Get Mystery Box with random crypto!

ጣፋጭ ውሸት የሚጣረሱ ሀሳቦችን የመያዝ ባህሪ (Cognitive Dissonance) አንድ ቀበሮ | የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍

ጣፋጭ ውሸት
የሚጣረሱ ሀሳቦችን የመያዝ ባህሪ
(Cognitive Dissonance)

አንድ ቀበሮ የወይን ፍሬ ያይና ለመብላት ይቋምጣል። ሙክክ ብሎ የበሰለውን ትልቅ ፍሬ ለማውረድም ተንጠራራ፡፡ የፊት እግሩን የወይን ግንዱ ላይ አስደገፈና አንገቱን ወደ ፍሬዋ አንጠራራ፤ ሊደርስባት ግን አልቻለም፡፡ በዚህ እየተናደደ እንደገና እድሉን ለመሞከር ወሰነ ፤ ራሱን በሚገባ አዘጋጅቶ ወደ ላይ ተወረወረ። አፉ ግን ቀዝቃዛ አየር ብቻ ቀዝፎ ተመለሰ፡፡ ለሶስተኛም ጊዜም ዘሎ ቢሞክር ወደ ኋላ ወደቀና ተፈጠፈጠ፡፡ ፍሬው ይቅርና አንዲት ቅጠል እንኳን ግን አልወደቀችም፡፡ ቀበሮውም አፍንጫውን አዞረና ‹‹ይህ ፍሬ ሲጀምር አልበሰለም፤ ለጎምዛዛ ፍሬ እንዲህ የሚያደርገኝ ምንድን ነው? ብሎ ወደ ጫካው ፈረጠጠ፡፡" -

ግሪካዊው ገጣሚ አይሶፕ የተለመዱ የምክንያታዊነት ስህተቶች ከሆኑት መካከል አንዱን ለማስረዳት ይህንን አፈ ታሪክ ፈጥሮ ነበር፡፡ ይህም የአስተሳሰቦች መጣረስ ነው፡፡ እሱ በፈጠረው በዚህ ታሪክ ውስጥ የቀበሮው የአስተሳሰብ መጣረስ የተፈጠረው ቀበሮውን የሆነ ነገር ለማድረግ ሲፈልግና አልሳካለት ሲለው ነው፡፡ ይህ ታሪክ ከሚከተሉት ሶስት መንገዶች መካከል በአንዱ ውስጥ ማለፉ የግድ ነው፡፡ አንደኛው መንገድ እንደ ምንም ብሎ ፍሬዋን ማውረድ ነው። ሁለተኛው ችሎታው በቂ አለመሆኑን አምኖ መቀበል፣ ሶስተኛው ደግሞ የተፈጠረውን ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ እንደገና በመተርጎም ሃሳብ መቀየር ነው፡፡ #የመጨረሻው አማራጭ የሚጣረሱ አስተሳሰቦችን ችግር የመያዝ የእሱ ነጸብራቅ ምሳሌ ነው። (Cognitive Dissonance)

በቅርቡ የአሸባሪው የህውሀት ቡድን አመራሮች በነፃ መለቀቃቸው ይታወቃል።ይህ በብዙሀኑ ህዝብ ዘንድ ትልቅ መደናገረን ፈጥሯል።መጀመሪያ መንግስት በህውሀት እና እሱን በሚደገፋ ምዕራብውያን ላይ ከፍተኛ ህዝባዊ ዘመቻ ማድረጉ ይታወሳል። በየሚዲያውም ህውሃት ለመስማትና ለማየት የሚቀፉ ግፎችን በንፁሀን ህዝብ ላይ እንደፈፀመ እያሳዩን ነበር። አሁን ደግሞ ጦርነቱ ባልተጠናቀቀበት እና ህውሀት ይበልጥ ለመዋጋት በተዘጋጀበት ጊዜ ለነዚህ ሰዎች ምህረት እና ይቅርታ ማድረግ እንዳለብን ይነግሩናል። እውነታው ግን መንግስት ርህራሄ ወይም ሰብዓዊነት ተሰምቶት ሳይሆን የምዕራባውያን ጫናን መቋቋም ስላልቻለ ይመስለኛል። የከሰረ የዲፕሎማሲ አቋሙ ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል። እናም ይህንንን ችግሩን ሽፋን ለመስጠት ስለ ይቅርባይነት እና ስለ ምህረት ከክርስቶስ በላይ ሊሰብከን ይሞክራል።መንግስት ስህተቱን ማመን አይፈልግም። ከዚህ በተቃራኒው የወሰነው ውሳኔ ብዙ ችግሮችን እያስተናገደም እንኳን ቢሆን ሰላም የሚያመጣ ውሳኔ እንደሆነ ይነግረናል። በየጊዜውም ይህንን ኢ-ምክንያታዊ አቋሙን የሚደግፍለትን ጣፋጭ ውሸት ይፈበርካል።

ገጣሚው እንዲህ ይላል
"የጎበዙን ቀበሮ ጨዋታ የፈለግከውን ያህል መጫወት ትችላለህ፣ በዚህ መንገድ ግን የወይኑን ፍሬ አታገኘውም::"

መነሻ ሀሳብ
(The Art of clearly thinking)
ሮልፍ ዶብሊ

መልካም ምሽት ተመኘዉላቹሁ

@Truzmulukenyegmila