Get Mystery Box with random crypto!

ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom3in1 — ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪
የቴሌግራም ቻናል አርማ wisdom3in1 — ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪
የሰርጥ አድራሻ: @wisdom3in1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 580
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ሌላ ስለምንም አናወራም...ግን " በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" ስለተባለለት ስለ እርሱ.......እናውጃለን!!!!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-04 14:46:52
“እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።”
— ዕብራውያን 7፥22

እዉቀት ወደ አካል ካላመጣን፥ በእዉቀት ዉስጥ ያለዉ ፍርድ፥ ከኩነኔ በላይ አስገባሪ ይሆንብናል፤ ምን ማለቴ መሰላችሁ!፥ እግዚአብሔርን የምናዉቅበት እዉቀት፥ ወደ ክርስቶስ ካላደረሰን፥ ገና በወደቀዉ መንፈስ እንኖራለን እንደማለት ነዉ፤ ከወደቀዉ ዓለም ይልቅ የወደቀዉ መንፈስ ዉስጥ ያለዉ ክስረት ይበልጣልና፥ ስለዚህ የምናወራለት እዉቀት፥ ዋስ አስፈልጎት ነበር፤ እግዚአብሔር በራሱ እዉቀት ሊሞላን፥ እዉቀት የሚገለጥበትን ቃል ሰጠን፥ "ቃልም ስጋ ሆነ"፤ እንግዲህ ይህ ቃል ነዉ ለሚሻል ኪዳን ዋስ የሆነን!

እነሆ ድነት በዋስ ነዉ፥ ፅድቅ በዋስ ነዉ፥ መንፈሳዊነት በዋስ ነዉ፥ የተቀበልነዉ ሁሉ በዋስ ነዉ፥ ስለሆነም ከእኛ የሆነ አንዳች ሊኖር አልተገባምና፥ እንዲያዉ ዋሳችንን እያመሰገንን በእረፍቱ ዉሃ ዘንድ በሰላም እንኖራለን፤ ይህም የታመነዉና እዉነተኛዉ ዋስ የተባለዉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ!

እንወዶታለን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
849 views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 16:49:23
“አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ በፊትህ ያልፋል፤”
— ዘዳግም 31፥3

ለሩቅ ዘመናት ከሕዝቡ ጋር ያልፍ የነበረዉ የተቀደሰዉ ታቦት፥ በእስራኤል መንደር የገናናነታቸዉን አርማ ሆኖ፥ በዙሪያቸዉ ከመሸጉት ይታደጋቸዉ ነበር፤ ሆኖም ግን ታቦቱን በመካከላቸዉ እያዩት፥ መቅረብ ግን የማይችሉ ነገዶች በዉስጥ እየበዙ ነበር፥ "ታቦቱን ታዉቀዋለህ?" ስትሉት "አዎ!" ይላችኋል ግን መቅረብ አይችልም፥ ማዋራት አይችልም፥ መዳሰስ አይችልም፥ ግን በመካከላቸዉ ኖረ፤ የድላቸዉና የሰላማቸዉ መንስኤ ሆኖ እንኳን አይጠጉትም፥ ታዲያ እግዚአብሔር የሚያዋራዉ ትዉልድ ፈለገ፥ ታቦቱ ኢየሱስ ከመስዋት የዘለለ ቀረቤታ አጣ፤ እናም እስራኤል ሆይ!፥ እግዚአብሔር ብቻዉን የድል አምላክ እንደሆነ ሊያስይህ፥ አሁን በሰራዊት ብዛት ሳይሆን በሰራዉ ስራ ኋያልነት ሊታደግህ፥ በፊትህ አለፈ፤
እነሆ ዛሬ!፥ አምላካችን እግዚአብሔር በፊታችን ነዉና ማለዳ ማለዳ ያለቀ ስራ በእሱ እናያለን!፤ አሰናካዩ ተቀድሞል!፥ እግዚአብሔር አምላክ ከፊታችሁ ወቷል!!!

