Get Mystery Box with random crypto!

“የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ።” — 2ኛ ጴጥሮስ 3፥15 የሁሉ ፍፃሜ በክር | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ።”
— 2ኛ ጴጥሮስ 3፥15


የሁሉ ፍፃሜ በክርስቶስ ይሆን ዘንድ፥ የተስፋዉን ቃል በእኛ አሳድሮ፥ በመጨረሻም ፀፀት የሌለበትን ዉሳኔ በእኛ የድነት ቁጥር ዉስጥ እንድናረጋግጥ አስቀድሞ ተወስናል፤ ሆኖም ለፍርድ በሚያበቃ አመፅ እና በማስረጃዉ ገፅ መካከል ትዕግስቱን በፍፁምነቱ በኩል እንዲያልፍ በዚህ አብ እጅግ ተደሰተ፤ ለወትሮ ታጋሽነት የሆነዉን መቀበል ነበር፥ ማለትም ለበደል የሚሆን ፍሬን በማፍራት ከሕይወት ዛፍ መካከል የተፈቀደዉ መመለስ ሆኖ ሳለ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ግን ትዕግስቱን ወደ መዳን ድረስ በሩን ከፈተዉ፥ ጌታ እየታገሰ ያለዉ ጥፋተኛ ለማድረግ ሳይሆን እንድን ዘንድ ነዉ፥ ትዕግስት በባህሪዉ ነገሩ ከሆነ በኋላ ያበቃል፥ ወይም በይቅርታ ሲዘጋ ይቀራል፥ እሱን እኛም እናዉቀዋለን ግን የክርስቶስ ከዚህ ይለያል፥ የክርስቶስ መከራ የእኛ ድነት ሆነ፥ ለካስ ሲታገሰኝ ቀን እየጠበቀልኝ ሳይሆን መዳንን እያየልኝ ነበር!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል ሆነ #Share እንዲሁም #like ለማድረግ ቀጥሎ ያለዉን link ይጫኑ

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!