Get Mystery Box with random crypto!

ቅድስት ፌብሮኒያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiwetwe — ቅድስት ፌብሮኒያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiwetwe — ቅድስት ፌብሮኒያ
የሰርጥ አድራሻ: @slehiwetwe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ስለ ሕይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፍልበት ነው ፤ እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 04:58:36
አደራ ድንግል አደራ
በፈተና ጊዜ ስጋዬ እንዳይፈራ........
አደራ ድንግል አደራ
አደራ ድንግል አደራ
ሰይጣንን ድል ነስተሽ
አውጭኝ ከመከራ
አደራ ድንግል አደራ.......

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
237 viewsedited  01:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:46:24
ለመጸለይ ትጋት ላለመጸለይ ምክንያት ለሌለኝ ለእኔ ጸልዩልኝ! ━━━━━━━༺✞༻━━━━━━ በዲያቆን ቴዎድሮስ በለጠ [በዕለተ-ልደቱ] ሰው "የማትጸልየው ለምንድነው?" ሲባል ቀዳሚ መልሱ "ጊዜ ስለሌለኝ" የሚለው ነው። በጎውን መንገድ የሚያሳዩት ግን ይህን ይላሉ "የማንጸልየው ጊዜ ስለሌለን ሳይሆን ጊዜው የሌለን ስለማንጸልይ ነው!" ምስጋናው ክቡር ልመናው ሥሙር የሆነለትማ ጸሎቱ ውኩፉ ኃጢዓቱ…
295 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:46:17 ለመጸለይ ትጋት ላለመጸለይ ምክንያት ለሌለኝ ለእኔ ጸልዩልኝ!
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

በዲያቆን ቴዎድሮስ በለጠ [በዕለተ-ልደቱ]

ሰው "የማትጸልየው ለምንድነው?" ሲባል ቀዳሚ መልሱ "ጊዜ ስለሌለኝ" የሚለው ነው። በጎውን መንገድ የሚያሳዩት ግን ይህን ይላሉ "የማንጸልየው ጊዜ ስለሌለን ሳይሆን ጊዜው የሌለን ስለማንጸልይ ነው!"

ምስጋናው ክቡር ልመናው ሥሙር የሆነለትማ ጸሎቱ ውኩፉ ኃጢዓቱ ግዱፍ ጊዜውም ትሩፍ ነው! ከሰዎች ጋር የሚያወራበትን ጊዜ የሚያሳጥር ፡ ከአምላኩ ጋር ለመነጋገር የሚጥር ሰው እንዴት ያለው "ዕድላም" ነው እናንተ! ከንግግሩ የሚቀንስ ከኃጢዓቱ ይቀንልና

☞ ወዘይጸልእ ብዙኃ ነቢበ ያሐጽጻ ለኃጢዓቱ ⇨ አብዝቶ መናገርን የሚጠላ ሰው ኃጢዓቱን ያሳንሳታል【ሲራ ፱፥፮】

የበረሐ አባቶችን ጥበብ የሚነግረን መጽሐፍ እንዲህ ስላለው ንግግር የመቀነስ ዝምታን የማብዛት ሕይወት የሚከተለውን አስተማሪ የቅዱስ አርሳንዮስ ታሪክ ያስቀምጣል።

ቅዱስ አርሳንዮስ ሁል ጊዜ ተሐራሚ ሆኖ በመዓልትና በሌሊት ይጸልይ ነበር:: ሰዎች ሲያነጋግሩት እንኳ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ላለማቋረጥ ጸጥ ይል ነበር:: ለዚህም በኣቱን ከገዳመ አስጤክስ አስር ምዕራፍ ያህል ርቆ ያለ ሲሆን አንድ ቀን አባ መቃርዮስ "ከእኛ ርቀህ የምትኖረው ስለምነው?" ቢለው "ለእኔስ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት መኖር ባይቻለኝ ነው:: የእግዚአብሔር ፈቃድ አንዲት ስትሆን የሰው ፍፈቃዱ ግን ልዩ ልዩ ብዙም ነው"ብሎታል:: ሌሎችም አኃው ሄደው በአርምሞ እንዲህ ጸንቶ ስለመኖሩ ቢጠይቁት "I have often regretted the words I have spoken, but I have never regretted my silence ⇨ በተናገርኳቸው ቃላቶች ብዙ ጊዜ ተጸጽቼ አውቃለሁ፣ በዝምታዬ ግን በፍጹም ተጸጽቼ አላውቅም" አላቸው:: 【+ St. Arsenios the Great 】

