Get Mystery Box with random crypto!

ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

የቴሌግራም ቻናል አርማ qineenazema — ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official
የቴሌግራም ቻናል አርማ qineenazema — ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official
የሰርጥ አድራሻ: @qineenazema
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 262
የሰርጥ መግለጫ

This is an official channel of QINE ENA ZEMA
PLEAS FOLLOW US
https://fb.com/QineEnaZema
https://www.youtube.com/channel/UCxFBvvBoNVtSyTEQbp4MScQ
Like,follow&subscribe

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-26 08:12:29 ' ብዕር አይጽፈውም
Kaleb Getachew || live worship




@nazrawi_tube
59 views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:52:29
ሁሉም ሰው በህይወቱ የሚያልፍበት አንድ መንገድ አለ፤ እርሱም ድካም ይባላል።
ታድያ በድካም ውስጥ ሆነን የፀሎት ህይወታችን ሲጠወልግ ፤ በቃሉ የገነባነው መንፈሳዊ ብርታት ሲደረመስብን፤ የህይወት ምንጭ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ ርቀን መንፈሳዊ ድርቅ ሲከሰትብን አንድ ድምጽ እናሰማለን
#ዘመናችንን_እንደ_ቀድሞ_አድስ!

@nazrawi_tube
63 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 13:55:29 ' #ወደኋላ_አላይም
መስፍን ማሞ
ከአዲሱ አልበም (#ንገስ አልበም) የተወሰደ ድንቅ ዝማሬ
Full album

@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
114 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 12:36:02
“ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።”
— ዕብራውያን 13፥16
Click here☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
124 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 20:40:45 ስለ ዮሃንስ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን

የዮሃንስ ወንጌል ልክ እንደ ሌሎቹ ሦስት ወንጌሎች ኢየሱስን በአመዛኙ ከታሪክ ጋር አጋብቶ ብቻ ሳይሆን የሚነግረን “አሁን” በአማኝ ወይም በቤተክርስትያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ፋይዳ በጥልቀት በማውሳትም ነው፡ በሌላ አባባል ታሪካዊ / historical ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዋውቀን አሁናዊ / existential ክርስቶስንም ነው።

ዮሃንስ በወንጌሉ ከሚገልጻቸው አሁናዊ እውነቶች መካከል አንደኛው አንድነት / unity ነው፡ ይህንን የአንድነት ክቡር እውነት በዋነኛነት በምእራፍ 17 ላይ አጽንኦት በመስጠት ያቀርብልናል።

ክፍሉ የሚጀምረው፦

“ኢየሱስም . . . ወደ ሰማይ አይኖቹን አነሳና እንዲህ አለ”
ብሎ ነው።

ይሄም የሚያሳየን እውነት በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታችን የሚናገረው ነገር በሙሉ በአብ ፊት እንደ ጸሎት የቀረበ ምልጃ መሆኑን ነው። በዚህ የምልጃ ምእራፍ ውስጥ ነው እንግዲህ ጌታችን በሚገርምና እጅግ ደስ በሚል መልኩ በአብ፣ በወልድና፣ በአማኞች መካከል ያለውን አንድነት ጸሎታዊ በሆነ ቅርጽ ለአባቱ የሚያቀርበው።

#አንድ
የአማኞች የእርስ በርስ አንድነት

ክርስቶስ በዚህ ምእራፍ ቁጥር አሥራ አንድ ላይ እንዲህ ብሎ ይጸልያል፦

“ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው”

መቼም ይህን ቁጥር በጥድፊያ ካላነበብነው በስተቀር ወሳኝ የሆነውን አሳብ የምናልፈው አይመስለኝም፡ ክርስቶስ በዋነኛነት አማኞች እርስ በርስ በአንድ የሰመረ ሕብረት እንዲሆኑ ወይም ብዙዎች ቢሆኑም ነገር ግን አንድ እንዲሆኑ አባቱን ይለምንላቸዋል፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ አማኞች አንድ እንዲሆኑ ለማነጻጸሪያ የተጠቀመበት እውነት ነው፡ እንዲህ ይላል፦

“እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ”

