Get Mystery Box with random crypto!

ወጣቱ አንድ አዛውንት አግኝቶ መጠየቅ ጀመረ: 'አስታወስከኝ?' አዛውንቱ 'አይ' አለ። ወጣቱ ' | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

ወጣቱ አንድ አዛውንት አግኝቶ መጠየቅ ጀመረ: "አስታወስከኝ?"

አዛውንቱ "አይ" አለ።

ወጣቱ "ያንተ ተማሪ ነበርኩኝ" አለው።

መምህሩ አዛውንትም "አሁን ከምን ደረስክ?" ሲል ጠየቀው።

ወጣቱም "መምህር ሆንኩኝ" ሲል መለሰለት።

"ዋው! ደስ ይላል። እንደ እኔ?"

"አዎን! በእርግጥ መምህር የሆንኩት አንተን አርዕያ አድርጌ ነው"

አዛውንቱም ወጣቱ መቼ መምህር ለመሆን እንደወሰነ ለማወቅ ስለጓጓ ጠየቀው። ወጣቱም የሚከተለው አጭር ታሪክ ያጫውተው ጀመር።

"አንድ ዕለት ጓደኛዬ አሪፍ ሰዓት ይዞ ትምህርት ቤት መጣ። በጣም ስለወደድኳት መውሰድ ፈለኩኝ እና ከኪሱ ወስድኳት። ብዙም ሳይዘገይ ጓደኛዬ ሰአቱ እንደተወሰደበት ስላወቀ ወዲያው ለመምህር አመለከተ። መምህሩም አንተ ነበርክ።

"እናም አንተ ለክፍሉ ተማሪዎች 'ይሄ ልጅ ዛሬ ሰአቱ ተሰዘርፎበታል። የሰረቃችሁበት በቶሎ መልሱለት' ስትል ተናገርክ። መመለስ ስላልፈለኩኝ ዝም አልኩኝ። እናም ማንም የሚወጣ ሰው ሲጠፋ በሩን ዘጋኸውና ተነስተን ክብ እንድንሰራ አሳሰብከን።

"ሰአቱ እስኪገኝ አንድ በአንድ ኪሳችንን ልትፈትሽ እንደሆነ፣ ነገር ግን ከዛ በፊት አይናችንን መጨፈን እንደሚገባን ነገርከን።

"እንዳዘዝከንም አደረግን።

"ከአንዱ ኪስ ወደሌላው መፈተሽክ ጀመርክ። የኔም ኪስ ስትበረብር ጊዜ ሰአቱን አገኝተኸው ወሰድክ። ዳሩ ግን መፈተሽህን አላቆምክም ነበር። ስትጨርስም 'አይናችንን እንድንከፍት እና ሰአቱም እንደተገኘ' ነገርከን።

"ቢሆንም ግን አልጠቆምክብኝም ወይም አሳልፈህ አልሰጠኸኝም ነበር። ሌባው ማን እንደነበር ፈፅሞ አልተናገርክም። ወይም ወደ ቢሮ ጠርተኸኝም ምክር ቢጤም አልሰጠኸኝም። በዛች ቀን ክብሬን ጠበክልኝ። የሕይወቴ በጣም አሳፋሪ ቀኔም ነበር። ቢሆንም ግን ዕለቱ ሌባ፣ መጥፎ ሰው ላለመሆን ቃል የገባሁበትም ነበር።

"በሚገባ ነበር መልዕክቱን የተረዳሁት። እውነት መምህር ምን ማድረግ እንደሚገባው ገብቶኛል። አመሰግንሃለሁ።

"ይሄንን አጋጣሚ ታስታውሰዋለህ?"

አዛውንቱ መምህርም "እንዴታ አስታውሰዋለሁ እንጂ! የሁላችሁንም ኪስ የፈተሽኩበት እንዴት ይዘነጋኛል? ነገር ግን አንተን አላስታውስህም ምክንያቱም እኔም አይኔን ጨፍኜ ነበር ስፈትሻችሁ የነበረው።

አየህ እንዲህ ነው፤ መምህርነት። ሌላውን እስከጥግ ለመረዳት መሞከር፤ በጭፍንነት ከመፈረጅ መቆጠብ። እንዲህ ነው ረቡኒነት፤ የምታስተምረውን በጥልቀት መረዳት፣ መኖር፣ መውደድ። ስታስተምር በግብዝብነት፣ በእብሪት፣ በመታበይ፣ በችኩልነት አይደለም፤ በትህትና ነው፤ በመተናነስ ነው፤ በትዕግስት ነው በማክበር ነው።

ይሄ ነው፤ የአዛውንቱ መምህር ትልቅነት… ማስተዋል… ጥበብ፤ ሰውኛውነቱ ተፅኖ እንዳያደርግብት ለመጠንቀቅ አይኑን ሸፈነ። ባይሆን ግን ሌባውን ተማሪ ስለእውነት፣ ስለመርህ ሲል አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈትነው፣ ይገፋፋው ነበር።

Big respect ለመምህራን

By Misikir Getachew