Get Mystery Box with random crypto!

The Niles ናይል 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ nileabay — The Niles ናይል 🇪🇹 T
የቴሌግራም ቻናል አርማ nileabay — The Niles ናይል 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @nileabay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.61K
የሰርጥ መግለጫ

news,article ,interview and analysis on nile and international issues .
በአባይ እና ከሃገራችን ጋር ተያያዥ በሆኑ አለምአቀፍ ጉዳዮች ዜና፣ሀተታ ፣ቃለ መጠይቅ እና ትንታኔ ያገኛሉ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-24 16:07:28 ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን ተመቶ መውደቁ ተገለጸ
~~~~
የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያ አየር ክልል ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ኃይል ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ፡፡

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም አንስተዋል።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ የማንንቱ ያልታወቀ አውፕላንም በጀግናው አየር ኃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ኃይሎች ቢኖሩም የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያነ ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ ምህናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል አሁን የመከላከል ርምጃ እየተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የማጥቃት ርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው ጠቁመዋል።
1.5K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:06:43
ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን ተመቶ መውደቁ ተገለጸ
1.4K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 18:36:54
ለተማሪ ቢንያም ኢሳያስ "ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ" እንዲሰጠው ተወሰነ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምክርት ሲከታተል ቆይቶ ትምህርቱን እንዲቋርጥ የተደረገው ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ተጨማሪ ትምህርት ሳይማር ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ ሊሰጠው መወሰኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገለፀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪውን በሚመለከት የወሰነውንውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የጤና ሳይንስ ኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ እንደገለፁት፤ ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ አራተኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ስምንት ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሀሳብ መሰረት ተማሪ ቢንያም ከጤና ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶችን እንዲማር መወሰኑን የጠቆሙት ዶክተር አንዷለም፤ በህክምና ፋርማሲ፣ በህክምና ላብራቶሪ ሳይንስ እንዲሁም በህክምና ላቦራቶሪ በመረጠው ዘርፍ እንዲማርና ባችለር ኦፍ ባዮሜዲካል ሳይንስ እንዲሰጠው መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ዶክተር አንዷለም በገለፃቸው፤ ተማሪው የአካል ጉዳት እያለበት ለህክምና ትምህርት ዘርፍ መመደቡና ለደረሰው ችግር ዋንኛ ምክንያት የህክምና ኮሌጁ ተማሪዎችን ራሱ መመልመል ያለመቻሉ መሆኑን አብራርተዋል።

የህክምና ኮሌጁ እና የትምህርት ክፍሉ አስቀድሞ ማድረግ የሚገባውን ነገር ማድረግ ባለመቻሉ በተማሪ ቢንያም ላይ ለተከሰተው ችግር ሀላፊነት እንወስዳለን ብለዋል፡፡ ( ኢኘድ)
1.2K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:30:28
ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ኩራት መገለጫ ነው !! - የቡርኪናፋሶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቫ ሮምባ
~~~~~~~~~~~

ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከቡርኪናፋሶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኦሊቫ ሮምባ ጋር ተወያይተዋል

በውይይቱ ላይ አቶ ደመቀ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶ ግንኙነት የቆየ ታሪክ ያለው መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነት በአዲስ መልክ ማጠናከር ይገባል ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ቡርኪናፋሶ በባለቡዙ ወገን መድረኮች በኢትዮጵያ ጉዳይ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የምታሳየውን ተከታታይነት ያለው እና ሚዛናዊ አቋም አድንቀዋል ።
የቡርኪናፋሶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቫ ሮምባ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሀገራቸው ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ ትልቅ ቦታ የተሰጣት ሆና ትቀጥላለች ብለዋል ። የኢትዮጵያ አስተዋፅኦ እና ሚና ካለችበት ቀጣና ያለፈ መሆኑን አስረድተዋል ።

በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ግድቡ የአፍሪካ ኩራት መገለጫ እንደሆነ ተናግረዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም የህዳሴ ግድብ የራስን ሀብት ተጠቅሞ እድገት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው ማለታቸው ተገልጿል።
1.4K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:59:49
#ጋና

" የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝ በ30 በመቶ ቀንሷል " - የጋና ፕሬዜዳንት

የጋናው ፕሬዝደንት ናና አዶ ዳንኩዋ አኩፎ-አዶ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የራሳቸውን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎቻቸው ደመወዝ በ30 % እንዲቀንስ መደረጉን አስታውቀዋል።

ይህን ያስታወቁት ትላንትና የዒድ አል-አድሃ በዓል ሲከበር ባሰሙት ንግግር ነው።

የ30% ቅነሳው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን እና መምሪያዎችን ወጪ ይነካልም ተብሏል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መንግስት እያሽቆለቆለ ያለውን ኢኮኖሚ ለመታደግ በሚያደርገው ጥረት ጋናውያን መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ተማጽነዋል።

" አሁን ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሁላችንም መስዋዕትነት መክፈል አለብን " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ መምሪያዎች እና ኤጀንሲዎች ወጪ በ30 በመቶ ቀንሷል። የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝም በ30 በመቶ ቀንሷል " ብለዋል።

የነዳጅ ኩፖን ምደባ በ50 % መቀነሱን እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች መታገዳቸውን ገልፀዋል።

ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ጋናውያን እንዲታገሷቸው አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንት ናና አዶ አኩፎ አዶ እኤአ ሰኔ 1/2022 የገንዘብ ሚኒስትሩ ኬን ኦፎሪ-አታ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር ይፋዊ ግንኙነቶችን እንዲጀምሩ አዘው ነበር።

የIMF ድጋፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠሙ ያሉ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ነው ተብሏል።
ምንጭ - ቲክቫህ
1.5K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:43:13 የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አለመውጣትን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አለመውጣትን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።

እንደሚታወቀው የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው ሳምንት የ20/80 የ14ኛ ዙር የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በ20/80 ፕሮግራም የባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች በእጣው አለመካተትን መነሻ በማድረግ ከአንዳንድ ግለሰቦች የደረሰንን የግልፅነት ጥያቄ አስመልክቶ የሚከተለውን ማብራርያ ለማቅረብ እንወዳለን፡-

በዚህ ዙር ለ20/80 የቤት ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እጣ የወጣባቸውና የተስተናገዱት የ1997 ተመዛጋቢዎች ብቻ ናቸው።

የ2005 የ20/80 ተመዝጋቢዎች ግን ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ በሙሉ በእጣ ውስጥ አልተካተቱም።

የ40/60 የቤት ፕሮግራም ግን በ2005 ዓ.ም ብቁ የሆኑ ሙሉ ለሙሉ በእጣ ተካተው በዚህ ዙር የእጣ አወጣጥ በ40/60 ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ ቤቶች እጣ እንደወጣላቸው ልብ ሊባል ይገባል።

ስለሆነም በዚህ ዙር ያልተስተናገዱት 1997 ዓ.ም የተመዘገቡ ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸው።

ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በ12ኛ ዙር እጣ የ1997 ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ ለሙሉ አስተናግደናል በሚል መነሻ መረጃቸው የተሟላ የሆኑት ተስተናግደው የባለሶስት መኝታ ፕሮግራም ተዘግቶ ነበር።

ከዚህ በኋላ በ1997 ተመዝጋቢዎች ውስጥ በ20/80 ባለሶስት መኝታ እጣ ሊወጣለት የሚችል ተመዝጋቢ የለም በሚል ቤቶቹን በሚያስተዳድረው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።

በዚህም ምክንያት በዚህኛው (በ14ኛ) ዙር እጣ ማስተናገድ አልተቻለም።

ነገር ግን ከተዘጋ በኋላ ከባንክ የተገኘው መረጃ ጥቂቶች ቢሆኑም ቁጠባ በመቀጠላቸው ብቁ የሆኑ ጥቂቶች ተገኝተዋል።

በአሁን ሰአትም ምዝገባው ከባንክ በሚወሰድበት (በሚከለስበት ወቅት) በተገኘው መረጃ ከ1997 ተመዝጋቢዎች መሃከል ጥቂት ሰዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉና ብቁ የሆኑ የ20/80 ተመዝጋቢዎችን ማግኘት ተችሏል።

