Get Mystery Box with random crypto!

'ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለ | ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

"ለመዳናችን የሚያስፈልገው የመድኀኒቱ መጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ያኽላል። ለመወደዴ ማስረጃው ከእልፍ አእላፋት ምስክሮች በላይ ገዝፎ ቆሟል። መድኅኔ ፍቅሩን ለመግለጥ በመስቀል ላይ በደሙ ቀለም ጽፎ ደብዳቤውን (ክቡር እሱነቱን) በችንካር ላይ ለጥፎታል (1ዮሐ. 3፥16)።
.
ዓለሙን የወደደው ቸሩ እግዚአብሔር የአልማዝ ፈርጥ ሳይኾን ሕይወቱን በልጁ ሰጠን። እኔ ችንካር እርሱ ፍቅር ኾነ። በወጋሁት እጁ አቀፈኝ። ባፈሰስሁት ደሙ ከኀጢአቴ ዐጥቦ አነጻኝ። ያቈሰልሁት ዐመፀኛው ችንካር እኔ ብኾንም፥ በቍስሉ ግን አከመኝ። እናንተንም በፍቅሩ ያክማችኋልና ወደ እርሱ፥ ኑ።"

ከ "የዱባ ጥጋብ፥ ገጽ 410፥ የተወሰደ

@nazrawi_tube
@nazrawi_tube