ሰው ከሰው ጋር ከመጨዋወት እና አብሮ ከመኖር የራቀ ያህል ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ለመነጋገርና አንድ ለመሆን የበቃ ይሆናልና::

ጌታችንን በምናወድስበት ጸሎትም በልቡናው ንጽሕና ተወዳጅነቱ የተመሰከረለትን አበ ልሳናት ባህረ ጥበባት ቅዱስ ዮሐንስን የሚያነሳ ይህን እጅግ ጠቃሚ ተማጽኖ እናገኛለን ፦

ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዐሞ፣
ንጽሐ ሕሊናሁ ወልቡ ለዓይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ፣
ኢየሱስ ክርስቶስ መፍቀሬ የዋሃት እምተቀይሞ፣
ጸግወኒ ማዕፆ አፍ እንተ ይእቲ አርምሞ፣
ለትዕግሥትከ ከመ አእምር ዐቅሞ።

ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤ ዮሐንስን ለሳመው መለኮታዊ አፍህ ሰላምታ ይገባል። የልቡናው ንጽሕና በፊትህ ተወዳጅነትን አግኝቷልና። ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ቅያሜ በአንተ ዘንድ ቦታ የለውም ቸርነት ግን የባሕርይህ ነው። ስለዚህ የትዕግሥትህን መጠን (ጥቅም) አውቅ ዘንድ። አፌም ክፉ ከመናገር ይቆጠብ ዘንድ የዝምታ ቁልፍ ስጠኝ።【መልክአ ኢየሱስ】

እንግዲህ በጎ ዘመን፡ መልካም ቀን፡ የተሻለ ጊዜ ለማየት አሁን ክፋትን እንቢኝ ተንኮልን ወዲያልኝ ብለን ብዙ እንጸልይ ብዙ ዝም እንበል፤ ባለቅኔው ሎሬት ከቆቃ የላኩትን ምክር እየሰማን እንደው ዝም ብለን እስኪ አብረን ዝም እንበል።

አብረን ዝም እንበል
·
·
·
ከሰው ኳኳታ እንነጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።【ጸጋዬ ገብረመድኅን 1961 ቆቃ。】

✧ "ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤" 【፩ጴጥ· ፫፥፲】

በመጨረሻውም መጨረሻ የምናገረው ነገር ቢኖር አለመናገርን ነው።

"አርምሞሰ ተፍፃሜተ ፍፃሜ ውእቱ" ይላል መጽሐፈ መነኮሳት፤ ይሔን ሁሉ ለመናገር ጊዜ የነበረኝ ለመጸለይ ግን ጊዜ አጠረኝ፤ ለመጸለይ ትጋት ላለመጸለይ ምክንያት ለሌለኝ ለእኔ ጸልዩልኝ! ◆ ክፍለ ሥላሴ

【 የማስታውሰው ፎቶው ገዳመ ቆሮንጦስ ጌታችን የጾመበትና የጸለየበት ታላቁ ሥፍራ የተነሳሁት ነው። ከመታወሻነቱ ባለፈ ወደ ሥዕሉ ዞሮ ለመጸለይ ጊዜ እንዳጠረኝ ከሥዕሉ ዞሮ ፎቶ ለመነሳት ግን በቂ ሠዓት እደነበረኝ አስታውሶኛል 】

————————————————————
በቴዎድሮስ በለጠ ⟟ ከደብረ ብርሃን [ በተወለድኩበት ቀን ነሐሴ ገብርኤል ፳፻፲፬ ዓ.ም ]
————————————————————
339 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:38:24
226 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 04:15:41
በጠላታችን ላይ ኃይልን ለሚሰጠን
በድንቅ ጥበቡ ከሞት ለሚያወጣን
ለልዑል እግዚአብሔር እንዘምራለን
ጠላታችን ይፈር አንወድቅም ፈፅሞ
ወደቁ ስንባል ያነሳናል ደግሞ.....

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
267 views01:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:50:56
ወደ ሰማይ የተወሰደችው ሸማ! /ድንግል ማርያም/ በ ሊ/ሊቃውንት ስሙር አላምራው ቅዱስ ጴጥሮ ከጫማ ሰፊው ስምዖን ቤት በእንግድነት ሳለ ያየው ራእይ ነው፡፡ "ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤ በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ…
330 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:50:47 ወደ ሰማይ የተወሰደችው ሸማ!
/ድንግል ማርያም/


በ ሊ/ሊቃውንት ስሙር አላምራው


ቅዱስ ጴጥሮ ከጫማ ሰፊው ስምዖን ቤት በእንግድነት ሳለ ያየው ራእይ ነው፡፡
"ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤
በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።

ጴጥሮስ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ አንዳች ርኵስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና አለ።
ደግሞም ሁለተኛ፦ እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፥ ወዲያውም ዕቃው ወደ ሰማይ ተወሰደ።" የሐ/ ሥራ 10:11-16፡፡

የራእዩ ትርጉም በጥቂቱ

ይኽን ራእይ ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያ እንዲህ ብሎ ተረጎመው፡፡ "አንቲ ውእቱ መንጦላዕት ስፍሕት እንተ ታስተጋብኦሙ ለመሃይምናን ሕዝበ ክርስቲያን፤ ምእመናን ሕዝበ ክርስቲያንን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ አንች ነሽ"
ሰፊዋ ሸማ/መጋረጃ እመቤታችን ናት፡፡

በአራት ማዕዘን መያዟ፥ 'ርእይ፣ ሰሚዕ፣ አጼንዎ፣ ገሢሥ'በማየት በመስማት በማሽተትና በመዳሰስ ከሚመጣ ኀጢኣት ንጽሕት መኾኗን ያስረዳል፡፡

በውስጧ ያሉት እንስሳት አራዊትና አዕዋፍ ልዩ ልዩ መልክና ጠባይ ያላቸው የሰውን ዘር ይወክላሉ፡፡
'ተነሥተህ አርደህ ብላ' ያለው፥ አሕዛብ አንገታቸውን ለስለት እስኪሰጡ የሚያጸናቸውን ትምህርት አስተምራቸው፤ አጥምቃቸው ሲለው ነው፡፡

ይኽን ሦስት ጊዜ ነግሮት ዕቃው/ሸማው #ወደሰማይ #ተወሰደ፡፡ ሸማዋ ድንግል ማርያም 64 ዓመታትን በምድር ላይ ቆይታ በልጇ ቀኝ ቆማለች፤ ሞታ ተነሥታ ዓርጋለች፤ ዛሬ በመቃብር የለችም፤ ወደእርሷ የመጣው ልጇ ወደ እርሱ ወስዷታል፡፡

የሚያስደንቀው ነገር የሸማዋ ወደሰማይ መወሰድ አይደለም፤ በሸማዋ ውስጥ ያሉት ነፍሳትም በእርሷ በኩል ወደሰማይ መወሰዳቸው እንጂ፡፡ 'ኦ ምዕራግ እምድር ውስተ ሰማይ፤ ከምድር ወደሰማይ መውጫ ' እንዲላት አባ ሕርያቆስ፡፡

በሸማዋ ወላዲተ አምላክነት የሚያምኑ በቃልኪዳኗ የተማጸኑ ኹሉ አንድ ኾነው ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ፡፡ እግዚአብሔር ባከበራትና በመረጣት 'ሸማ'ውስጥ ለሌሉት ሰዎች ያብርህ አዕይንተ ልቦሙ፡፡
ለነሂ ይክፍለነ ነሀሉ ውስተ መንጦላዕት ስፍሕት፡፡
304 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:11:53
"የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገባች"

+.ባስልዮስ ዘቂሳርያ
338 viewsedited  19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:11:53 ቤታቸውን
302 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 06:32:48 ወዳጄ ምንም አይነት የኃጢአት አዘቅት ውስጥ ብትሆን በእግዚአብሔር ሁሉ ይቻልሀል።ተስፋ አትቁረጥ.......

ማርያም ግብፃዊት

ከልጅነቷ ጀምራ ዘማዊት ነበረች።ነገር ግን በኃላ ዘመን ንስሓ ገብታ በገዳመ ዮርዳኖስ በምናኔ ኑሮዋን አሳለፈች።ያች ዘማዊት ሴት የጾም ፣የተጋድሎ ሰው ሆነች።መጀመሪያ ራሷን በኃላም ዲያቢሎስን አሸነፈች።
የቅድስት እናታችን በረከት ይደርብን አሜን።

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
329 views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