Get Mystery Box with random crypto!

የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ truzmulukenyegmila — የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ truzmulukenyegmila — የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍
የሰርጥ አድራሻ: @truzmulukenyegmila
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 378
የሰርጥ መግለጫ

በዚች ሄደት መለስ በበዛበት ዓለም
ዉሸትን ቀበሮ እዉነትን ተናግሮ የሞተ የለም
አምላክ ላስተሳስብ በሰጠን አምሮ
የተጎዳ የለም ዉሸትን ሸሽጎ እዉነትን ተናግሮ።
@እዉነትን ለማወቅ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል
@እዉነትን ለመናገር ደሞ ትልቅ ድፍረት ይጠይቃል
@እዉነትን ለመኖር ደሞ ትልቅ መስዋዕት ያስከፍላል።
@Truzmulukenyegmila
ግጥም ለመላክ
@Mulukenyejmila
✍ሙሉቀን የጀሚላ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-27 22:32:58 ብዕርሽ አይንጠፍ በርቺ
125 viewsRozale , edited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 19:36:48 ልረሳሽ እየጣርኩ ነው
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ ማሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽታሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ...

(በዕውቀቱ ሥዩም)

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ ማሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽታሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ...

(በዕውቀቱ ሥዩም)
185 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 09:29:53 አላምንሽም
===========

አንደበት ሚናገር
መሆን የሚሹትን
አይን የሚመሰክር
አሁን የሆኑትን
መሆኑን እያወቅኩ እንዴት ብዬ ልመን
ከአፍሽ የሚወጡ ሰባሪ ቃላትን :
ምላስ እየገፋ ብሌን ሲለማመጥ
ልሳን እየጮኸ ልብ በሀዘን ሲቀልጥ
ምርምር ሳያሻኝ ኢምንት ሳልጠረጥር
ከፊትሽ እያየው..
ሺ ተወኝ ብትዪ
ሺ ጊዜ ብትዘልፊኝ
ወዴት እሄዳለው...
:
መስማት አለመቻል
መደንቆር እስኪያምረኝ
የኔ እንደማትሆኚ ልሳንሽ አስምሮ
ደጋግሞ ሲነግረኝ
ለዘመን አዝማናት ታግሼ በጄ ያልሁት
ወግድ ከዚ እያሉት እንደሚያፈጥ ነዳይ
ዛሬም ካንቺ ያለሁት
መደበቅ የማይችል ገራገር አይንሽን
ነበር ስላወቅሁት...

ግና እንደው የአፍሽን
የቃልሽን እውነት..
ለሽራፊ ሰዐት ለአፍታ ወይ ለቅጽበት
አይንሽ ላይ ተስሎ ተስማምቶ የማይ ለት
ጻድቁ አባቴን....
ሳትነግሪኝ ነው ምሄድ
ወደማልመጣበት !
156 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 06:27:43 እሳት ወይ አበባ

(ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን)

እሳት ወይ አበባ
ሌት ከዋክብቱ እንደ ፀደይ
አጥለቅልቆን በቀይ አደይ
ሰማዩ ሥጋጃ አጥልቆ
ተሽለምልሞ አንጸባርቆ
ፈክቶ አሸብርቆ ደምቆ
በአዝመራ በአጥቢያ ዐፀድ ሰፍኖ
የዓደይ አዝርዕት ተከሽኖ
በዕንቁጣጣሽ ሰብል ታጥኖ
ኢዮሃ አበባዬ ሆኖ፥
ጨረቃዋ ከቆባዋ፥ ከሽልምልሚት እምቡጧ
ጧ ብላ ከሰንኮፈንዋ፥ ተንዠርግጎ የእንኮይ ቡጧ፥
ድንግል ጽጌ-ረዳ ፈልቃ
ፍልቅልቂት ድምቡል ቦቃ …
ተንሠራፍታ የአበባ ጮርቃ፥
ታድያን ብሌኑ የጠጠረ
ባሕረ-ሃሳቡ የከረረ
የውበት ዓይኑ የታወረ
ልበ-ሕሊናው የሰለለ
አይ፥ አበባ አይደለም አለ፤
አይ፥ እሳት አይደለም አለ፤
ያልታደለ። …
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥ እሳት አደል ብሎ ካደ
እቶን ባይኑ እየነደደ።
ከዋክብቱ እንደ ችቦ
በነበልባል ወርቀ ዘቦ
ከፅንፍ ፅንፍ አውለብልቦ
ደመራው እየተመመ
እየፋመ እየጋመ
ደመና እንደንዳድ ሲነድ
መንጸባርቅ ሰደድ ሲወርድ፥
በራሪ ኮከብ ተኩሶ
በአድማሳት እሳት ለኩሶ…
ይኸ እንደኔና እንዳንቺው፥ የውበት ዓይኑ የሰለለ
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥ እሳት እኮ አይደለም አለ፥
ያልታደለ። …
… ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፤
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም፥ እንዲያው ዝም … ዝም።
አበባ አንሆን ወይ እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መዓት
ዕድሜ አችንን እንዳማጥናት፤ …
እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን፥ እየቃተትን ስናነባ
ሳንፈጠር በሞትንባት
ሳናብብ በረገፍንባት
ሳንጠና ባረጀንባት
አበባ ወይንም እሳት፥ መሆኑን ብቻ አጣንባት።
*****************************************
1966 ዓ.ም.
ብርሀንና ሠላም ማተሚያ ቤት
235 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 06:27:18 የነብር ጅራት ...
።።።።።።።።።።።።