ስለሆነም አስተዳደሩ እነኚህን ተመዝጋቢዎች ምንም እንኳን ፕሮግራሙ በይፋ የተዘጋ ቢሆንም ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት በአግባቡ እስከቆጠቡ ድረስ ማስተናገድ እንደሚገባ ያምናል።

ነገር ግን ከመረጃ ውስንነትና በሲስተሙ ላይ የሚያስከትለውን ተጨማሪ የመረጃ መመሰቃቀል ለመከላከል ሲባል ወደ በኋላ ተመልሶ ሲስተሙን ለቀሩት ጥቂት ቆጣቢዎች ብቻ መክፈት አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት እነዚህን ተመዝጋቢዎች ለብቻቸው በልዩ ሁኔታ ልናስተናግድ ይገባል የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢ ሆናችሁ ባለሶስት መኝታ ቤቶች በአግባቡ የቆጠባችሁ አስተዳደሩ በሚያወጣው ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ የምትስተናገዱ መሆኑን እያሳወቅን፤ ህብረተሰቡ ይህንን አስመልክቶ አንዳንድ የሚናፈሱ የተሳሳቱ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን!!

በተጨማሪም ዘርፉን የሚመሩ አመራሮች ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ ሚድያዎች የሚያደርሱ መሆኑንም እናሳውቃለን!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም
1.5K views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 23:27:07
በድል ተመለሱ

ብሄራዊ አትሌቲክስ ቡድናችን በክብር ተሸኘ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በአሜሪካ ኦሪገን በሚካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚወዳደረው የአትሌቲክስ ቡድናችን ዛሬ ምሽት አሸኛኘት ተደርጎለታል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኘሬዝደንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች ሃላፊዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ለአትሌቶቹ አበርክተዋል።

18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከጁላይ 15 - 24/2022 ይካሄዳል ።

ድል ለአትሌቲክስ ቡድናችን
1.6K views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:51:49
የሶማሊያው ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሀሙድ አስመራ ገብተዋል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ኘሬዝደንቱ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራው ኘሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጉብኝቱ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
1.6K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:31:31
በምታምኑት ሁሉ ልለምናችሁ ለዚህ ልጅ እንድረስለት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እዩኤል ዳንኤል ይባላል የ9 አመት ልጅ ሲሆን የ3ተኛ ክፍል ተማሪ ነበር ግን እንደእኩዮቹ መማር አልቻለምና በህመሙ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጧል::መቅኔው ደም ማምረት በማቆሙ ምክንያት በህፃን አቅሙ እየተሰቃየ ይገኛል::

ለህክምና የሚያስፈልገው ወጪ 75% ተሰብስቦ 25% ያህል በመጉደሉ በየጊዜው እየደማና ሆስፒታል እየተኛ በልጅ አቅሙ ፈታኝ ስቃይን እየተጋፈጠ ይገኛል::

እርዳታው የሚሰበሰበው በወላጅ አባቱ በአቶ ዳንኤል ዻውሎስ አካውንት ነው::ስለችግሩ ልታናግሩት ከፈለጋችሁ ደውሉለት:: የምትችሉትን እያስገባችሁ ኮመንት ላይ ደረሰኙን እንድታስቀምጡልኝ እማፀናችሁዋለሁ ይህንንም ፖስት መርዳት የሚችሉት ጋ እንዲደርስ ሼር ማድረግም ትልቅ እርዳታ ነው::

Daniel Pawlos
Father of Eyoiel
=======================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000007608482

አዋሽ ባንክ ፡ 01320837549600

ብርሃን ባንክ ፡ 1012244241632

ዳንኤል ጳውሎስ
Daniel Pawlos
Father of Eyoiel
1.7K views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:10:33 አቤ እና አበበ

