Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፡፡ ተወልደ ለክሙ ዮ | የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ገፅ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ፡፡

ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ-ዛሬ መድኃኒት እርሱም ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋል፤(ሉቃ ፪፡፲፩)

ቃሉን የጻፈልን ቅዱስ ሉቃስ ሲሆን የተናገረው ደግሞ መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እንደሚወለድ ለቅዱሳን ነቢያት በገለጠላቸው ምሥጢር መሠረት ትንቢት ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” (እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች) በማለት ተናግሯል ነቢያት በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝተው የወልደ እግዚአብሔርን ሰው የመሆን ምሥጢር አስቀድመው አስተምረዋል (ኢሳ ፯፡፲፬)፡፡ በመሆኑም በተነገረው ትንቢትና በተቆጠረው ሱባኤ መሠረት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተፀነሰው አምላክ ፱ ወር ከ ፭ ቀን ሲፈጸም ጌታ ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና በቤተልሔም ተወለደ፤ (ሉቃ ፩፡፳፯-፴)፡፡