Get Mystery Box with random crypto!

#እኔ ማነኝ ልመናዬን ያልከለከልከኝ ጌታ ሆይ በፊትህ እኔ ማነኝ/፪/ ዳዊት የልብህ ሰው እኔ ትል | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

#እኔ ማነኝ
ልመናዬን ያልከለከልከኝ
ጌታ ሆይ በፊትህ እኔ ማነኝ/፪/

ዳዊት የልብህ ሰው እኔ ትል ነኝ ካለህ
ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ጭንጋፍ ነኝ ካለህ
ታዲያ እኔ ማነኝ ጌታ በፊትህ

የቀደሙት አበው ክብራቸውን ጣሉ
ብንኖር ብንሞት ላንተ ነው እያሉ
በፍቅር ተይዘው ቁልቁል ተሰቀሉ

በብዙ ተጋድሎ ክብርህን ወረሱ
እየሞቱ ጠሩህ ስምህን ሳይረሱ
እንደምን አመንከኝ እኔን እንደነሱ

እንዳላሰናክል ሌላውን በከንቱ
ይቀድሰኝ ዛሬ የፀጋህ እሳቱ
ናዝራዊው ኢየሱስ አስበኝ አቤቱ