የአንድነቱ ንጽረት አባትና ልጅ ናቸው፡ ታዲያ ይሄ አይገርምም!
በዚሁ ወንጌል ውስጥ ጌታችን “እኔና አብ አንድ ነን - We are in one accord” ብሎ እንደተናገረ እናነባለን፣ ይሄንኑ አንድነት ወይም የአሳብና የልብ ስምረት አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲለማመዱት ይጸልይላቸዋል፡ እውነት ግን እስኪ አስቡት፣ አብና ወልድ አንድ እንደሆኑት እኛ አንድ እንድንሆን እኮ ነው የሚጸልየው፡ በምድር ላይ የአማኞችን አንድነት ለማነጻጸር የሚመጥን አንድ እውነት ያለው በአብና በኢየሱስ መካከል ያለው አንድነት ብቻ ነው፡ ይሄ አንድነት ደግሞ እኛ #የምንጀምረው ሳይሆን #የምንገባበት ነው፣ ምክንያቱም አስቀድሞ በአባትና በኢየሱስ መካከል የተመሰረተ ነው። አንድነታችን የዘር፣ የቋንቋ፣ የአጥቢያ ቤተክርስትያን፣ የጓደኝነት፣ ወይም የቲፎዞ ሳይሆን የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ነው፡ ከዚህ ያነሰ አንድነት በሰው፣ ከሰውና፣ ለሰው የሆነ ነው።

#ሁለት
የአብ፣ የወልድና፣ የአማኞች አንድነት


አማኞች እርስ በርስ ሊኖራቸው ከሚገባቸው አንድነት ወይም ሕብረት በዘለለ መልኩ ጌታችን፣ እርሱ፣ አብና፣ አማኞች ደግሞ በአንድ አንድ እንዲሆኑ ሲጸልይ እናነባለን ቁጥር 21 - 22

“አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ፣ እኔም በአንተ፣ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ . . . እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ . . . “

ደቀመዛሙርት በአብና በወልድ መካከል ባለ አንድነት እርስ በርሳቸው አንድ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን የተጸለየላቸው፣ እነርሱ ራሳቸው ከአብና ከወልድ ጋር በአንድ እንዲሰመሩም ጭምር ነው፡ አብ በወልድ ውስጥ፣ ወልድ ደግሞ በአብ ውስጥ፣ አማኞች ደግሞ በአብም በወልድም ውስጥ ሆነው በአንድ እንዲሆኑ፡ እውነት ከዚህ የሚበልጥ ጸሎት አለ? እውነት ከዚህ የሚበልጥ ክብር ወይም ሕይወት አለ? ከአብና ከወልድ ጋር አንድ መሆን!!

#ማሳረጊያ

የእርስ በርስ አንድነታችን ወይም ሕብረታችን በአብና በወልድ መካከል ባለው ሕብረት መቃኘቱ ሲገባን፣ እንዲሁም አንድነታችን የእርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከአብና ከወልድም ጋር በአንድ መሆኑ ሲገባን፣ ለዚህ ክቡር እውነት ስንል የማንጥለው ነገር አይኖርም፡ ለዚህ ሕብረት ብለን የምንጥለው ነገር ሕብረቱ የገባንን ያህል ነው።

በዚህ አንድነት ውስጥ ያልተሰመረ ሁሉ፣ ፓስተር ይሁን ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ ይሁን ነብይ፣ የሥነ-መለኮት ምሁር ይሁን ዓቃቤ-እምነት፣ ፈጽሞ የመለኮትን ሕይወት አይቋደስም - የመለኮት ሕይወት ከአብና ከወልድ ጋር እንዲሁም እርስ በርስ አንድ በመሆን ብቻ የሚገለጥ ነው።

ምን አይነት ክብር ነው!
ከአብም ከወልድም ጋር በአንድ መሰመር!


“ኅብረታችንም ከአባት ጋር ክልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው”

Yilu danu
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
146 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:44:20 በጥንት አበው ዘመን “አማኝ ነኝ” የሚል ሁሉ በርግጥ የመዳኑና የመለወጡ ምልክት የግል ፍተሻ (self-examination) እንዲያደርግ፣ የሽማግሌውና የተወዳጁን ሐዋርያ ዮሐንስን መልእክት ቱንቢ አድርገው ይጠቀሙበት እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያስረዳል። በዚያ ሚዛን የት ይሆን ያለነው - ማለት በሰው ፊት ሳይሆን በጌታ ፊት? የእግዚአብሔር መንግሥት መዝገብ ሳይውቀን፣ በቤተ ክርስቲያን መኖርና ማገልገልም ይቻላል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነውና! በቤቱ ውስጥ እንክርዳድም አለ። መከር በሚታጨድበትና እውነተኛው ሰብል ከእንክርዳዱ በሚለይበት ዘመን እራሳችንን የት እናገኝ ይሆን? በዚህ ምድር በጌታ ቤት ዘመን ቆጥሮ፣ ምስባኩ ላይ ታይቶና ደምቆ፣ በላይ ግን፣ “ከቶ አላወቅኋችሁም”፣ መባልን ከመሰማት የምናመልጠው አሁን ቀን ሳለ በእግዚአብሔር ፊት በእውነት በመኖር ነው! እስቲ በሐዋርያው ዮሐንስ “የእግዚአብሔርና የዲያቢሎስ ልጆች" ልዪነት መለኪያዎች፣ በግርድፉ ለቅመን ባወጣናቸ 31 መስፍርት እራሳችንን እንይ። ልብ እንበል፣ ዮሐንስ የጻፈው ለአማኞች ነው። “እንግዲህ ልጆች ሆይ፤ እርሱ ሲገለጥ ድፍረት እንዲኖረን፣ በሚመጣበትም ጊዜ በፊቱ እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።” (1 ዮሐ. 2:28)።

1) እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም . . . በጨለማ እየተመላለስን ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል እንዋሻለን፤ እውነትንም አንኖረውም።(1ዮሐ. 1፡5-6)

2) ኀጢአት የለብንም ብንል [በዚህ ምድር በራስችን ፍጹም - perfectionism) ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም (1ዮሐ. 1:8)

3) “እርሱን ዐውቃለሁ” እያለ ትእዛዙን የማይፈጽም ግን ሐሰተኛ ነው፤ እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም (1ዮሐ. 2፡4)

4) ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል። (1ዮሐ. 2:6)

5) በብርሃን አለሁ የሚል፣ ወንድሙን ግን የሚጠላ አሁንም በጨለማ ውስጥ አለ። ነገር ግን ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው (1ዮሐ. 2:9-11)

6) ማንም ዓለምን ቢወድ፣ የአብ ፍቅር በእርሱ ዘንድ የለም፤ (1ዮሐ. 2:15)

7) ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው። (1ዮሐ. 2:23)

8) ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ ታውቃላችሁ። - (1ዮሐ. 2:29)

9) ኀጢአት የሚያደርግ ሁሉ ዐመፅን ያደርጋል፤ ኀጢአትም ዐመፅ ነው . .በእርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም (ሁን ብሎ ልቡ እያወቀ - perpetual, habitual and intentional sinning) ፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም። (1ዮሐ. 3:4-6)

10) ኀጢአትን የሚያደርግ (perpetual, habitual and intentional sinning) ከዲያብሎስ ነው:: ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ [እስከ አሁን] ኀጢአትን የሚያደርግ ነው (1ዮሐ. 3:8)

11) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም። (1ዮሐ. 3:9)

12) የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። (1ዮሐ. 3:10)

13) ፍቅር የሌለው ሁሉ በሞት ይኖራል።ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ። (1ዮሐ. 3:14-15)

14) እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።ማንም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በእርሱ ይኖራል? (1ዮሐ. 3: 16-17)

15) ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።እኛ የእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን (1ዮሐ. 3:18-19)

16) ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን፤ (1ዮሐ. 3:21)
17) ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በእርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን። (1ዮሐ. 3:24)

18) የሚወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማይወድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና (1ዮሐ. 4:7-8)

19) መንፈሱን ስለ ሰጠን፣ እኛ በእርሱ እንደምንኖር እርሱም በእኛ እንደሚኖር እናውቃለን። (1ዮሐ. 4:13)

20) ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። (1ዮሐ. 4:15)

21) በዚህም ዓለም እርሱን እንመስላለንና። (1ዮሐ. 4:17)

22) ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና። (1ዮሐ. 4:20)

23) እግዚአብሔርን ስንወድና ትእዛዛቱን ስንፈጽም የእግዚአብሔርን ልጆች እንደ ምንወድ በዚህ እናውቃለን፤ (1ዮሐ. 5:2)

24) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። (1ዮሐ. 5:4)

25) ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። (1ዮሐ. 5:12)

26) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት እንደማያደርግ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚጠብቀው፣ ክፉውም እንደማይነካው እናውቃለን። (1ዮሐ. 5:19)

27) እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደሆነ እናውቃለን። (1ዮሐ. 5:19)

28) በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው። (2ዮሐ. 1:9)

29) ልጆቼ በእውነት [እንደ ክርስቶስ] የሚመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም። (3ዮሐ. 1:4)

