Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxhymanot — የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxhymanot — የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxhymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-30 08:40:34
"…አያችሁ አይደል…?

"…የፈጣሪ ያለህ ውሾች እንኳ ይብለጡን…?
1.0K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 23:00:14 Watch "Ethiopia: ሮፍናን ወጣቱን ሊያስተው ነው የኢትዮጵያ ህዝብ የታሰበልህ ያስፈራል ኮንሰርቱ የተዘጋጀው ለዲያቢሎስ ነው" on YouTube


922 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 08:14:26 2ቱ መነኮሳት

"ሁለት መነኮሳት ወደ ገዳም ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳሉ ከፊታቸው ወንዝ ያጋጥማቸዋል። ያን ወንዝ ለመሻገር ሲሞክሩ ሌላ ጥሩ ልብስ የለበሰች አንዲት ሴት ወንዙ ልብሷን እንዳያበላሽባት ፈርታ ግራ በመጋባት ከዳር ቆማ አዩአት። ከሁለቱ መነኮሳት አንዱም ያቺን ሴት በጀርባው ተሸክሞ አሻገራት። ከዚም መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከሰዓታት በኋላ አንደኛው መነኩሴ "እንዴት ከሴት ልጅ ጋር ያን ያህል ትቀራረባለህ? እንዴትስ እርሷን በመሸከም የምንኩስናን ሕግ የሚቃረን ነገር ታደርጋለህ? እንዴት...?" እያለ ተቃውሞውን ማሰማት ጀመረ። ይሁን እንጂ ያ መነኩሴ ግን ምንም መልስ ሳይሰጠው በዝምታ ይሄድ ነበር። አሁንም ወሳው ቀጥሏል "እንዴት የሴትን ሰውነት ትነካለህ? እንዴት ትሸከማታለህ?" እያለ ደጋግሞ እየተቆጣ ይጠይቀዋል። በስተመጨረሻም ያ መነኩሴ እንዲህ ሲል መለሰለት "እኔ ያቺን ሴት ቅድም ከወንዙ ዳር አውርጃታለሁ። አንተ ግን እስከ አሁን ድረስ ተሸክመሃታል? ለምን አታወርዳትም?"

አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገር ይገጥመናል። ሌሎች ለደቂቃ የሠሩትን ጥሩ ያልሆነ ድርጊት እኛ ቀኑን ሙሉ በማሰብ ውስጣችንን እናረክሳለን። ወንድማችን አንድ ጊዜ የፈጸመውን በደል እኛ ኅሊና ውስጥ ሺህ ጊዜ እየደጋገምን እናየዋለን። ምናልባትም ያ ሰው ያንን የበደል ሸክም ፈጥኖ በንስሐ አራግፎት ይሆናል። እኛ ግን ለዚያ ኃጢአት በልባችን የተሻለ ቦታ በመስጠት ከፍ አድርገን እንሰቅለዋለን። ሠሪው ቶሎ ያወረደውን የኃጢአት ሸክም እኛ ታዛቢዎቹ ግን በኅሊናችን ተሸክመን በየሥፍራው እንዞራለን። ለምን አናወርደውም?
1.0K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 08:09:37 ወጣቱ አንድ አዛውንት አግኝቶ መጠየቅ ጀመረ: "አስታወስከኝ?"

አዛውንቱ "አይ" አለ።

ወጣቱ "ያንተ ተማሪ ነበርኩኝ" አለው።

መምህሩ አዛውንትም "አሁን ከምን ደረስክ?" ሲል ጠየቀው።

ወጣቱም "መምህር ሆንኩኝ" ሲል መለሰለት።

"ዋው! ደስ ይላል። እንደ እኔ?"

