Get Mystery Box with random crypto!

“ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤” — ማቴዎስ 6፥13 እነሆ ደስ ከማይል የሰዉኛ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤”
— ማቴዎስ 6፥13

እነሆ ደስ ከማይል የሰዉኛ ምኞት ፍፃሜ ተስቦ፥ ከአባቱ ቤት ደስታ ዘንበል ከሚል ፍጥረት፥ ምህረትን በእሱ ዘንድ እንደ ደሞዝ ቆጥሮ ይወጣል።

የምንፈልገዉ ስጋን ከሆነ፥ በአባታችን ቤት የሚያኖረን መንፈስ በራሳችን አይምሮ የተነሳ እናጣለን ማለት ነዉ፤ ይሄ ደግሞ የሚያመለክተዉ፥ የተጠጋነዉ ፍሰቱን የማያቆም ወንዝ እንደሆነ ማዘናጊያ ነዉ።

እርያዎቹ ስለምግባቸዉ ሲያስቡ፥ ከእነሱ ጋር መብላት የፈለገ እንዳለ ግን አያዉቁም ነበር፥ አገልጋዩ ልጅ ከአባቱ መድረክ ሲወርድ፥ የሳተዉ ቦታ የምኞቱን ግብ እንጂ፥ ባባቱ ቤት የነበረዉን ክብር እንደማይደርስበት ሳይቆጥር፥ ያልነገሰባት ቅናት ከአባቱ ቤት ይበልጥ ስለ ራሱ ኑሮ በላችዉ።

ፈተናዎቻችን ከመሰራታችን ምክንያት ጋር አያይዘን፥ የአባታችንን ቤት የማያስመኙንና የማያስናፍቁን ከሆነ፥ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ፥ ለፈተና ፈተና የሆነዉ እኛ ነን።

የሚነደዉን ጧፍ በክብር ለሚጠብቃት እግዚአብሔር፥ ያጨልማት ዘንድ እርሱን ጨለማ አይመለከተዉም፥ የተቀጠቀጠዉን ሸንበቆ ያሰብር ዘንድ፥ በፍቅሩ እርሱ አይደራደርም፤ ነገር ግን "ከክፉ አድነን እንጂ" እንድንል፥ አዳኝነቱን በመስቀል አስመሰከረ፥ እናም ፈተናችንን እርሱ ተቀበለ፥ ስለዚህ እኛ ተፈታኝ ሳንሆን፥ ፈተናዉን ያለፍን ባለዉጤት ነን።

የተከበራችሁ ወዳጆቼ ክርስቶስ ኢየሱስ ካሰበልን በላይ ልናስብ የበቃን አይደለንም፥ እርሱ ደግም አንዴ አስቦልናል!።

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!