Get Mystery Box with random crypto!

“ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥17 ዳርቻችን 'በክርስቶስ ኢየሱስ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥17

ዳርቻችን "በክርስቶስ ኢየሱስ መሰወር" በሚል የፀና ግንብ፥ እግዚአብሔር የስልጣኑን ቃል፥ የሁሉ ማሰሪያ አደረገዉ፤ ምክንያቱም ሁሉ ያለዉ በአንዱ፥ አንዱም ያለዉ በሁሉ ዉስጥ ነዉ!፤ ስለዚህ "ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ" ሲል ጳዉሎስ ተናገረ፤ ይህ ማለት፦ "ክርስቶስም በእኔ ዉስጥ ተገልጧል"፥ የሚለዉን ትርጉም ይዞ እንዲነሳ፥ ከዚህ በላይ ሊገልጥ በሚችል መንፈስ አስተማረን፤ እንግዲህ ዋናዉ ጥያቄ እዚህ ጋር ነዉ!፥ እያበረታን ያለዉ ጌታ፥ አጠገባችን ሆኖ ሲዳስሰን፥ ስንቶቻችን ምንስ ያህል ከዝለታችን በላይ ሰምተነዉ ይሆን?፤ እንኪያስ ብርታት ከሚያስፈልገዉ ዝለት ፊት፥ እርሱ መቶ ሲቆም፥ በእኛ ዉስጥ ስለመሆኑ ማስረጃ ለሚፈልጉብን ሁሉ፥ ማረጋገጫ እናሳያለን፤ ደግሞም ለከበቡን ሁሉ መልስ ሆነ ማለትስ አይደል!፤ በነገራችን ላይ ክርስቶስ ስለ እኛ ጠበቃ የሚሆነዉ፥ ከችግራችን ጋር በመከራከር ሳይሆን፥ የእኛን ጉልበት በማፅናትና፥ በማበርታት፥ በክርስቶስ ዉስጥ እንደሸሸገን ገሃድ ለማዉጣት ነዉ፤ ክርስቶስን ለመምሰል ያለን አካሄድ፥ የራሳችንን በመተዉ ያማረ መሰዋት የሚቃኝ ነዉ፥ ይህንን ዉድ መስዋዕት እርሶ ዘንድ ይኖራልን?፥ ግድ የለም እስኪገለጥ ድረስ፥ ክርስቶስ በእናንተ እንዲገኝ በሱ ተሰወሩ!፥ ክርስቶስም በእናንተ ይገለጣል!!!

#ሰማያዊ_ጥበ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!