"አዎን! በእርግጥ መምህር የሆንኩት አንተን አርዕያ አድርጌ ነው"

አዛውንቱም ወጣቱ መቼ መምህር ለመሆን እንደወሰነ ለማወቅ ስለጓጓ ጠየቀው። ወጣቱም የሚከተለው አጭር ታሪክ ያጫውተው ጀመር።

"አንድ ዕለት ጓደኛዬ አሪፍ ሰዓት ይዞ ትምህርት ቤት መጣ። በጣም ስለወደድኳት መውሰድ ፈለኩኝ እና ከኪሱ ወስድኳት። ብዙም ሳይዘገይ ጓደኛዬ ሰአቱ እንደተወሰደበት ስላወቀ ወዲያው ለመምህር አመለከተ። መምህሩም አንተ ነበርክ።

"እናም አንተ ለክፍሉ ተማሪዎች 'ይሄ ልጅ ዛሬ ሰአቱ ተሰዘርፎበታል። የሰረቃችሁበት በቶሎ መልሱለት' ስትል ተናገርክ። መመለስ ስላልፈለኩኝ ዝም አልኩኝ። እናም ማንም የሚወጣ ሰው ሲጠፋ በሩን ዘጋኸውና ተነስተን ክብ እንድንሰራ አሳሰብከን።

"ሰአቱ እስኪገኝ አንድ በአንድ ኪሳችንን ልትፈትሽ እንደሆነ፣ ነገር ግን ከዛ በፊት አይናችንን መጨፈን እንደሚገባን ነገርከን።

"እንዳዘዝከንም አደረግን።

"ከአንዱ ኪስ ወደሌላው መፈተሽክ ጀመርክ። የኔም ኪስ ስትበረብር ጊዜ ሰአቱን አገኝተኸው ወሰድክ። ዳሩ ግን መፈተሽህን አላቆምክም ነበር። ስትጨርስም 'አይናችንን እንድንከፍት እና ሰአቱም እንደተገኘ' ነገርከን።

"ቢሆንም ግን አልጠቆምክብኝም ወይም አሳልፈህ አልሰጠኸኝም ነበር። ሌባው ማን እንደነበር ፈፅሞ አልተናገርክም። ወይም ወደ ቢሮ ጠርተኸኝም ምክር ቢጤም አልሰጠኸኝም። በዛች ቀን ክብሬን ጠበክልኝ። የሕይወቴ በጣም አሳፋሪ ቀኔም ነበር። ቢሆንም ግን ዕለቱ ሌባ፣ መጥፎ ሰው ላለመሆን ቃል የገባሁበትም ነበር።

"በሚገባ ነበር መልዕክቱን የተረዳሁት። እውነት መምህር ምን ማድረግ እንደሚገባው ገብቶኛል። አመሰግንሃለሁ።

"ይሄንን አጋጣሚ ታስታውሰዋለህ?"

አዛውንቱ መምህርም "እንዴታ አስታውሰዋለሁ እንጂ! የሁላችሁንም ኪስ የፈተሽኩበት እንዴት ይዘነጋኛል? ነገር ግን አንተን አላስታውስህም ምክንያቱም እኔም አይኔን ጨፍኜ ነበር ስፈትሻችሁ የነበረው።

አየህ እንዲህ ነው፤ መምህርነት። ሌላውን እስከጥግ ለመረዳት መሞከር፤ በጭፍንነት ከመፈረጅ መቆጠብ። እንዲህ ነው ረቡኒነት፤ የምታስተምረውን በጥልቀት መረዳት፣ መኖር፣ መውደድ። ስታስተምር በግብዝብነት፣ በእብሪት፣ በመታበይ፣ በችኩልነት አይደለም፤ በትህትና ነው፤ በመተናነስ ነው፤ በትዕግስት ነው በማክበር ነው።

ይሄ ነው፤ የአዛውንቱ መምህር ትልቅነት… ማስተዋል… ጥበብ፤ ሰውኛውነቱ ተፅኖ እንዳያደርግብት ለመጠንቀቅ አይኑን ሸፈነ። ባይሆን ግን ሌባውን ተማሪ ስለእውነት፣ ስለመርህ ሲል አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈትነው፣ ይገፋፋው ነበር።

