Get Mystery Box with random crypto!

ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele12 — ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele12 — ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekele12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 500

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-31 07:31:48
"…የዛሬው የዕለተ ቅዳሜ ከሰዓት መርሀ ግብራችን ወደ ፍጻሜ ምእራፍ እየተቃረብን ነው። ከዚያ በፊት ግን "ግራቀኝ የገባው" አንድ የጂጂን እህት የቀዶሞዋን የዶክተር ወዳጄነህን ሚስት የዘማሪ ሶፊያ ሽባባውን "እንባና ሳቅ" ከተሰኘው አልበሟ ላይ አንድ ሙዚቃዊ መዝሙር ልጋብዛችሁ።

"…ወልዳችሁ ያልጨረሳችሁ በፍፁም እንዲህች ብላችሁ እንዳትስቁ። ተሳስታችሁ አላስችል ብሏችሁ የሳቃችሁም ካላችሁ አጠገባችሁ ያገኛችሁትን ብረት ንከሱ። ብረት ካጣችሁ ማንኪያም ሹካም ቢሆን ሞክሩ። አቤቱ ይቅር ይበለን። ከምር በጠሽ አይሳቅም።

• እኔምለው ትጦዛለች ግን…?
169 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48 "…እንቀጥል…?
154 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
"…አድማጭ ተመልካቾቻችን እዚህ ሃገረ ጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ ከሚገኘው ስቱዲዮአችን የምናስተላልፈው የቅዳሜ ከሰዓት ዝግጅታችን እንደቀጠለ ነው።

"…ከዚህ 1ኛ ደረጃ ታጥቦ ከተቀሸረ እልል የተባለለት አሽቃባጭ ሙዚቃ እና የጴንጤ መዝሙር በኋላ እንመለሳለን። መልካም ቅዳሜ ምሽት ይሁንላችሁ…!! ፈታ በሉ…!!

"…የጋሽ ሽባባው ልጅ ሶፊ በዚሁ በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ ፕሮግራሙን ስለምትመለከተው በኢራቅ፣ ወይም በኢኳዶር አምላክ ስም አስተያየታችሁን እንድትሰጧት ትጠየቃላችሁ።

"…ወዳጄ አይተ ኢሳይያስ ለሜንጤ መስሚያው ጥጥ ነው።
153 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
ማሳሰቢያ፣ ማስታወሻም፣ ማስጠንቀቂያም…!!

"…ይሄ የእኔ የዘመድኩን በቀለ ዘመዴ ነጭ ነጯን የምዘራበት የግል የቴሌግራም ቻናሌ ነው። በዚህ ቻናሌ ላይ እኔ ዘመዴ ስፈልግ እቀልዳለሁ፣ ስፈልግ እቀደድበታለሁ፣ እበረጠቅበታለሁ፣ ስፈልግ መረጃ አቀብልበታለሁ፣ ስፈልግ እነቋቆርበታለሁ፣ ስፈልግ እንበጫበጭበታለሁ፣ ስፈልግ አንበጫብጭበታለሁ። አለቅስበታለሁ፣ ስፍለግ አስለቅስበታለሁ፣ እሟገትበታለሁ፣ እከራከርበታለሁ፣ እገለፍጥበታለሁ፣ አሽካካበታለሁ፣ እንዳሻኝ እሆንበታለሁ።

"…ስማስሚ አንተ እና አንቺ የወሬ ጠኔ ይዞሽ፣ አልያም ፔጄ ተመችቶሽ ወደ ፔጄ መጣህ መጣሽ እንጂ እኔ አላመጣሁሽም፣ አልመጣሁብህም። መጀመሪያ ይሄን እወቅ እወቂ። በእኔ በዘመዴ ፔጅ መሳቅ መጫወት፣ መፎጋገር፣ መነታረክ መብት ነው። ከዚያ ባለፈ ግን ወደ ፔጄ ዘለህ ገብተህ ስታበቃ እንደአሽከርህ ቆጥረህ ይሄን ደረቅ ቂጣ የቀደደውንና ያሰፋውን አፍህን እከፍትብሃለሁ፣ የምትል ስድአደግ ባለጌን ወገብ ዛላህን ብዬ ድራሽ አባትህን ነው የማጠፋው። ጨምላቃ… ተጠንቀቅ።

• ተሳስተህ፦ እዚህ ገብተህ ነውር የሆነ ስድብ እሳደባለሁ ብትል አባቴ ይሙት አለቅህም። ንዴትህን እዚያው ሚስትህ፣ ባልሽ ላይ ተወጪ እንጂ እኔ ላይ አይፈቀድም። ካካ ነው፣ እፉ ነው።

"…እርግጥ ነው ቴሌግራሜ ምርር አድርጎም ያስለቅሳል። እልልል አድርጎም ያስጨበጭባል። አንዳንዴም ዘና ፈታም እንልበታለን እንጂ ሁሌም እኚኝ ብቻ አንለበትም። ይልቅ በነፃ ተጠቀምበት። አይደለም እንዴ…?…ደግሞ የሐረርጌ ልጅ እኮ ነኝ። እንደልቡ፣ መራታ የሐረርጌ ልጅ። ጭንቅ የማልችል የሐረርጌ ልጅ። ካልተመቸህ ውልቅ በል እንጂ ፔጄ ላይ መጥተህ አስታውካለሁ ብትል ከነው የምቀስፍህ። ሰምተሃል…!