#እንወዳችኋለን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
817 views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:29:56
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
— ኢሳይያስ 40፥31

ወዳጆቼ አንድ ነገር ልበላችሁ!፥ እግዚአብሔርን በመተማመን ለሚጠባበቁ እንዲህ ይሆንላቸዋል፦ ኋይላቸዉን ያድሳሉ፥ ክብራቸዉን፥ ሞገሳቸዉን፥ መንፈሳቸዉን፥ ረሃባቸዉን፥ ፍቅራቸዉን፥ እይታቸዉን ያድሳሉ፤ ስለዚህ መተማመን በሚፈጥረዉ መጠበቅና፥ እርግጠኝነትን በሚያስከትል ሕይወት በቀላሉ ይተካል

የዉሃዉን መናወጥ ሲጠባበቅ የነበረዉ ሰዉ፥ ህመምተኛዉ ያለ ጤነኛዉ ሰዉ፥ ወደ መጥመቂያዉ መግባት አቅቶት፥ ከነዉጡ ሲጎመጅ ታከተ፤ ምክንያቱም ከሚናወጠዉ ጋር ለመገናኘት ኋይል አልነበረዉምና፥ ከሚናወጠዉ በላይ የሚያናዉጠዉ ሲመጣ፥ ድካም ጠፋ

እህት ወንድሞቼ!፥ አንዴ መብረር የጀመረች ንስር፥ ከምድር እርቃ፥ ከመዘግየት ዞን አልፋ፥ ወደናፈቃት ሰማይ ዘወትር ታንጋጥጣለች፤ እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረዉ፦ “አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን ነዉ” ይላል፥ ስለሆነም እግዚአብሔርን በመተማመን ለሚጠባበቁ፥ ኋይል የሚሆንላቸዉ እርሱ ራሱ ነዉ፤ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ኋይል በሚል ሰጠ፤ ይህም ኋይል፥ እግዚአብሔርን የማወቅና የመምሰል፥ ወደ ፍፁምነትና እርሱን ወደመተረክ የሚያበቃን ኋይል ነዉ፤ ደግሞም የእግዚአብሔር መንፈስ የኋይል መንፈስ ነዉ፥
ዛሬም ይሄ ኋይል ካላችሁበት ነገር፥ በቃ ይበላችሁ!፥ ስትጠብቁት ከነበረዉ በላይ፥ ካስጠበቃችሁ እግዚአብሔር ጋር፥ መገናኘት ይሁንላችሁ!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
730 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 10:13:27
ወንድሜ! ምኩራብ ዉስጥ የእግዚአብሔር ሃሳብ የሚመስል፥ የብዙ ስጋ ለባሽ ሃሳብ ታገኛለህ፥ "ፕሮግራሙ መቼ በተጀመረ" ስትል፥ ቀድሞ በስሙ የተጀመረ፥ ስለ ስሙ ብሎ ክርስቶስን የነጠለ ግርግር፥ ከሚያጉረመርም አጣኝ ትሰማለህ፤ ለምን?

በነብዩ ኤልያስ ዘመን፥ በእስራኤል ብዙ ለምፅ ያለባቸዉ ሰዎች ቢኖሩም፥ ነገር ግን ከሶርያዊዉ ከንዕማን በቀር፥ አንድም የነፃ አልነበረም፤ ደግሞ ከነበሩትም ብዙ መበለቶች መካከል፥ ሰራፕታዋ ዘንድ ሄደ እንጂ፥ ወደቀሩት መፍትሄዉን ይዞ አልሄደም፤ ለምን?

ሁለቱም ደግሞ ከኋለኞች አንደኛ እና፥ ከፊተኞች መጀመሪያ ቢሆኑም፥ በጭራሽ ለእግዚአብሔር ሃሳብ የማይዘገይ ልብ ግን ኖራቸዉ፤ ከፍፁምነት ይበልጥ ቋጠሮ ቢኖራቸዉም፥ የሚጣራ የእምነት አካል ነበራቸዉ፤ ምነኛ በመንፈስ የሚያሰክር ታሪክ ባለቤት እንደነበሩ ተመልከቱ!

