2022-12-23 17:47:03
بسم الله الرحمن الرحيم ቁርኣን
በቀለሉ እንድንሓፍዝ
ከሚረዱን ነገሮች
ክፍል አራት ከዛ ቡኋላ እንደ መጀመሪያው አካሄድ እየሄድን አያዎችን አያይዘን መቀጠል ነው።ከቆምነበት እንቀጥላለን
ልብ በሉ ሥታሓፍዙ ብቻ በጭንቅላታችሁ መሆን የለበትም።
ለምሳሌ በአይናችሁ በልባችሁ በጆሯችሁ በጭንቅላታችሁ መሆን አለበት በረከሏሁ ፊኩም በዝርዝር እንዴት ካላችሁኝ
ለምሰሌ በአይናችን የምንሓፍዘውን ሱራ እና አያዎች ከነ ቁጥራቸው በደምብ ማየት ነው። ምክንያቱም በሂፍዝ በምንቀራ ሰዓት ቶሎ ለማስታወስ በጣም ይረደናልና። በጆሯችን ደግሞ ቃሪዕዎችን እና ራሳችንም እየቀራን ቢሆን ድምፃችን ከፍ አድርገን ለራሳችን በሚሰማን ልክ በደምብ መደመጥ የምነሓፍዘውን ሂፍዛችንን ሳንጀምር በፊት ደገግመን ማዳመጥ ይሄም ሂፍዙ እንደይከብደን ያግዘናል።
በልባችን ደግሞ የቁርኣኑን መሃባ ነው መሓፈዝ ያለብን ምክንያቱም አንድ ሰው አንድን ሰው ሲወደው ምን የክል ነው የሚያስበው የሚያስታውሰው ምን ያክል ልቡ በወደደው ሰው ለይ ይንጠለጠላል መልሱን ለራሳችሁ ልተወው እና
ልክ እኛም ቁርኣኑን ከዛ በበለጠ ልንወደው ልናፈቅረው ይገባናል እና ይሄ ደሞ ጥቅሙ ሁሌም ከቁርኣን ጋር እንድንኖር እና ከሱ ውጭ ጓደኛ እንዳያስፈልገን ያደርገናል ይሄ ከሆነ ደግሞ ሰለሳ ጁዙ ቁርኣን ልክ እንደ ፈቲሃ ይሆንልናል ማለት ነው እንደ ፈቲሃ ቀላል ይሆናል ለማለት ነው
ይሄ ደሞ ትልቅ እድል ነው አሏህ የወፈቀቻው እንጂ የሰው ልጆች ሁሉ አያገኙትም
ይሄ ብቻ አይደለም ቁርኣን ለእኛ የደስታችን ምንጭ የልባችን መርጊያ የጀናት መግቢያችን የሁለት አገር ጀነትን የሚያሰጠን ማን ነው ቁርኣን ነው ኣ?
ጌታችን አሏህ ሱብሃናው ወተዓላ እንዲህ ብሎ ያበስረናል
إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا
ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ም
ንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡ 9/سورة الإسراء
ብዙዎች መጥቀስ ይችላል አጣር ለድርገው ብዬ ነው
ሌላኛው በጭንቅላታችን ነው የምንሓፍዛው እና ጭንቅለታችን በዱኒያዊ ጉዳይ ብሎም ከልክ ባለፈ ሀሰብ ብዚ ልናደርገው አይገባም ምክንያቱም ጭንቅላታችን በተለያዬ ነገር ብዚ ስሆን እሽ ብሎ ቁርኣኑን ልቀበለው አይችልምና።
በመጨረሻም ሂፍዙን ስንጀምርም ይሁን ሥናቆም ብሎም ባገኘነው አገጠሚዎች ሁሉ
ጌታችንን አሏህን ሱብሃናው ወተዓላ መለመንን ዱዓ መድረግን መርሳት የለብንም ምክንያቱም ሁሉም ከአሏህ ተውፊቅ ቡኋላ ነው ና
አላለቀም ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ
ኡሙ ዑሰይሚንhttps://t.me/+LhY2Pp1VFwdiOGNk
https://t.me/+LhY2Pp1VFwdiOGNk
104 views14:47