Get Mystery Box with random crypto!

“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
— ኢሳይያስ 40፥31

ወዳጆቼ አንድ ነገር ልበላችሁ!፥ እግዚአብሔርን በመተማመን ለሚጠባበቁ እንዲህ ይሆንላቸዋል፦ ኋይላቸዉን ያድሳሉ፥ ክብራቸዉን፥ ሞገሳቸዉን፥ መንፈሳቸዉን፥ ረሃባቸዉን፥ ፍቅራቸዉን፥ እይታቸዉን ያድሳሉ፤ ስለዚህ መተማመን በሚፈጥረዉ መጠበቅና፥ እርግጠኝነትን በሚያስከትል ሕይወት በቀላሉ ይተካል

የዉሃዉን መናወጥ ሲጠባበቅ የነበረዉ ሰዉ፥ ህመምተኛዉ ያለ ጤነኛዉ ሰዉ፥ ወደ መጥመቂያዉ መግባት አቅቶት፥ ከነዉጡ ሲጎመጅ ታከተ፤ ምክንያቱም ከሚናወጠዉ ጋር ለመገናኘት ኋይል አልነበረዉምና፥ ከሚናወጠዉ በላይ የሚያናዉጠዉ ሲመጣ፥ ድካም ጠፋ

እህት ወንድሞቼ!፥ አንዴ መብረር የጀመረች ንስር፥ ከምድር እርቃ፥ ከመዘግየት ዞን አልፋ፥ ወደናፈቃት ሰማይ ዘወትር ታንጋጥጣለች፤ እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረዉ፦ “አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን ነዉ” ይላል፥ ስለሆነም እግዚአብሔርን በመተማመን ለሚጠባበቁ፥ ኋይል የሚሆንላቸዉ እርሱ ራሱ ነዉ፤ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ኋይል በሚል ሰጠ፤ ይህም ኋይል፥ እግዚአብሔርን የማወቅና የመምሰል፥ ወደ ፍፁምነትና እርሱን ወደመተረክ የሚያበቃን ኋይል ነዉ፤ ደግሞም የእግዚአብሔር መንፈስ የኋይል መንፈስ ነዉ፥
ዛሬም ይሄ ኋይል ካላችሁበት ነገር፥ በቃ ይበላችሁ!፥ ስትጠብቁት ከነበረዉ በላይ፥ ካስጠበቃችሁ እግዚአብሔር ጋር፥ መገናኘት ይሁንላችሁ!

#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ!