Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ሰማይ የተወሰደችው ሸማ! /ድንግል ማርያም/ | ቅድስት ፌብሮኒያ

ወደ ሰማይ የተወሰደችው ሸማ!
/ድንግል ማርያም/


በ ሊ/ሊቃውንት ስሙር አላምራው


ቅዱስ ጴጥሮ ከጫማ ሰፊው ስምዖን ቤት በእንግድነት ሳለ ያየው ራእይ ነው፡፡
"ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤
በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።

ጴጥሮስ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ አንዳች ርኵስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና አለ።
ደግሞም ሁለተኛ፦ እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፥ ወዲያውም ዕቃው ወደ ሰማይ ተወሰደ።" የሐ/ ሥራ 10:11-16፡፡

የራእዩ ትርጉም በጥቂቱ

ይኽን ራእይ ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያ እንዲህ ብሎ ተረጎመው፡፡ "አንቲ ውእቱ መንጦላዕት ስፍሕት እንተ ታስተጋብኦሙ ለመሃይምናን ሕዝበ ክርስቲያን፤ ምእመናን ሕዝበ ክርስቲያንን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ አንች ነሽ"
ሰፊዋ ሸማ/መጋረጃ እመቤታችን ናት፡፡

በአራት ማዕዘን መያዟ፥ 'ርእይ፣ ሰሚዕ፣ አጼንዎ፣ ገሢሥ'በማየት በመስማት በማሽተትና በመዳሰስ ከሚመጣ ኀጢኣት ንጽሕት መኾኗን ያስረዳል፡፡

በውስጧ ያሉት እንስሳት አራዊትና አዕዋፍ ልዩ ልዩ መልክና ጠባይ ያላቸው የሰውን ዘር ይወክላሉ፡፡
'ተነሥተህ አርደህ ብላ' ያለው፥ አሕዛብ አንገታቸውን ለስለት እስኪሰጡ የሚያጸናቸውን ትምህርት አስተምራቸው፤ አጥምቃቸው ሲለው ነው፡፡

ይኽን ሦስት ጊዜ ነግሮት ዕቃው/ሸማው #ወደሰማይ #ተወሰደ፡፡ ሸማዋ ድንግል ማርያም 64 ዓመታትን በምድር ላይ ቆይታ በልጇ ቀኝ ቆማለች፤ ሞታ ተነሥታ ዓርጋለች፤ ዛሬ በመቃብር የለችም፤ ወደእርሷ የመጣው ልጇ ወደ እርሱ ወስዷታል፡፡

የሚያስደንቀው ነገር የሸማዋ ወደሰማይ መወሰድ አይደለም፤ በሸማዋ ውስጥ ያሉት ነፍሳትም በእርሷ በኩል ወደሰማይ መወሰዳቸው እንጂ፡፡ 'ኦ ምዕራግ እምድር ውስተ ሰማይ፤ ከምድር ወደሰማይ መውጫ ' እንዲላት አባ ሕርያቆስ፡፡

በሸማዋ ወላዲተ አምላክነት የሚያምኑ በቃልኪዳኗ የተማጸኑ ኹሉ አንድ ኾነው ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ፡፡ እግዚአብሔር ባከበራትና በመረጣት 'ሸማ'ውስጥ ለሌሉት ሰዎች ያብርህ አዕይንተ ልቦሙ፡፡
ለነሂ ይክፍለነ ነሀሉ ውስተ መንጦላዕት ስፍሕት፡፡