Get Mystery Box with random crypto!

“እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤” — መዝሙር 67፥1 ዉድ ኢትዮጵያ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤”
— መዝሙር 67፥1

ዉድ ኢትዮጵያን፥ የእግዚአብሔር ሰላም በእኛ ላይ ትሁን፤
እንግዲህ ምን እንላለን!፥ እነሆ የተማርንበት የፊተኛይቱ ርህራሄ እኮ፥ እግዚአብሔር የሰጠን በረከታችን ነዉ ብለን እንተማመንበታለን፤ ምህረትን እንደ ተሰጠዉ በረከቱ የሚቆጥር ማንነት አደገ ማለት፥ መጽሐፍ ቅዱስ፦ "አስቀድማችሁ ጽድቁን ፈልጉ" ካለን ከፍታ ጋር ወስዶ ያገናኘናል፥ ጽድቅ ማለት ምረት እንደሆነም ይገባዋል፤ በመሆኑም ምህረት የተሰጠንም ቀን ፀድቀናል፥ ያም ምህረት ክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ ምሮናል፤ ስለዚህ አስቀድማችሁ፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ፈልጉ፥ እግዚአብሔርም ያበራላችኋል፥ ብለን እንጎተጉታችኋለን።

ስለዚህ መፍትሄዎቿን እስከነቁልፉ የተነጠቀችዉ ምድር፥ ለተሸነፈችለት አንደ ፃድቅ አስረክባለችና፥ ለሚጠይቃት የምትሰጠዉ ስለሌላት፥ ወደ ማሃሪዉ ትጠቁማለች፥ መፍትሄዉ ራሱ ምህረት ነዉና፤ ምህረት ዉስጥ ከስሜታችሁ በላይ መፅናናት፥ ከስሜታችሁ በላይ በረከት ሁሌም በዚያ ይኖራል፤ አዎ! አሁንም ቀና የሚያደርግ የእግዚአብሔር ፊት ከፍላጎታችን በላይ ያስፈልገናል!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!