Get Mystery Box with random crypto!

“፦ አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።” — ማርቆስ 10፥49 ከሕይወት እስትንፋስ በፊት | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“፦ አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት።”
— ማርቆስ 10፥49

ከሕይወት እስትንፋስ በፊት ምክንያት በሌለህ ጊዜ፥ ሳትጠራዉ እሱ ግን አጠገብህ ቆሞ ነበር፤ የአይሁድ እምነት አንተን ለመቀበል ያመነታዉን፥ ኢየሱስ ስለፈለገህ ብቻ ሃይማኖትም ጠራህ።

ዙሪያችን ያሉ አጀቦች ሁሉ፥ በክርስቶስ እንጂ፥ ለካስ ከሳሾቻችን ነበሩ፥ ይህንን ከክርስቶስ የተነሳ አዉቀን ባንጨርስም፥ ግን ደግሞ ከፍለን እናዉቃለን፤ ዲንጋዩን ከምህረት ይልቅ፥ ራሳቸዉን ከእግዚአብሔር መንፈስ ይበልጥ፥ አምነዉና አተልቀዉ በተሸከሙት መካከል፥ የማረን ኢየሱስ በግርግር ዉስጥ ስለሰማን አይደለምን?፤
በዚያ ምፅዋት እየለመነ ለነበረዉ ሰዉ፥ ጌታ ትኩረት እንደሰጠዉ ሲያዉቁ፥ መልክተኞች በዙሪያዉ በዙ፥ "ይጠራሃል" አሉት።

ይሄኛዉ ጥሪ፥ የተቀመጠበትን አላማ የሚያሳካ ሳይሆን፥ የክርስቶስ እይታን ወደ አላማ ቀይሮ የሚያስነሳ ነዉ!!!።

ወዳጆቼ ክርስቶስ ኢየሱስ ዛሬም ለእናንተ መልዕክት አለዉ፥ አይዟችሁ! እርሱ እየጠራችሁ ነዉ!፥ ከምትጠብቁት በላይ ያልጠበቃችሁት ክብር፥ በመዳፋችሁ ላይ ተቀምጦ በብዙ ዲንጋዬች መካከል ወደ እናንተ ሕይወት ይመጣል!
አይዟችሁ!፥ አይዟችሁ!፥ አይዟችሁ!፥ እርሱ እየጠራችሁ ነዉ!።

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!