Big respect ለመምህራን

By Misikir Getachew
717 views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 07:29:19 https://fb.watch/gfdGePZaek/?mibextid=nfde2n

ከትናንት ወዲያ ቅድስት ሥላሴ ያደረጉትን ተዓምር ይመልከቱ
793 viewsedited  04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 17:21:27
770 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 16:58:09 #እኔ ማነኝ
ልመናዬን ያልከለከልከኝ
ጌታ ሆይ በፊትህ እኔ ማነኝ/፪/

ዳዊት የልብህ ሰው እኔ ትል ነኝ ካለህ
ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ጭንጋፍ ነኝ ካለህ
ታዲያ እኔ ማነኝ ጌታ በፊትህ

የቀደሙት አበው ክብራቸውን ጣሉ
ብንኖር ብንሞት ላንተ ነው እያሉ
በፍቅር ተይዘው ቁልቁል ተሰቀሉ

በብዙ ተጋድሎ ክብርህን ወረሱ
እየሞቱ ጠሩህ ስምህን ሳይረሱ
እንደምን አመንከኝ እኔን እንደነሱ

እንዳላሰናክል ሌላውን በከንቱ
ይቀድሰኝ ዛሬ የፀጋህ እሳቱ
ናዝራዊው ኢየሱስ አስበኝ አቤቱ
697 views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 12:44:10 አማርኛ

የሥርዓተዊ ጥቃት ናሙና፡
- ሰሜን ሸዋ ዞን ኦሮሚያ ክልል ከነበሩት 283 አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ 3ቱ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል የመንግሥት መዋቅር ባልፈረሰበት እና አካባቢውን የሚያስተዳደር መንግሥት ባለበት 3ቱ ተቃጥለዋል፣ 83 ሁለገብ ጫና ተደርጎባቸውና በፖለቲካ ዘመቻ ተዘግተዋል፣ 36ቱ ካህናትና ምእመናን እንዲፈልሱ በመደረጉ የሚቀደስባቸው በወር አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በምትካቸው 17 ቃልቻ ቤት፣ 127 ቸርች፣ 209 መስጊድ እና 8 የዋቂፈታ መተኪያዎች በልዩ ድጋፍ እየተጠናከሩ ነው። ይህንን በሸኔ፣ በኦነግ፣ በወጣት አመጽ፣ ወዘተ ማላከክ አይቻለም። ሁሉም የሚሆነው ጠቅላይ ቤተክህነት፣ በሀገር ስብጀትና በወረዳ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በብሔረሰብ ቋንቋ አመካኝተው በሚሠሩና በፖለቲካው ሥረዓት ቅንጅት የሚሠራ ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊያንን የመጥቃት መንግሥታዊ ሥርዓት ውጤት ነው። የእኛን የውስጥ ስንፍና፣ ድሎት ፍለጋ፣ ጎጠኝነት፣ በበዓላት መድመቅና የታይታ አገልገሎት ለጥቃቱ የበለጠ ኃይል ሰጥቶታል።

ኦሮምኛ
Agarsistu Dula Casaa Siyaasaatin Ortodoki irrtii ademsismu :- Godina Oromiyaa Zoonii Kaaba Shewaa keessatti manneen amantaa Orthodoksi 283 keessaa mootummaan Yohinbarbadaa'anii 3 cufameera, 3 gubatanii, 83 dhiibbaa roga hedduu irra ga'uun sababa duula siyaasaatiin cufaman, 36 lubootaa fi amantoota godaanuuf dirqaman, ji’atti al tokko qofa qulqullaa’u. Haa ta’uu malee Manneen Kalchaa 17, manneen amantaa 127, masjiidota 209 fi bakka bu'oota waqifataa 8 deeggarsa addaatiin cimsamaa jira. Kunis Shenee, ABAO, fincila qeerroo fi kkf irratti komatamuu hin danda'u. Wanti ta’u hundi bu’aa sirna mootummaa roga hedduu qabu kan Ortodoksii irratti duuluu haala archdiocese, yaa’ii biyyaalessaa fi caasaa waldaa aanaa keessatti, kan afaan sabaatiin haqa qabeessa ta’ee fi sirna siyaasaatiin qindaa’eedha. Dadhabbiin, araada, ofittummaa, ayyaantummaa fi tajaajila mul’ataa kessaa keenyaa weerara kanaaf humna caalu kenneera.