ወድጄሽ ... ወድጄሽ
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
እንደገና ጀመርኩ ፤ 'ሀ' ብየ መውደዴን
ተረት የሚቀይር ፤ ተመልከችው ጉዴን
'' ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ '' ሲል ተረቱ ፣
ኑሬ ኑሬ ኑሬ - እንዳዲስ ተወለድኩ እኔ ያንቺ ገልቱ ፣
እንኳንም ተወለድኩ
እንኳን ሳትኩኝ አቅሌን
እንኳን አፀናሁት .. ላንቺ ያልኩት ቃሌን
እንደ ነብር ጅራት ስምሽን አንቄ
እንደ ርሃብ ስንቅ ፍቅርሽን ደብቄ
ያ'ሽሙር የተረቱን ስንክሳራ ሳልፈራ
እንቅ ፍቅርሽ እንደ ነብረሰ ጭራ
ሙጭጭ ካንች ጋራ
ጥብቅ !!
'ጅልና ወረቀት
የያዘውን አይለቅ '
ብለው ቢሞግቱሽ
አትከራከሪ ሀሰትም የለበት ፣
ወረቀት ልቤ ላይ
ጅል ፍቅርሽ ነውና የተከተበበት ፤!!
እንቅ እኔ ጅሉ ...
እንቅ እኔ ሌጣው እኔ ወረቀቱ ፣
ያዝ ለቀቅ የለም ለፍቅር ሲሞቱ ፤
አሰንቅ !!

#አሌክስ አብርሃም
179 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:18:49 የነብር ጅራት ...
።።።።።።።።።።።።

ወድጄሽ ... ወድጄሽ
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
እንደገና ጀመርኩ ፤ 'ሀ' ብየ መውደዴን
ተረት የሚቀይር ፤ ተመልከችው ጉዴን
'' ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ '' ሲል ተረቱ ፣
ኑሬ ኑሬ ኑሬ - እንዳዲስ ተወለድኩ እኔ ያንቺ ገልቱ ፣
እንኳንም ተወለድኩ
እንኳን ሳትኩኝ አቅሌን
እንኳን አፀናሁት .. ላንቺ ያልኩት ቃሌን
እንደ ነብር ጅራት ስምሽን አንቄ
እንደ ርሃብ ስንቅ ፍቅርሽን ደብቄ
ያ'ሽሙር የተረቱን ስንክሳራ ሳልፈራ
እንቅ ፍቅርሽ እንደ ነብረሰ ጭራ
ሙጭጭ ካንች ጋራ
ጥብቅ !!
'ጅልና ወረቀት
የያዘውን አይለቅ '
ብለው ቢሞግቱሽ
አትከራከሪ ሀሰትም የለበት ፣
ወረቀት ልቤ ላይ
ጅል ፍቅርሽ ነውና የተከተበበት ፤!!
እንቅ እኔ ጅሉ ...
እንቅ እኔ ሌጣው እኔ ወረቀቱ ፣
ያዝ ለቀቅ የለም ለፍቅር ሲሞቱ ፤
አሰንቅ !!

#አሌክስ አብርሃም

@
258 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:11:48 ስለት
በስለት ፀንሰውኝ በስለት ወለዱኝ

በስለት አድጌ በስለት አለውኝ

መጥፊያዬም በስለት እንዳይሆን ሰግቼ

ሌላ ስለት ተሳልኩ ጧፍ ሻማ ገዝቼ።

ይስማዕከ_ወርቁ

ከወንድ ምጥ መፅሐፍ የተወሰደ

@Truzmulukenyegmila
@Truzmulukenyegmila
@Truzmulukenyegmila
153 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:09:49 ልደት በእኛ መንደር

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድን

ሙሉቀን የጀሚላ

@Truzmulukenyegmila
@Truzmulukenyegmila
145 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