Get Mystery Box with random crypto!

የነብር ጅራት ... ።።።።።።።።።።።። ወድጄሽ ... ወድጄሽ ወድጄሽ ... ወድጄሽ እንደገና | የእዉነት ግጥም። ሙሉቀን የጀሚላ✍✍✍

የነብር ጅራት ...
።።።።።።።።።።።።

ወድጄሽ ... ወድጄሽ
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
እንደገና ጀመርኩ ፤ 'ሀ' ብየ መውደዴን
ተረት የሚቀይር ፤ ተመልከችው ጉዴን
'' ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ '' ሲል ተረቱ ፣
ኑሬ ኑሬ ኑሬ - እንዳዲስ ተወለድኩ እኔ ያንቺ ገልቱ ፣
እንኳንም ተወለድኩ
እንኳን ሳትኩኝ አቅሌን
እንኳን አፀናሁት .. ላንቺ ያልኩት ቃሌን
እንደ ነብር ጅራት ስምሽን አንቄ
እንደ ርሃብ ስንቅ ፍቅርሽን ደብቄ
ያ'ሽሙር የተረቱን ስንክሳራ ሳልፈራ
እንቅ ፍቅርሽ እንደ ነብረሰ ጭራ
ሙጭጭ ካንች ጋራ
ጥብቅ !!
'ጅልና ወረቀት
የያዘውን አይለቅ '
ብለው ቢሞግቱሽ
አትከራከሪ ሀሰትም የለበት ፣
ወረቀት ልቤ ላይ
ጅል ፍቅርሽ ነውና የተከተበበት ፤!!
እንቅ እኔ ጅሉ ...
እንቅ እኔ ሌጣው እኔ ወረቀቱ ፣
ያዝ ለቀቅ የለም ለፍቅር ሲሞቱ ፤
አሰንቅ !!

#አሌክስ አብርሃም

@