Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2022-12-05 16:42:53
በገበታ አድማስ የታጠረው የአማራ ፖለቲካ……!

አቶ የሱፍ ኢብራሒም

በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ በተቀመጡ ሹማምንት እግሮች ስር የንፁሃን አማራዎች ደም እንደ ጅረት በከንቱ እየፈሰሰ ነው። በአንድ ሕዝብ አንገት ላይ የተሳለው ካራ ከ50 አመታት በላይ በቅብበሎሽ እዚህ ደርሷል። ገዳዬች ተሿሚዎች ናቸው፤ ተጨማሪ ጭፍጨፋ ተጨማሪ ጥቅምና ስልጣን ያስገኛል።

አማራውን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ አካላት አሁን ተሿሚ፣ ተፎካካሪ ወይም አማካሪ ናቸው፤ ለግድያ አገልግሎታቸው ድጎማ እና ጡረታ ይከፈላቸዋል። የአናቂ አንቂዎችን በይፋ ያደራጃሉ፤ ሚዲያ ከፍተው የፕሮፖጋንዳ ዘርፉን ይመራሉ። ፋኖ ባለበት ቦታ ሸኔ እንደማይኖር ይታወቃል፤ ሆኖም የአራጆች ጠበቃ በመሆን ሟች ወቃሽ የሆነ አሉባልታ ይነዛሉ። ምናልባት ግን በዚህ ሁኔታ የተመኙት የሚቀር አይመስልም!

የአማራ ገዳዬች ሱፍ እና ከረባት ለብሰው የሃገሪቱን መድና ጨምሮ በተለያዩ ከተማዎች ውስጥ በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ፤ በመድረኮች ላይ ይሰየማሉ። ቅንጣት ስጋት አይሰማቸውም፤ የፖለቲካ አማካሪ፣ ድፕሎማት፣ ተንታኝ እና አስተማሪም ናቸው። ካባዎችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል፤ በአማራ ከተሞች እና መድረኮች ላይ ጭምር!

በገበታ አድማስ የታጠረው የአማራ ፖለቲካ ለቫምፖየሮች የደም ግብር ማቅረቡን ቀጥሏል። ለማንኛውም የበሬ ካራጁ ፖለቲካ ካልቆመ ደም መፍሰሱ አይቆምም!
1.4K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 15:57:45
በወለጋ እየሆነ ያለውን ግልፅ አርጎ የሚያሳይ መረጃ!

#ሙሉውን ያድምጡት!

<< ..ከእስር ቤት የወጣው እንኳ 80 አስከሬን ነው! >>

<< የላኩን እነሽመልስ አብዲሳ ናቸው! >>

#ሼር
1.9K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 21:25:19
እነዚህ የአለምን ክፉና በጎ እንኳ በቅጡ ያለዩ ብላቴናዎች አንገት ላይ ቢላዋ አጋድሞ  ለማረድ ሰይጣንን ራሱ መሆን ይጠይቃል!

ይሄን ታሪክ ተሸክመን ነገስ ወዴት እንደምናመራ አስባችሁታልን ?
3.7K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 21:16:22
"ሀገር እየመራን ነው" የሚሉትም ሆኑ "ስለኦሮሞው ህዝብ ቆመናል" የሚሉት ፥ በእነሱ የጥላቻ ፖለቲካ መርዝ የተፈጠረ ፥ ይህ አይነቱን ዘመን የማይሽረው ጥቁር የታሪክ ሸክም ፥ ባለእዳ ያደረጉት ማንን እንደሆነ ግን ያውቁ ይሆንን ?

እኔ በጣም ልቤ የሚሰበረው ፥ ከዛሬውም በላይ የነገውን ሳስብ ነው!
3.6K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 20:22:24
ጨፍጭፎና አርዶ በእሳት እያቃጠሉ ሸልፊ የመነሳትን ያህል የደረሰ አውሬነትና የጭካኔ ጥግ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው!
3.7K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 19:56:42
3.7K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 19:56:19 5 አመት የዘለቀውን የዘር ፍጅትና ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እጥፍ ድርብ የሚያደርጉት " የህዝብ በዝምታ ተባባሪነትና መንግስታዊ ክህደት" ናቸው!

እንደአለመታደል ሆነና ፥ በአንድ መንግሥት አለሁ በሚልባት ሀገር ያለእረፍት ይህ ሁሉ እልቂትና ግፍ ሲፈፀም የመጀመሪያው እርምጃ ፥ እንደመንግስትም ሆነ እንደህዝብ የሚፈፀመውን እልቂት በስሙና በአፈፃፀሙ ልክ በትክክል ጠርቶ በአደባባይ በግልፅ ከማውገዝ ይጀምራል፡፡

ነገርግን ይህ ሁሉ ለሰሚው የሚከብድ በሀገራችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ እልቂትና ፍጅት ሲፈፀም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት የነበረበት መንግሥት ተብዬው ሀይል አይደለም ወንጀሉን በትክክል ገልፆ በማውገዝ እልቂቱን የማስቆም መንግስታዊ ግዴታውን መወጣት ይቅርና እኚህን " እንደቅጠል የሚረግፉ ዜጎችን ጭምር ወክዬ" ተቀመጥኩ የሚለው ፓርላማ የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንኳ ነፍጓቸዋል፡፡ እልፍ ሲልም እልፍ ሲልም ከችግኝ ተከላ ጋር እያነፃፀሩ መሳቂያና መሳለቂያ አድርገውታል፡፡ ይህ ጭፍጨፋም ገና በጧቱ ያልተገታውና ተጠናክሮ የቀጠለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡

መላው ለአንባገነን መሪዎች ሀዘን 40 ቀን ድንኳን ጥሎ ደረት እየደቃ ሲነፋረቅ የምናውቀው የኢትዮጵያ ህዝብም ፥ በሚሊየኖች እልቂትና ስደት ላይ ሰብአዊነቱ ርቆታል ፥ የእንባ ከረጢቱ ደርቆበታል ብሎም ለማውገዝ የሚያስችለው አንደበቱ ተቆልፎበታል፡፡ ይህ ዝምታው ነገ ማንንም ወደማያስቀር የእልቂት ውቅያኖስ እየዘፈቀው መሆኑን እንኳ ለአፍታ እንዳያስብ አድርጎታል፡፡

ከዝምታው ባሻገር ሌላው ሰቆቃና በደሉን እጥፍ ድርብ የሚያደርገው ክህደት ነው፡፡፡ መንግስትም ሆነ በዙሪያው ያሉ ( ሸኔ ፥ አመራሮች ፥ አክቲቪስቶች ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፣ …ወዘተ) ይህን በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀም እልቂት ፥ በስሙ ጠርቶ ከማውገዝና እንዲቆም ከመረባረብ ይልቅ ፥ ተራ ግጭት በማስመሠል እልፍ ሲልም በመካድ ብሎም "አማራ ተጨፈጨፈ" ለሚለው መራራ ሀቅ አቻ ማስተባበያ ጨፍጫፊና ተጨፍጫፊ ታሪክ በመፍጠር እልቂቱ እንዲባባስና ዘላቂ መፍትሔ ማምጣቱ ቀርቶ ወደማንወጣውና ማንኛችንንም ተራፊና አሸናፊ ወደማያደርገን ዘላቂ የእርስበርስ እልቂት ውስጥ እንድንገባ ከፍተኛውን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

አንዳች ልበ-ስውርነት ሆኖ እንጂ ፥ ለኦሮሞም ሆነ ለሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የሚያስብ ሀይል ፈፅሞ ይህ አይነቱን ነውር ከመፈፀም በተቆጠበ ነበር፡፡ ይህ የሚፈፀመው እልቂትም እነርሱ የስልጣን ጥማታቸውን ለማርካትና በዙፋን ለመሰንበት ሲሉ በየአደባባዩና መድረኩ ሲረጩት የነበረው የጥላቻ ትርክትና ፖለቲካ ያፈራው መርዛማ ፍሬ ነው፡፡

ሀገራችን የተሸፋፈነውንና የተደበቀውን ገላልጦ የመመልከት ሀያልነት ያለው ፈጣሪ እንኳ የማይፈራባት የጭካኔ ምድር ሆናለች!
4.0K viewsedited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 18:54:28
ይቺን የሰቆቃና የእልቂቱን ጥቂት ገፅታ ብቻ የምታሳይ ምስል ተመልከት!

ክቡር የሆነውን ሠብአዊነት የተሰኘ ሰዋዊ የመመልከቻ መነፅር አድርግ ፥ ከዚያም "ነግ በእኔ!" የሚለውን የሀበሻ ብሒል አስታውሰህ " የሚታረዱትና የሚጨፈጨፉት ብሎም በእሳት የሚቃጠሉት የኔ ቤተሰቦች ቢሆኑስ?" ብለህ ለአፍታ አሰላስል?

ምን ተሠማህ ?

"አማራ" ተብለው ስለሚታረዱና ስለሚጨፈጨፉ ብቻ "አማራዎች ማንነትን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ ተፈፀመባቸው"  እንላለን፡፡ ሀቁም ይሄው ነው!

ነገርግን በእንዲህ አይነቱ መንገድ 5 አመታት የቀጠለው እልቂት ከአማራው አልፎ  ፥ የእያንዳንዳችን ቤት ሳያንኳኳ እንደማይቆም ለአፍታ አስበኸው ታውቃለህን ?

#Stop_Amhara_Genocide
4.1K viewsedited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 20:10:52
1.2K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 20:10:44 Stop fabricating an equivalent crime story!

#Caution

Oromo politicians, activists, leaders and other stakeholders should refrain from running to find a propaganda equivalent to the 5 years of relentless massacre and displacement and start looking at themselves.

It is important to understand that all the horrible massacres and persecutions that have taken place over the past years, including today, are the result of the politics of hatred that they have been promoting in public in order to satisfy their thirst for power and to stay in power. This is a destructive way that will make the Oromo people, who they claim to represent, bear the debt of hatred in the next generation, and is pushing us into a conflict where none of us can be victorious.

yes! We have squandered many opportunities to build lasting peace and stability, because of that, now we are found in the last hour of entering a conflict that we cannot stop. The entire Ethiopian is also approaching to pay the price for his silence.

Caution Caution Caution!

#Stop_Amhara_Genocide
#Oromia_Wollega
1.3K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