በአንድ ወቅት ጌታ ኢየሱስን፥ ከትምህርቱ የተነሳ፥ ሰዎች በዚህ እዉነት ክርስቶስን ለመቃወም፥ ከተማይቱ ተሰርታበት ወደነበረዉ ከፍታ ወሰዱት፤ ነገር ግን ወደ ዋንኛቸዉ፥ ወደ ዉስጣቸዉ፥ ወደ ኑሮአቸዉ፥ ወደ ትልቁ ቦታ የወሰዱት እንዳይመስላችሁ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ትምህርቱን ሊጥሉ ገፉት፤ ኢየሱስን አስወጥቶ ስለ ኢየሱስ የሚመሰክር ትዉልድ፥ ቀጥሎ ያለዉን ክንዉን ከቶ አያዉቅም፤ እንግዲህ ንዕማን የሰማዉን አምኖና አቆራርጦ ሊፈልግ የመጣ ታላቅ ሰዉ መሆኑን አንድ፥ መበለቲቱ ደግሞ በፋንታዋ ታዛ እንደነበር ፈፅሞ ረስተዋል፤ አዎ መፈለግና መታዘዝ ቁልፍ ናቸዉና፥ እርሱም ተገኘላቸዉ።
እንዲህ እያልኳችሁ ነዉ፥ ክርስቶስ እንዳለፈዉ እኛም ከታዘዝን በመካከል እናልፋለን!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ

                    @wisdom3in1

#ተባረኩ!
962 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 11:35:24
“እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤”
— መዝሙር 67፥1

ዉድ ኢትዮጵያን፥ የእግዚአብሔር ሰላም በእኛ ላይ ትሁን፤
እንግዲህ ምን እንላለን!፥ እነሆ የተማርንበት የፊተኛይቱ ርህራሄ እኮ፥ እግዚአብሔር የሰጠን በረከታችን ነዉ ብለን እንተማመንበታለን፤ ምህረትን እንደ ተሰጠዉ በረከቱ የሚቆጥር ማንነት አደገ ማለት፥ መጽሐፍ ቅዱስ፦ "አስቀድማችሁ ጽድቁን ፈልጉ" ካለን ከፍታ ጋር ወስዶ ያገናኘናል፥ ጽድቅ ማለት ምረት እንደሆነም ይገባዋል፤ በመሆኑም ምህረት የተሰጠንም ቀን ፀድቀናል፥ ያም ምህረት ክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ ምሮናል፤ ስለዚህ አስቀድማችሁ፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ፈልጉ፥ እግዚአብሔርም ያበራላችኋል፥ ብለን እንጎተጉታችኋለን።

ስለዚህ መፍትሄዎቿን እስከነቁልፉ የተነጠቀችዉ ምድር፥ ለተሸነፈችለት አንደ ፃድቅ አስረክባለችና፥ ለሚጠይቃት የምትሰጠዉ ስለሌላት፥ ወደ ማሃሪዉ ትጠቁማለች፥ መፍትሄዉ ራሱ ምህረት ነዉና፤ ምህረት ዉስጥ ከስሜታችሁ በላይ መፅናናት፥ ከስሜታችሁ በላይ በረከት ሁሌም በዚያ ይኖራል፤ አዎ! አሁንም ቀና የሚያደርግ የእግዚአብሔር ፊት ከፍላጎታችን በላይ ያስፈልገናል!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
983 viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 15:27:10
“፦ አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።”
— ማርቆስ 10፥49

ከሕይወት እስትንፋስ በፊት ምክንያት በሌለህ ጊዜ፥ ሳትጠራዉ እሱ ግን አጠገብህ ቆሞ ነበር፤ የአይሁድ እምነት አንተን ለመቀበል ያመነታዉን፥ ኢየሱስ ስለፈለገህ ብቻ ሃይማኖትም ጠራህ።

ዙሪያችን ያሉ አጀቦች ሁሉ፥ በክርስቶስ እንጂ፥ ለካስ ከሳሾቻችን ነበሩ፥ ይህንን ከክርስቶስ የተነሳ አዉቀን ባንጨርስም፥ ግን ደግሞ ከፍለን እናዉቃለን፤ ዲንጋዩን ከምህረት ይልቅ፥ ራሳቸዉን ከእግዚአብሔር መንፈስ ይበልጥ፥ አምነዉና አተልቀዉ በተሸከሙት መካከል፥ የማረን ኢየሱስ በግርግር ዉስጥ ስለሰማን አይደለምን?፤
በዚያ ምፅዋት እየለመነ ለነበረዉ ሰዉ፥ ጌታ ትኩረት እንደሰጠዉ ሲያዉቁ፥ መልክተኞች በዙሪያዉ በዙ፥ "ይጠራሃል" አሉት።

ይሄኛዉ ጥሪ፥ የተቀመጠበትን አላማ የሚያሳካ ሳይሆን፥ የክርስቶስ እይታን ወደ አላማ ቀይሮ የሚያስነሳ ነዉ!!!።

ወዳጆቼ ክርስቶስ ኢየሱስ ዛሬም ለእናንተ መልዕክት አለዉ፥ አይዟችሁ! እርሱ እየጠራችሁ ነዉ!፥ ከምትጠብቁት በላይ ያልጠበቃችሁት ክብር፥ በመዳፋችሁ ላይ ተቀምጦ በብዙ ዲንጋዬች መካከል ወደ እናንተ ሕይወት ይመጣል!
አይዟችሁ!፥ አይዟችሁ!፥ አይዟችሁ!፥ እርሱ እየጠራችሁ ነዉ!።

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
1.2K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 19:04:18
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ?”
— ማርቆስ 9፥50

የተወደዳችሁ እህት ወንድሞቻችን ሰላም ለእናንተ ይሁን

ከፍርድ ቀን በላይ የምንኖርባትን እያንዳንዷን ቀን፥ እንደ መጨረሻዉ ቆጥረን፥ በንቃት የምንጠባበቀዉ ጌታ እንዳለን ጭምር፥ ከዚህ ክፉ ዘመን ተነጥለን ገና የምንሰብከዉ የክርስቶስን መገለጥ ይቀረናል፤ በዚህም ደግሞ በምድር ፊት፥ እነሆ የመረረዉን ጣዕም ካለዉ ጋር፥ የወደቀዉን ከተነሳዉ፥ ክህደትን ከእምነት፥ ጥላቻን ከፍቅር፥ ዉድቀትን ከክርስቶስ ትንሳኤ ጋር፥ ዘወትር አስታራቂዎች ነን፤ ስለሆነም የማስታረቅን አገልግሎት በኛ አኑሮ፥ ድል በመንሳት፥ እንደ ጨዉ ተሰርተን ተገለጥን።

ነገር ግን፥ ክርስትና ክርስቶስ ከሌለበት አልጫ ነዉ!፥ ሕይወት ያለበትን መንፈስ ተከትለን፥ ነገር ግን ከበራድና ትኩስ መካከል ካለዉ ክርስትና እንጠነቀቅ ዘንድ፥ አልጫ ከተሰኘዉ እንራቅ፤ ጨዉ...ጨዉ ያስባለዉ ንፅህናንና አለመለወጥን፥ በጊዜ መካከል ሳይቀየር እንደዛዉ ይዞና ጠብቆ መገኘቱ ነዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለዉ "እናንተ የምድር ጨዉ ናችሁ" ይላል፥ ነገር ግን የጣዕማችን ሚስጥር ለሌላዉ ነዉ!፤ ክርስቶስ የሚሰራብን ዉስጣችንን ወደ ጨዉነት በቃሉ በቀየርን መጠን ነዉ፥ ይሄ ማለት ደግሞ ክርስቶስ በዉስጣችን በሚነበብበት ልክ መሆኑ ነዉ።

#ሰማያዊ_ጥበ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
1.2K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 22:14:01 የእግዚአብሔር ዓይኖች



612 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 14:52:44
“ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥17