30) ነገር ግን መሪ መሆን የሚወደው ዲዮጥራጢስ [leader in the spirit of anti-Christ) አይቀበለንም። ስለዚህ እኔ ከመጣሁ እርሱ በክፉ ቃላት ስማችንን ለማጥፋት የሚያደርገውን ሁሉ ይፋ አወጣለሁ፤ ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሏቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፤ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል። (3ዮሐ.1:9-10)

31) መልካም የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉ የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም (3ዮሐ. 1:11)
___
Dr. Girma Bekele
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
138 views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 21:48:07 - ስንቶቻችን ለፈተና የተዘጋጀን ነን?-
------- •• --- •• ------
*
- የእኛ ፍላጎት "ወደ ፈተናም ኣታግባን" (ማቴ• 6:13) የምትል መሆን ነበረበት። የእርሱ ትእዛዝ ደግሞ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም" (ማር• 14:38) የሚል ነው።
- ዲያቢሎስ ፈተናውን ሁሉ ሲጨርስ ከእርሱ ለጊዜው ተለይቶት ነበር (ሉቃስ 4:13)። እኛ መጠንቀቅ ያለብን፣ ቀድመን ቃሉን በደስታ ተቀብለን፥ ለጊዜው ያመንን እንጂ በፈተና የምንክድ ሥር የሌለን እንዳንሆን (ሉቃስ 8:13) ነው።
- እርሱ በፈተናዎቹ ጸንተው የኖሩ ደቀ መዛሙርት ነበሩት (ሉቃስ 22:28)። እኛስ በደረሰብን ፈተና ለጌታ እየተገዛን ዘመናችንን ሁሉ ከጌታ ልጆች ጋር እንሆናለን ወይ? (ሐዋ. ሥራ 20:19)።
- እኛ ከሰው ሁሉ ከሚሆነው በላይ ምንም ፈተና አልደረሰብንም፥ እርሱ ከምንችለው መጠን ይልቅ እንፈተን ዘንድ ላለመፍቀድ የታመነ ነው፤ እኛ ለመታገሥ እንችላለን፥ እርሱ መውጫውን ደግሞ ያደርግልናል (፩ኛ ቆሮ• 10:13)።
.
እናም ... ከበፊት/አሁን/ወደፊትም
- እኛ: (ሀ) ባለ ጠጎች ለመሆን ፈልገን፣ በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ (፩ኛ ጢሞ• 6:9)። (ለ) ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስብን እንደ ሙሉ ደስታ እንቊጥረው። ትዕግሥትን የሚያደርግልን የእምነታችን መፈተን ነውና (ያዕ• 1:2-3)! በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነት ኖሮን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና እንዘን። በዚህም እጅግ ደስ ይበለን (፩ኛ ጴጥ• 1:6-7)።
.
የጌታን ፈቃድ አጥርተን እንወቅ!
- "ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። (፪ኛ ጴጥ• 2:9-10)
______
.
ራእይ 3: 10፤ የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
*
---- •• ------ •• -----
- በዓለም ላይ ካለው የፈተና ሰዓት ተጠብቀን ይሆን?

amex tabor
@nazrawi_tube @nazrawi_tube
Share and join
162 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 22:41:25
"ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለመወደዴ ማስረጃው ከእልፍ አእላፋት ምስክሮች በላይ ገዝፎ ቆሟል። መድኅኔ ፍቅሩን ለመግለጥ በመስቀል ላይ በደሙ ቀለም ጽፎ ደብዳቤውን (ክቡር እሱነቱን) በችንካር ላይ ለጥፎታል (1ዮሐ. 3፥16)።
.
ዓለሙን የወደደው ቸሩ እግዚአብሔር የአልማዝ ፈርጥ ሳይኾን ሕይወቱን በልጁ ሰጠን። እኔ ችንካር እርሱ ፍቅር ኾነ። በወጋሁት እጁ አቀፈኝ። ባፈሰስሁት ደሙ ከኀጢአቴ ዐጥቦ አነጻኝ። ያቈሰልሁት ዐመፀኛው ችንካር እኔ ብኾንም፥ በቍስሉ ግን አከመኝ። እናንተንም በፍቅሩ ያክማችኋልና ወደ እርሱ፥ ኑ።"

ከ "የዱባ ጥጋብ፥ ገጽ 410፥ የተወሰደ

@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
161 views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 16:58:27 በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው "አሁን ሰላም ነው" የተሰኘው የዘማሪ ሙሴ አለሙ መዝሙር ተለቋል በዩቱብ እየገባች አድምጣችሁ ተባረኩበት።


742 views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 12:48:45
የዕለቱ ጥቅስ
“ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”
— 2 ዜና 29፥11

@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
183 views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