2022-04-26 21:50:44
ግሩም ጥቅሶች
1.‹‹ አዋቂ ሠው ሁለት ልብ አለው፡፡ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛው ይታገሳል፡፡››
ካህሊል ጂብራን
2."ችሎታህ የማይዋጥላቸዉ ጠላቶችህ በዉሃ ላይ ስትራመድ ቢያዩህ ዋና ስላማይችል ነዉ ይሉሃል።"
ኦሾ
3."ሁሉም ሰው ሞትን ይቀምሳል ህይወትን የሚቀምሰው ግን በጣም ጥቂቱ ነው።"
ሩሚ
4."በዙሪያህ ያለው ሁሉ ጨለማ ከመሰለህ ወደ ቀልብህ ተመለስና እንደገና ተመልከት፤ምናልባት ብርሃን መሆን ያለብህ አንተ ልትሆን ትችላለህ"!!!
ሩሚ
5."አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!"
ኮንፊሽየስ
6.‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን
7."ህይወት የግማሽ እስትንፍስ ያህል አጭር ነች፣ ከፍቅር በቀር ሌላ ነገር አትተከል።"
ሩሚ
8.‹‹ ሐዘንና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው። ሁለቱም አብረው ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከጎንህ ሲሆን አንደኛው መኝታ ቤትህ እንደተጋደመ አትርሳ፡፡»
ካህሊል ጂብራን
9."ደስታ ዱሪዬ አይደለም። ሰዎች ግን እየመሰላቸው በየመጠጥ ቤቱና በጫት ቤቱ ይፈልጉታል።"
ያልታወቀ
10."እውነተኛ ፍቅር እንደ መናፍስት ነው - ሁሉም ሰው ስለእሱ ይናገራል ፣ ግን ያዩት ጥቂቶች ናቸው።"
ሮቼኩዋል
11." ንግግር ከማድረግህ በፊት ንግግርህን በነዚህ ሶስት በሮች ፈትሸህ አሳልፈው...
ትክክል ነው ወይ?
አስፈላጊ ነው ወይ?
በጎ ነገር ነው ወይ? "
ሩሚ
12." ፍቅር ያልነካው እሱ በጨለማ ውስጥ እንደሚጓዝ ፍጡር ነው "
ፕሉቶ
13."በአለም ላይ ከብዙ ሰው ጋር ትገናኛላችሁ ግን በጭራሽ ከራሳችሁ ጋር ተገናኝታችሁ አታውቁም።"
ኦሾ
14.‹‹ ፍቅርና ደግነት የድክመትና የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ሳይሆኑ የጥንካሬና የውሳኔ ሠጪነት መገለጫ ናቸው፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን
15. ‹‹ ፍቅር አልባ ሕይወት አበባ ወይም ፍሬ እንደሌለው ዛፍ ነው፡፡››
ካህሊል ጂብራን
@Truzmulukenyegmila
294 viewsሙሉቀን የጀሚላ 777 @Truzmulukenyegmila, 18:50