ዳርቻችን "በክርስቶስ ኢየሱስ መሰወር" በሚል የፀና ግንብ፥ እግዚአብሔር የስልጣኑን ቃል፥ የሁሉ ማሰሪያ አደረገዉ፤ ምክንያቱም ሁሉ ያለዉ በአንዱ፥ አንዱም ያለዉ በሁሉ ዉስጥ ነዉ!፤ ስለዚህ "ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ" ሲል ጳዉሎስ ተናገረ፤ ይህ ማለት፦ "ክርስቶስም በእኔ ዉስጥ ተገልጧል"፥ የሚለዉን ትርጉም ይዞ እንዲነሳ፥ ከዚህ በላይ ሊገልጥ በሚችል መንፈስ አስተማረን፤ እንግዲህ ዋናዉ ጥያቄ እዚህ ጋር ነዉ!፥ እያበረታን ያለዉ ጌታ፥ አጠገባችን ሆኖ ሲዳስሰን፥ ስንቶቻችን ምንስ ያህል ከዝለታችን በላይ ሰምተነዉ ይሆን?፤ እንኪያስ ብርታት ከሚያስፈልገዉ ዝለት ፊት፥ እርሱ መቶ ሲቆም፥ በእኛ ዉስጥ ስለመሆኑ ማስረጃ ለሚፈልጉብን ሁሉ፥ ማረጋገጫ እናሳያለን፤ ደግሞም ለከበቡን ሁሉ መልስ ሆነ ማለትስ አይደል!፤ በነገራችን ላይ ክርስቶስ ስለ እኛ ጠበቃ የሚሆነዉ፥ ከችግራችን ጋር በመከራከር ሳይሆን፥ የእኛን ጉልበት በማፅናትና፥ በማበርታት፥ በክርስቶስ ዉስጥ እንደሸሸገን ገሃድ ለማዉጣት ነዉ፤ ክርስቶስን ለመምሰል ያለን አካሄድ፥ የራሳችንን በመተዉ ያማረ መሰዋት የሚቃኝ ነዉ፥ ይህንን ዉድ መስዋዕት እርሶ ዘንድ ይኖራልን?፥ ግድ የለም እስኪገለጥ ድረስ፥ ክርስቶስ በእናንተ እንዲገኝ በሱ ተሰወሩ!፥ ክርስቶስም በእናንተ ይገለጣል!!!

#ሰማያዊ_ጥበ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
1.3K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 16:14:04
ዛሬስ ወግ ደርሶኝ አንድ ጥሪ በመልክተኞች በኩል ደረሰኝ፥ ጠሪዉን አዉቀዋለሁ፥ ለምን ፈጥኜ እንድመጣለት ግን አልነገረኝም!፥ ታዲያ አባቴ ምን አስቦ ነዉ ያስጠራኝ?

እግዚአብሔር በምህረት ያጠባችሁ ቀን ምን አይነት ለዉጥ በሕይወታችሁ ላይ እንደተመዘገበ፥ በትኩሱ ፍቅር ላሳስባችሁ ቀርቤአለሁ!፥ ምህረት የበዛለት ዳዊት፥ ከመጠራት ወደ ማጥራት፥ የተለወጠበትን ምህረት ላወራችሁ ጓጓሁ!

የሆነ ምርኩዝ የያዘና፥ በበግ ሽታ የተናጠ ሰዉ ስትመለከቱ፥ ደግሞ በኮረብቶች ላይ የሚታገለዉን ብላቴና በመገረም ብታጤኑ፥ እሱ እኮ የመረሳት ዕጣ ገጥሞት፥ ከከፍታ ሊዘለል የነበረዉን ወጣት፥ ከማይታየዉ ደላይ ሜልኮላዊ የአስተያየት ጦርና፥ ከሚታየዉ የሰለጠነ የሳኦል የእጅ ጦር፥ ደጋግሞ ከሁለቱም ተሳተ፥ ሁለቱም ግን አንድ ነበሩ፥ ጠላታችሁ በብዙ መንገድ ሊመጡ ይችላሉ ነገር ግን ሳኦልና ሜልኮል አንደ ነበሩ፤ የሚጨምር ነገር ካለ የሚበልጥ ምህረት እንዳለ ማስረጃዉ ይሄዉ ነዉ!

“በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥”
— መዝሙር 143፥12

በዳዊት አናት ላይ የፈሰሰዉ ዘይት፥ ከሚመጡት አስከፊ ሰዓታት በፊት፥ የተሰጡትን የምህረት ጅረቶቹን የሚያስታዉሱት፥ የእግዚአብሔር አብሮነት እንደሆነ፥ በእርግጥ ጠላትም በደንብ ይረዳዋል፤ ስለምህረት ስትማፀኑ፥ እግዚአብሔር ስለ እናንተ በሌላ ቦታ ጠላትን እየመታ እንደሆነ አስምሩበትና እለፉ፤ ዳዊት እንደመጀመሪያዉ ጥሪ ጎልያድን ለመጣል የሄደ ይመስላችኋልን?
በማጣራት ዉስጥ ጎልያድ ወደቀ፤ ዳዊት በበዛለት ምህረት ታሪኩ እንዲህ ከተነበበ፥ አትጠራጠሩ ከዚህ የሚበልጥ ነገርን ገና በእግዚአብሔር ምህረት ዉስጥ ታያላችሁ!
እንወዳችኋለን!
#ሰማያዊ_ጥበ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!
1.0K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