" ስሜ አቤ ነው ፤ ሆኖም ትምህርት ቤት ሳለሁ ግን ሁሉም የሚጠሩኝ አበበ እያሉ ነበር " ሺንዞ አቤ
~~~~

በሰላም ሙሉጌታ

በአሳዛኝ ሁኔታ ዛሬ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በመሪነት ዘመናቸው ከጎበኟቸው አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች።

አቤ ከስምንት አመት በ 2014 (እኤአ) በፊት ወደ ሃገራችን በመምጣት ጉብኝታቸውን የጀመሩት ገና በጨቅላ እድሜያቸው ታላቅ መገረምን የፈጠረባቸው ጥቁሩን አፍሪካዊ ፈርጥ የአበበ ቢቂላን ቤተሰቦች እና የኢትዮጵያን ብርቅዬ አትሌቶች በማግኘት ነበር።

በብሄራዊ ቤተመንግስት በነበረው ዝግጅት ላይ ለሺንዞ አቤ የአበበ ቢቂላ ፎቶ በአትሌቱ ልጅ የትናየት አበበ ቢቂላ በስጦታ ተበርክቶላቸው ነበር። ስጦታው ለያኔው ጠቅላይ ሚኒስቴር ልዩ ስሜትን ፈጥሮባቸዋል ፤ ሃምሳ አመታትን ወደ ኋላ ተጉዘው በዘመናት ውስጥ ሳይደበዝዝ ሁሌም ስለሚያስታውሱት አስደናቂው ክስተት ተናገሩ።

አበበ ቢቂላ ገናናውን የኦሎምፒክ ገድል እ.አ.አ በ1964 በቶኪዮ ሲፈፅም ሺንዞ አቤ የ10 አመት ህፃን ነበሩ። እድሜያቸው ምንም እንዃን ትንሽ ይሁን እንጂ በአይናቸው የተመለከቱት የጥቁሩ አትሌት ድል ትልቅ ነበር እና እጅጉን አስደንቋቸው እንደነበር በስነስርአቱ ላይ መስክረዋል።

" በማራቶኑ ተሳታፊ የነበሩ የጃፓን ሯጮች ውድድሩን እንዳጠናቀቁ ሁሉም ራሳቸውን እየሳቱ ይወድቁ ነበር፤ ሆኖም አበበ ቢቂላ ግን ውድድሩን ጨርሶ ሰውነቱን ለማቀዝቀዝ እንቅስቃሴ ማድረጉን ስመለከት ተገረምኩ " በማለት በ10 አመት እድሜያቸው ያዩትን አሰደናቂ ትዝታ ለታዳሚ አካፍለዋል።

" አበበ " ለጃፓናውያን ገናና ስም ነው። ገድሉ ሁሌም የሚዘከር ፣ አብዝተው የሚያከብሩት ፣ ልዩ የታሪካቸው አካል ነው። አበበ እንደ በጃፓናውያን ዘንድ እንደ ሃገርኛ ስሞች ሰፊ እውቅና አለው።

ሺንዞ አቤ በአዲስ አበባው ስነ ስርአት ላይ የስማቸውን ነገር አንስተው ታዳሚውን ፈገግ አሰኝተው ነበር ፤ እንዲህ አሉ " እኔ ስሜ አቤ ነው ፤ ሆኖም ትምህርት ቤት ሳለሁ ግን ሁሉም የሚጠሩኝ አበበ እያሉ ነበር "

ጃፓናውያን አቤን ' አበበ 'ሲሉ እኛ ደግሞ አበበን ስናቆላምጥ ' አቤ ' ማለታችንን ያውቁ ነበር ግን ??
ለማንኛውም አበበም አቤም ቢያልፉም ስራቸው ስማቸውን ከፍ አድርጎታል እና ታሪክ ያወሳቸዋል !!

በቴሌግራም መረጃ ያግኙ

https://t.me/nileabay
1.5K viewsedited  20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