Get Mystery Box with random crypto!

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ መጋረ | የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ ማሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽታሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ...

(በዕውቀቱ ሥዩም)

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ ማሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤

መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽታሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው፤
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤

ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ...

(በዕውቀቱ ሥዩም)