Get Mystery Box with random crypto!

“ብቻ ጽና፥ አይዞህ።” — ኢያሱ 1፥18 የተወደዳችሁ ዉድ ኢትዬጵያዉያን ዛሬ በቆምንበት የ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“ብቻ ጽና፥ አይዞህ።”
— ኢያሱ 1፥18

የተወደዳችሁ ዉድ ኢትዬጵያዉያን

ዛሬ በቆምንበት የዉድቀት ምዕራፍ ላይ ሆነን፥ የተበታተኑ ነገሮቻችንን ለመሰብሰብ እነሆ በፊቱ እንፍገመገማለን፤ የእኛ ሽንፈት ከእግዚአብሔር ብርታት በላይ የገነነ ሲመስለን፥ ደግሞ ራሳችንን እንታዘብና ለጥቂት ብንፅናናም፥ ደግመን ደጋግመን እንደ ሃገር "አትለፈን!" ብለን፥ ጩኋታችንን ሁሉን በሚችል አምላክ ፊት፥ ማቃችንን እናሳየዋለን፤ ይሄ ማለት ልክ ድፍን እስራኤል በሙሴ ሞት አዝኖና ተክዞ፥ ሲያለቅሱ በነበሩበት ምድረበዳ መካከል፥ ወደፊት የሚቀጥሉበትን ወኔ ባጡና፥ ከፍ ባለ ምሬት ባለቀሱ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ግን ወደ ኢያሱ ድንኳን መጽናናት ይዞ መጣ፤ የእስራኤል እንባ የሚታበሰዉ በሙሴ መኖር ሳይሆን እግዚአብሔር በእስራኤል መኖሩን እንደሆነ ኢያሱ ገባዉ፥ ከሃዘናችን በላይ የእግዚአብሔር ስም በእኛ መጠራቱ ዋጋዉ መፅናናት ነዉ፤ ያለቀሳችሁ ሰዎች ልላችሁ የምችለዉ ነገረረ ቢኖር፦ እግዚአብሔር ዛሬ በድንኳናችሁ ገብቶ፥ ሃዘናችሁን እንዳለፈ ዉሃ እንዲሆን ያዘዋል እያልኳችሁ ነዉ!፤ ስብራትን የሚጠግን የእግዚአብሔር ፀጋ በእናንተ ላይ ይሁን!!!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!