ኢንግሊዝኛ
A sample of systematic violence against Orthodox Church and the Christians: of the 283 churches in North Shewa Zone, Oromia region, the government system allowed to do so standing by and letting whosoever attack whatever belongs to the Orthodox Christians and 3 churches were burned down, 83 were closed subjected to multi-faceted pressure and political campaign, 36 gets mass service only once a month because the priests are pressurized to leave the area and believers under pressure. Contrary to these 17 Kalcha homes, 127 churches, 209 mosques and 8 waqifata as an Orthodox Christian belief displacement project are being strengthened with special support. This cannot be blamed on Shene, OLF, youth rebellion, etc. Everything that happens is the result of a multi-faceted governmental system of attacking the Orthodox. In additional, the Church’s administrative structure is undermined by organized group and corrupted individuals whose unchristian behavior and actions are justified by ethnic language service improvement movements. The movements are coordinated by the political system and empowered by the laziness, greediness and selfishness of some minsters who hold important offices at different levels within the Church structure
742 views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 16:50:25 ለልጅዎ የግእዝ ስም ማውጣት ከፈለጉ ክፍል ፪

ግእዝ__አማርኛ
፩) መዓርዒር__ጣፋጭ
፪) አሜር__ፀሐይ
፫) አርያም_ሰማይ
፬) አምኃ_እጅ መንሻ
፭) ብሥራት___የምስራች
፮) ሰሎሜ_ሰላም
፯) አሜን__እውነት/ይሁንልኝ
፰) ሠዊት__እሸት
፱) ጸገየ___አበበ
፲) አስካል____ፍሬ
፲፩) ልዑል____ከፍ ያለ
፲፪) ሣህሉ____ይቅርታው
፲፫) ቀጸላ_አክሊል
፲፬) ሐመልማል___የለመለመ
፲፭) ከሃሊ_የሚችል ቻይ
፲፮) ጸዳሉ_መብራቱ
፲፯) ፈትለ ወርቅ____የወርቅ ፈትል
፲፰) ፊደል_ፊደል
፲፱) ማኅተም____ማተሚያ
፳) ሥዩም__የተሾመ ሹም
፳፩) ስብሐት____ምስጋና
፳፪) ስቡሕ_ምስጉን
፳፫) ተቅዋም_መቅረዝ
፳፬) ንጹሕ_የነጻ
፳፭) ሰላማ__ሰላም
፳፮) አዳም__ያማረ
፳፯) ዳግም_የደገመ
፳፰) ግሩም_ተፈሪ
፳፱) ጥዑም____የሚጣፍጥ
፴) ፍጹም__የተቀባ
፴፩) ይኄይስ____ተሻለ
፴፪) ሐዳስ/ሐዲስ___አዲስ
፴፫) ሕዳሴ__መታደስ
፴፬) ሰንኮሪስ_መምህር
፴፭) መቅደስ_ማመስገኛ
፴፮) ሞገስ__ባለሟል የተወደደ
፴፯) ትዕግሥት_መቻል
፴፰) ንጉሥ__የነገሠ
፴፱) ወራሲ__ወራሽ
፵) ውዳሴ__ምስጋና
፵፩) ጌራወርቅ____የወርቅ ሥራ
፵፪) ማኅደር_ማደሪያ
፵፫) ምሕረት_ይቅርታ
፵፬) መሓሪ__ይቅር ባይ
፵፭) ሠምረ__ወደደ
፵፮) ሥሙር_ተወዳጅ
፵፯) ሥምረት____መወደድ
፵፰) ነጸረ__ተመለከተ
፵፱) ምሥጢሩ____ምሥጢሩ
፶) መራሒ____መሪ
፶፩) ፍሥሓ_ደስታ
፶፪) አእመረ____አወቀ
፶፫) አእምሮ____እውቀት
፶፬) ፍቅር__መውደድ
፶፭) ክቡር__የከበረ
፶፮) ደብሩ__ተራራው
፶፯) ተግባር_ሥራ
፶፰) ረቂቅ__ረቂቅ
፶፱) መብረቁ____መብረቁ
፷) ነጸብራቅ__ነጸብራቅ

