Get Mystery Box with random crypto!

“እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።” — ዕብራውያን 7፥22 እዉቀት ወደ አካል ካላመ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።”
— ዕብራውያን 7፥22

እዉቀት ወደ አካል ካላመጣን፥ በእዉቀት ዉስጥ ያለዉ ፍርድ፥ ከኩነኔ በላይ አስገባሪ ይሆንብናል፤ ምን ማለቴ መሰላችሁ!፥ እግዚአብሔርን የምናዉቅበት እዉቀት፥ ወደ ክርስቶስ ካላደረሰን፥ ገና በወደቀዉ መንፈስ እንኖራለን እንደማለት ነዉ፤ ከወደቀዉ ዓለም ይልቅ የወደቀዉ መንፈስ ዉስጥ ያለዉ ክስረት ይበልጣልና፥ ስለዚህ የምናወራለት እዉቀት፥ ዋስ አስፈልጎት ነበር፤ እግዚአብሔር በራሱ እዉቀት ሊሞላን፥ እዉቀት የሚገለጥበትን ቃል ሰጠን፥ "ቃልም ስጋ ሆነ"፤ እንግዲህ ይህ ቃል ነዉ ለሚሻል ኪዳን ዋስ የሆነን!

እነሆ ድነት በዋስ ነዉ፥ ፅድቅ በዋስ ነዉ፥ መንፈሳዊነት በዋስ ነዉ፥ የተቀበልነዉ ሁሉ በዋስ ነዉ፥ ስለሆነም ከእኛ የሆነ አንዳች ሊኖር አልተገባምና፥ እንዲያዉ ዋሳችንን እያመሰገንን በእረፍቱ ዉሃ ዘንድ በሰላም እንኖራለን፤ ይህም የታመነዉና እዉነተኛዉ ዋስ የተባለዉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ!

እንወዶታለን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!