• የእኔ ፔጅ እንደ ገነት ያለ ነው። አንዴ ከወጣህ ተመልሰህ አትገባትም።

"…ጨዋታ ቁምነገራችን ይቀጥላል…
144 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
፫ኛ፦ ሰለሜ ሰለሜ በዘመነ ብልፅግና…

ሀ• መጀመሪያ ሥርዓቱ ወፋፍራም ሴቶችን ከጂምም ከጸሎት ቤትም ይመርጣል። ከዚያ ሜካፕ ቀባብቶ የጠቆሩትን አንጥቶ ለአደባባይ ያበቃቸዋል።

ለ• የሥርዓቱ መሲህ የሥርዓቱን ነቢያት አምጥቶ "በጌታቸው ፍቅር" እንዴት ሰለሜ ሰለሜ መጫወት እንዳለባቸው በሚገባ ያሰለጥኗቸዋል።

ሐ• ከዚያም ሥልጠናውን የጨረሱት ሞዴላ ሞዴል ሚንስትሮቻችን ሴቶች በሚደፈሩባት፣ ነፍሰጡሮች በሚታረዱበት፣ ህጻናት እንደ ጭዳ በሚታረዱበት ሃገር እነሱ ፌራቸውን እየተቀቡ ሰው መሳይ በሸንጎ ሆነው ባላየ ባልሰማ ዳሌያቸውን እያደለቡ በቤተ መንግሥት ሰለሜ ሰለሜ ይጫወታሉ።

"…እርጎጌ… ሙፈሪያት… ከዚያ ማነች አላወቅኳትም ከሙፈሪያት ጀርባ ያለችዋን። ዥልጥ ገተት ሁላ አለ ታሜ…! የበሻሻው ፈላ ግን ሸገር መረጣ ላይ እንዴት ነው።

"…የእለተ ቅዳሜ መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው።
132 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
"…ሰለሜ ሰለሜ…!!

"…አሁን ደግሞ በ3ቱ ዘመናት ማለትም በዘመነ ህወሓት፣ በዘመነ ኃማደ፣ በዘመነ ዐቢይ አህመድ ሰለሜ ሰለሜ የደረሰበትን እድገት እንመለከታለን።

፩ኛ፦ ዘመነ ህወሓት፦

"…ይሄ የምታዩት ፎቶ በዘመነ ህወሓት ይጨፈር የነበረው ሰለሜ ሰለሜ የሚባለው ተወዳጅ የሀድያ ብሔረሰብ ጭፍራ ምን እንደሚመስል ነው። አስጨፋሪው ከኋላ ይሆንና ጨፋሪዎቹን በሰደፍ አናት አናታቸውን ብሎ ይደፋቸዋል። በጥግ በኩል ደግሞ የምታዩት በአግአዚ ወታደር እየተወቀጠ ያለ ኢትዮጵያዊ ነው። በዘመነ ህወሓት ሰለሜ ሰለሜ እንዲህ ነበር። ወይ ጊዜ እንዴት ይሮጣል በማርያም። መረሸ እኮ።
131 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
"…ይህቺ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን እንዲህ በፎሊሶች ተከባ የሃይላንድ ውኃ የምትጠጣዋ ችግኝ ደግሞ የታደለች ናት ጃል። ግን ስንተኛ ሚሊዮኗ ችግኝ ትሆን?… ትራፊክ ግን ገንዘብ ላይ ግድ የሌለው ለምንድነው። ማነህ ሹፌር ጉቦ የሰጠኸው ትራፊክ ገንዘብህን በከንቱ አልባከነብህም። ይኸው ችግኝ እያጠጣልህ ነው።

"…ጎንደር የዝናብ ውኃ ይጠጣል በኦሮሚያ ችግኝ የሃይላንድ ውኃ ይጠጣል… ይኸው ነው።
128 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
"…አንድ ለ ሦስት…? …በቃ ፎቶ ተነሥታችኋል እናንተም ተነሡ…!!… ችግኟ ራሷ ጨነቃት… አልሸባብ 150፣ ደቡብ ሱዳን 150 ሰሜን ሱዳን 80 ኪሜ ወደ እኛ ገብተው የሚዋጉን አይመስልም እኮ ይሄ ሲታይ…
135 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:31:48
"…ኧረ ውይይ ውይ በእናትህ ቶሎ በልልኝማ… ወገቤ ሊቆረጥ እኮ ነው…እባክህ ፎቶውን ቶሎ እንሣኝ እና ቀና ልበልበት… ኣአዓ… እስከ አሁን 5.3 ሚልዮን ችግኝ በዚህ ቅልጥፍና ነው ተተከለ ተብሎ ሪፖርቱ እየቀረበልን ያለው…!! …እኔየምለው ችግኙ ከተተከለ በኋላ እንዲህ ፍዳ ከምትበላ ፎቶ ባትነሣስ ቢቀር…? ሃኣ…?

"…ጠቅላዩ እስከ አሁን አልተከለም። አልተገለጠምም።
138 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 08:08:36 እንኳን ወደ EXODUS የገበያ ማዕከል በድህና መጡ የትኛዉንም ትእዛዝ በዝህ bot አማካኝነት ማዘዝ ግብይት መፈፀም ይችላሉ እኛ እስካሉበት ድረስ ይዘን እንመጣለን በተጨማሪም የምንሰራቸው ስራዎች ድለላ ነክ ስራዎችን እንሰራለን::

አንድ ሰው ስጋብዙ 1ብር ያገኛሉ

እስካሁን 0 ሰው ጋብዛሉ ።

የእርሶ መጋበዣ ሊንክ : https://t.me/Exodusmarket_bot?start=YWEOG
130 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