
የተጣለባችሁን ተስፋ እውን እንድታደርጉት አደራ እላለሁ።
I entrust you with bringing Africa's hope to fruition.
17.7K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 18:51:00
አፍሪካ አሁን የሆነችውን ብቻ ሳይሆን፣ ያላትን ዐቅም አገናዝበው ልትሆን የሚገባትን የሚቀምሩላት ወጣት ልጆቿ ናቸው። ፓንአፍሪካዊነትን በአመራራቸው የገለጡ የትናንት ፈር ቀዳጆች ለዚህ ጽኑ መሠረትን ጥለዋል። አህጉራችን ያላትን ዐቅም ተጠቅማ ለሁሉም ዜጎቿ ምቹ እንድትሆን ማስቻል በተለይም ከአፍሪካውያን ወጣት መሪዎች ይጠበቃል። ስለዚህም የተጣለባችሁን ተስፋ እውን እንድታደርጉት አደራ እላለሁ።

Afrikaan bakka amma jirturraa fageessanii ilaaluudhaan humna isheen qabdu hubatanii waan isheen ta'uu maltu kan wixineessaniif ilmaanshee dargaggootaati. Dura buutonni kaleessaa hooggansa isaaniitiin Paan Afrikaaniizimii mul'isan kanaaf bu'ura cimaa kaa'aniiru. Ardiin keenya humna qabdutti fayyadamtee lammiileeshee hundaaf kan miijattu akka taatu gochuun keessumaa hooggantoota dargaggootaarraa ni eegama. Kanaafuu abdii Afrikaa akka milkeessitanin imaanaa isinii dhaama.
20.0K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 18:50:54
ጋብቻ የሀገር መሠረት ከሆኑት ተቋማት አንዱ የሆነው ቤተሰብ የሚመሠረትበት ነው። የወዳጅነት ፓርክ ምዕራፍ ሁለትን በከፈትንበት ዕለት በሠርግ ዐጸዱ ጋብቻችሁን የፈጸማችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ኢትዮጵያውያን በሀገራችን፣ ሌሎችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ዓለም አቀፍ፣ ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ክንውኖች የሚፈጸሙበትን ድንቅ ስፍራ በሠርጋችሁ ደስታ አድምቃችሁ አስጀምራችሁታል።

Marriage is a means of establishing a family, which is one of a nation's core institutions. Congratulations to all who married at the wedding garden on the day the Friendship Park phase two was launched. With the joy of your wedding, you have blessed this wonderful site that welcomes Ethiopians as well as visitors for international, national, and social activities.
29.7K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 12:19:21
የወዳጅነት ፓርክ ሁለተኛው ምዕራፍ ዛሬ ተከፍቷል። ስፖርትን፣ ጨዋታንና ማኅበራዊ መስተጋብርን ያቀናጀ ነው። ልጆች እየተጫወቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ይለማመዳሉ። ወጣቶች ያነብባሉ፣ ደግሞም ስፖርት ይሠራሉ። ወላጆችና አያቶች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው ማኅበራዊ ልምዳቸውን ይለዋወጣሉ። አዲስ ተጋቢዎች በሠርግ ዐጸዱ ጋብቻቸውን ይመሠርታሉ። የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን።

Boqonnaan lammaffaa Paarkii Freendshiippii har'a banameera. Ispoortii, taphaafi walittidhufeenya hawaasumma kan waliin qabatedha. Daa'imman taphataa saayinsiifi teknooloojii shaakalu. Dargaggoonni ni dubbisu; ispoortiis ni hojjetu. Warri daa'immaniifi akaakayyuuwwan daa'immansaanii waliin dhufanii muxannoosaanii hawaasummaa walii qoodu. Warri sirna gaa'elasaanii raawwatan bakka cidhaaf qophaa'etti qubeelaa kakuusaanii waljijjiiru. Itoophiyaan borii kan wayyoofte akka taatu dhaloota wayya qabu horachaa itti fufna.
30.9K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 13:38:03
This is Ethiopia's #GreenLegacy. Let’s work together to mitigate climate change and forge a new system of green living, green behaviour and green development.
8.0K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 09:56:00 የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ሆይ

ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው።

የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ።
9.2K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 08:51:05 እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

በነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) መወለድ ዓለም እጅግ ተጠቅማለች። የዓለምን ታሪክ ቀይረዋል። የሰው ልጆችንም ሕይወት ለውጠዋል።

የመውሊድን በዓል የምናከብረው የዓለምን ታሪክና የሰው ልጆችን ሕይወት በመለውጥ መሆን አለበት።
በግብርና እና በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ እየሠራን ያለው ሥራ የሀገራችንን ታሪክና የሕዝባችንን ሕይወት የሚለውጥ ነው።

ኢትዮጵያን ከጦርነት በመገላገል ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ታሪክና ሕይወት ወደሚለውጡ ዕቅዶቻችን እንዞራለን። የጀመርነው "የሌማት ትሩፋት" የቤተሰቦቻችንን ሥርዓተ ምግብ እንዲለውጥ ተግተን እንድንሠራ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁን
12.2K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 18:08:50
የእንጂባራ ዩኒቨርስቲ ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ አስተማሪ የሆነ ሥራ ሠርቷል። ዩኒቨርስቲው ግቢውን በማሣመር የሠራውን አኩሪ ሥራ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ችግር በመፍታትና በዓለም ደረጃ የሚወዳደሩ ልሂቃንን በማፍራት ይደግማል ብዬ አምናለሁ።

Yuniversiitiin Injibaaraa mooraasaa baruufi barsiisuuf mijataa taasisuuf hojii barsiisu hojjeteera. Yuniversiitichi hojii boonsaa mooraasaa bareechuudhaan hojjete rakkoo hawaasichaa hiikuufi hayyoota sadarkaa addunyaatti dorgoman horachuudhaan ni dabala jedheen amana.
17.8K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