፷፩) ይባቤ___እልልታ
፷፪) ጥበቡ___ብልሃቱ
፷፫) መሠረት__መሠረት
፷፬) ብሑት___ስልጡን
፷፭) ትሕትና___ትሕትና
፷፮) ተከሥተ__ተገለጠ
፷፯) ሃይማኖት_ሃይማኖት
፷፰) በየነ__ፈረደ
፷፱) መኰንን____ገዢ
፸) በጽሐ__ደረሰ
፸፩) መስፍን____የሚገዛ
፸፪) ምስፍና____ግዛት
፸፫) ክርስቲያን____ክርስቲያን
፸፬) ወሰን__ድንበር
፸፭) መዋዒ_አሸናፊ
፸፮) ትንሣኤ_መነሳት
፸፯) ነቅዐ ሕይወት_የሕይወት ምንጭ
፸፰) ገዛኢ__ገዢ
፸፱) ምሕርካ ክርስቶስ___የክርስቶስ ምርኮ
፹) ባራኪ____ባራክ
፹፩) መልአክ____አለቃ
፹፪) በረከት____በረከት
፹፫) ህላዌ_መኖር
፹፬) ኂሩት_ቸር የሆነች
፹፭) ልባዌ_ማስተዋል
፹፮) ቤዛዊት_ያዳነች የምታድን
፹፯) ስርጋዌ____ሽልማት
፹፰) ስርጉት____የተሸለመች
፹፱) ተስፋ_ተስፋ
፺) ኬንያ__ብልሃተኛ
፺፩) ኖላዊ__ጠባቂ
፺፪) መርዓዊ____ሙሽራ
፺፫) ማዕዶት____መሻገሪያ
፺፬) ወልታ____መከታ/ጋሻ
፺፭) ሐዋዝ____ያማረ
፺፮) ግእዛን____ነጻነት
፺፯) ሕሊና____ሕሊና
፺፰) ማኅሌት____ምስጋና
፺፱) ኅሩይ__ምርጥ
፻) ሲሳይ__ምግብ
፻፩) ሠናይ____ያማረ
፻፪) ፈታሒ____የሚፈርድ
፻፫) ሐሴት____ደስታ
፻፬) ትርሲት_ሽልማት
፻፭) ተዋናዪ_ተጫዋች
፻፮) ዐቢይ___ከፍ ያለ
፻፯) ትውፊት_ስጦታ
፻፰) ኃያል_የበረታ
፻፱) ጽጌ__አበባ
፻፲) ፍሬሕይወት____የሕይወት ፍሬ
፻፲፩) ምዕዳን_ምክር
፻፲፪) ንኡድ___ያማረ
፻፲፫) ነገደ___ሄደ
፻፲፬) ነጎድጓድ____ነጎድጓድ
፻፲፭) ጸዓዳ_ነጭ
፻፲፮) ሠረጸ_በቀለ
፻፲፯) ደምፀ____ተሰማ
፻፲፰) ሮሐ_ወለወለ/አራገበ/አናፈሰ
፻፲፱) ናርዶስ_ሽቱ
፻፳) እፀ ሕይወት___የሕይወት እንጨት
664 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