Get Mystery Box with random crypto!

አላምንሽም =========== አንደበት ሚናገር መሆን የሚሹትን አይን የሚመሰክር አሁን የሆኑትን | የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍

አላምንሽም
===========

አንደበት ሚናገር
መሆን የሚሹትን
አይን የሚመሰክር
አሁን የሆኑትን
መሆኑን እያወቅኩ እንዴት ብዬ ልመን
ከአፍሽ የሚወጡ ሰባሪ ቃላትን :
ምላስ እየገፋ ብሌን ሲለማመጥ
ልሳን እየጮኸ ልብ በሀዘን ሲቀልጥ
ምርምር ሳያሻኝ ኢምንት ሳልጠረጥር
ከፊትሽ እያየው..
ሺ ተወኝ ብትዪ
ሺ ጊዜ ብትዘልፊኝ
ወዴት እሄዳለው...
:
መስማት አለመቻል
መደንቆር እስኪያምረኝ
የኔ እንደማትሆኚ ልሳንሽ አስምሮ
ደጋግሞ ሲነግረኝ
ለዘመን አዝማናት ታግሼ በጄ ያልሁት
ወግድ ከዚ እያሉት እንደሚያፈጥ ነዳይ
ዛሬም ካንቺ ያለሁት
መደበቅ የማይችል ገራገር አይንሽን
ነበር ስላወቅሁት...

ግና እንደው የአፍሽን
የቃልሽን እውነት..
ለሽራፊ ሰዐት ለአፍታ ወይ ለቅጽበት
አይንሽ ላይ ተስሎ ተስማምቶ የማይ ለት
ጻድቁ አባቴን....
ሳትነግሪኝ ነው ምሄድ
ወደማልመጣበት !