Get Mystery Box with random crypto!

- ስንቶቻችን ለፈተና የተዘጋጀን ነን?- ------- •• --- •• ------ * - | ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

- ስንቶቻችን ለፈተና የተዘጋጀን ነን?-
------- •• --- •• ------
*
- የእኛ ፍላጎት "ወደ ፈተናም ኣታግባን" (ማቴ• 6:13) የምትል መሆን ነበረበት። የእርሱ ትእዛዝ ደግሞ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም" (ማር• 14:38) የሚል ነው።
- ዲያቢሎስ ፈተናውን ሁሉ ሲጨርስ ከእርሱ ለጊዜው ተለይቶት ነበር (ሉቃስ 4:13)። እኛ መጠንቀቅ ያለብን፣ ቀድመን ቃሉን በደስታ ተቀብለን፥ ለጊዜው ያመንን እንጂ በፈተና የምንክድ ሥር የሌለን እንዳንሆን (ሉቃስ 8:13) ነው።
- እርሱ በፈተናዎቹ ጸንተው የኖሩ ደቀ መዛሙርት ነበሩት (ሉቃስ 22:28)። እኛስ በደረሰብን ፈተና ለጌታ እየተገዛን ዘመናችንን ሁሉ ከጌታ ልጆች ጋር እንሆናለን ወይ? (ሐዋ. ሥራ 20:19)።
- እኛ ከሰው ሁሉ ከሚሆነው በላይ ምንም ፈተና አልደረሰብንም፥ እርሱ ከምንችለው መጠን ይልቅ እንፈተን ዘንድ ላለመፍቀድ የታመነ ነው፤ እኛ ለመታገሥ እንችላለን፥ እርሱ መውጫውን ደግሞ ያደርግልናል (፩ኛ ቆሮ• 10:13)።
.
እናም ... ከበፊት/አሁን/ወደፊትም
- እኛ: (ሀ) ባለ ጠጎች ለመሆን ፈልገን፣ በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ (፩ኛ ጢሞ• 6:9)። (ለ) ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስብን እንደ ሙሉ ደስታ እንቊጥረው። ትዕግሥትን የሚያደርግልን የእምነታችን መፈተን ነውና (ያዕ• 1:2-3)! በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነት ኖሮን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና እንዘን። በዚህም እጅግ ደስ ይበለን (፩ኛ ጴጥ• 1:6-7)።
.
የጌታን ፈቃድ አጥርተን እንወቅ!
- "ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። (፪ኛ ጴጥ• 2:9-10)
______
.
ራእይ 3: 10፤ የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
*
---- •• ------ •• -----
- በዓለም ላይ ካለው የፈተና ሰዓት ተጠብቀን ይሆን?

amex tabor
@nazrawi_tube @nazrawi_tube
Share and join