Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxhymanot — የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxhymanot — የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxhymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-04 11:47:54
ይህንን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ ሼር እናድርገው።
https://t.me/onesinod
128 views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 23:40:59 https://vm.tiktok.com/ZMY8XRHp8/
339 views20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 12:40:52
344 views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 10:58:16
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፡፡

ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ-ዛሬ መድኃኒት እርሱም ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋል፤(ሉቃ ፪፡፲፩)

ቃሉን የጻፈልን ቅዱስ ሉቃስ ሲሆን የተናገረው ደግሞ መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እንደሚወለድ ለቅዱሳን ነቢያት በገለጠላቸው ምሥጢር መሠረት ትንቢት ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” (እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች) በማለት ተናግሯል ነቢያት በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝተው የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ምሥጢር አስቀድመው አስተምረዋል (ኢሳ ፯፡፲፬)፡፡ በመሆኑም በተነገረው ትንቢትና በተቆጠረው ሱባኤ መሠረት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተፀነሰው አምላክ ፱ ወር ከ ፭ ቀን ሲፈጸም ጌታ ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና በቤተልሔም ተወለደ፤ (ሉቃ ፩፡፳፯-፴)፡፡
424 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 10:52:19
ትናንት…

"…አስቀድሞ በትንቢት… “…ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 ተብሎ ተናገረን። …በኋለኛው ዘመን የሚወለደውን ጌታ ስሙን ጭምር በምልክት የነገረን። ቀጥሎም ነቢዩ በመንፈስ ቅዱስ መነጽር ዓይቶ እንዲህ አለ። "…ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። ኢሳ 9፣ 6-7።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
343 views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:25:40 join for learning Geez https://t.me/Learning_Geez https://t.me/Learning_Geez https://t.me/Learning_Geez https://t.me/Learning_Geez
1.0K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:16:48 የገና ጾም /ጾመ ነቢያት/
የገና ጾም ጾመ ነቢያት የተባለበት ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡ ነቢያት ጌተችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዚህ ዓለም መጥቶ በሥጋ የታመሙትን በተአምራት፣ በነፍስ የታመሙትን ደግሞ በትምህርት ማዳኑን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ መቀበሉንና መሰቀሉን፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑት እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳ የትንቢቱን ፍጸሜ በዘመናቸው ባያዩትም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡ ነቢያት በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ አባቶቻችንም ይህን መሠረት ባደረገ መልኩ በጾመ ነቢያት ውስጥ ያሉ ጊዜያትን በመከፋፈል ዘመነ ስብከት፣ብርሃን፣ኖላዊ በማለት ትምህርት እንድንማርባቸው አድርገው አዘጋጅተውልናል።
ዘመነ ስብከት
ከነቢያት መካከል እነ ኢሳይያስ የነቢያት ጾም እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል። ኢሳ 58-1፡፡ በዘመነ ሐዲስም ነቢያት አስቀድመው ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት የተናገሩለትንና ሱባዔ የቆጠሩለትን ሐዋርያት ያላቸውን ትተው ተከተሉት ፈቃዱንም ፈጸሙ፡፡ ስለዚህ ምእመናን ክፉ ሐሳባቸውን አርቀው ርኵሰትን አስወግደው ፍጹም ለእግዚአብሔር እንዲገዙ በዚህ የጾም ወቅት በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ይሰጣል፣ ስብከት ይሰበካል። የሚነበበውም ምንባብ ይህንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን የሰበኩበት፣ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበትና የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡
ብርሃን
ክቡር ዳዊት «አቤቱ ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ» /መዝ. 42-3/ እያለ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ከርሱ ወገን እንዲወለድ ትንቢት ስለተናገረ ይህ የሚታሰብበት ነው፡፡ ነቢዩ ዓለም በጨለማ ስለሆነች ብርሃንህን ላክ፣ ሐሰትና የሐሰት አባት ነግሦባታልና እውነትህን ላክ አለ፡፡ ወልድን ላክልን ማለቱ ነው፡፡ ይህንም ቅዱስ ዮሐንስ «ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ» ብሎ ሲመሰክር ጌታም ራሱ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም» ብሎ ተናግሯቸዋል፡፡ ዮሐ. 8-12 እንዲሁም ብርሃንን እውነት ማለቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ ላክልን ሲል ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ስደድልን ማለቱ ነው፡፡
ከጨለማ ወደ ብርሃን አውጣን፣ ማለቱ ደግሞ ንስሐ ከመግባት ቸል እንዳይሉ ይነግራቸዋል፡፡ ነቢያት የጥል ግድግዳን ሰብሮ መለያየትን አጥፍቶ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያወጣቸውን ሽተው ውረድ ተወለድ አድነንም እያሉ ጮኹ፣ እውነተኛ ብርሃን ጌታችን ጊዜው ሲደርስ ወደ ዓለም ወጣ፡፡ በመምጣቱም በጨለማ ያለው በብርሃን እንዲገለጥ ለሰው ልጆች እግዚአብሔርን የሚያውቁባት ዕውቀት ተሰጠች፡፡
ኖላዊ
ኖላዊ ተብሎ የሚጠራው ከብርሃን ቀጥሎ ያለው ሳምንት ነው፡፡ የቃሉ ፍች እረኛ ማለት ነው፡፡ እረኞች ለበጎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውኃ ሳያጓድሉ እንዲጠብቁ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነው፡፡ እረኛ የሌለው በግ ተኩላ ነጣቂ እንዲበረታበት በበደሉ ከትጉኅ እረኛው የተለየው የሰው ልጅም በሲኦል አጋንንት በርትተውበት ሲጠቀጠቅ ኖሯል፡፡ እንዲሁም ከመንጋውና ከእረኛው የተለየ በግ እንዲቅበዘበዝ አምላኩን ዐውቆ አምልኮቱን ከመግለጽ የወጣው ሕዝብ በየተራራው መስገጃዎችን እየሠራ የሚታደገውን አምላክ በመፈለግ ሲንከራተት ኖሯል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ «እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር» እንዳለ፡፡ 1ኛ ጴጥ.2-25፡፡ ነቢያት በዓለም ተበትነው የሚቅበዘበዙትን ሕዝቡን በቤቱ ሰብስቦ የሚጠብቃቸው እውነተኛ ቸር እረኛ እንዲወለድ ስለተናገሩ ያን ለማስታወስ ሳምንቱ ኖላዊ ተባለ፡፡
ነቢያት ይወርዳል፣ ይወለዳል ብለው የተናገሩት ቃል ይፈጸም ዘንድ የሰው ልጆችም ድኅነት ማረጋገጫ እውን ይሆን ዘንድ እንደ ጾሙ እንደ ጸለዩ እኛም እንደ አባቶቻችን እንደ ነቢያት በፍቅር፣ በጾም በጸሎት ዛሬም እናስበዋለን፡፡ ነቢያት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን፡፡ ለዚህም አምላካችን ይርዳን አሜን፡፡
921 views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 23:33:06 https://www.facebook.com/BegenaKirarMesenko/videos/461537672712332/?flite=scwspnss&mibextid=o7d1FKF6OwB1pP9P
956 views20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 22:43:01 Watch "አስደንጋጭ የስልክ ጥሪ ከ666 ቢሮ | አዲስ አበባ ኢሉሚናቲ (666) ቢሮ ደወልን | ጴንጤ ሆኖ የ(666) አባል መሆን ይቻላል @BETESEB TUBE" on YouTube




ጥንቃቄ እናድርግ
1.1K viewsedited  19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 21:28:12 Watch "7 ገዳይ የሆኑ የግቢ ውስጥ ትክሎች" on YouTube


1.0K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