Get Mystery Box with random crypto!

The Niles ናይል 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ nileabay — The Niles ናይል 🇪🇹 T
የቴሌግራም ቻናል አርማ nileabay — The Niles ናይል 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @nileabay
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.61K
የሰርጥ መግለጫ

news,article ,interview and analysis on nile and international issues .
በአባይ እና ከሃገራችን ጋር ተያያዥ በሆኑ አለምአቀፍ ጉዳዮች ዜና፣ሀተታ ፣ቃለ መጠይቅ እና ትንታኔ ያገኛሉ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 18:24:52
አፋልጉን
~~~~~~~~
ወንድማችን ዳዊት ወልዴ እሁድ ነሀሴ 22 ቀን 2014 ዓም ከረፋዱ 5:00 ከቤት እንደ ወጣ አልተመለሰም።
ደዊትን ያያችሁ ወገኖች ትጠቁሙን ዘንድ እንማፀናለን !

በተከታዮቹ ቁጥሮች ጠቁሙን


0911719825
0921324626
እህቶቹ
1.4K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:23:54
ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ
1.7K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:47:50
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
**************

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል።

ነሃሴ 21 ቀን 2014 ዓም
አዲስ አበባ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
1.7K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:45:54
በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ ናይሮቢ ከተጓዘ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የልዑክ ቡድን አባላት ውይይት አደረጉ ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በውይይቱም  አምባሳደር ባጫ ሚሲዮኑ በኢኮኖሚና ቢዝናስ ዲፕሎማሲ ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ዋና ዋና ተግባራት ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል። በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ይቻል ዘንድ እንደአዲስ አባባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ካሉ የአገራችን ተቋማት ጋር በቅንጅት እና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በኬንያ የሚገኙ ታዋቂ ባለሀብቶች ወደ አገራችን ገብተው መዋዕለ-ነዋያቸውን እንዲያፈሱ እና የአገራችን የወጪ ምርቶችን በኬንያ ገባያ የተሻለ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የልምድ ልውውጡ የሚኖረውን አስተዋጽኦ የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ የንግድ ማህበሩ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሳካ ሚሲዮኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል። 

የአዲስ አበባ ንግድንና ዘርፍ ማህበራት የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ማሞ በበኩላቸው  በቀጣይ ሀገራችን ከኬንያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ሚሰሩ ስራዎች የንግድ ማህበሩ ተገቢ መረጃዎችን በመለዋወጥና ከሚሲዮኑ ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።  

የልኡካን ቡድኑ ከነሃሴ 17- 20 ቀን 2014 ዓ.ም በኬንያ በሚኖረው ቆይታ እያደረገ ከሚገኘው የልምድ ልውውጥና ስልጠና ጎን ለጎን በኬንያ የሚገኙ ታዋቂ የንግድ ማህበራትን እና ባለሃብቶችን አግኝተው ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
1.8K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:41:16
የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ተወስኗል
~~~~~~~~~~~~

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ያስታውቃል፡፡
1.4K views04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:21:44
ህወሃት በዓለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘን የፈጸመውን ዝርፊያ የሚወገዝ እና አስነዋሪ ተግባር ነው - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጊኔ ተርክሂን
~~~~~~~~~~~~

ህወሃት በዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የነበረ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ አስነዋሪና ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ተናገሩ።

በመቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የነበረ 12 ታንከር ወይም 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ በህወሃት መዘረፉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ መግለጻቸው ይታወቃል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ህወሃት የዘረፈውን ነዳጅ በአፋጣኝ እንዲመልስ የጠየቁ ሲሆን፤ በነዳጁ መዘረፍ ምክንያት የሰብዓዊ ርዳታዎችን ለማሳለጥ እንቸገራለን ብለዋል።

በዚህ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን፤ በመጋዘኑ ውስጥ የነበረው የምግብና የነዳጅ ክምችት በአስችጋሪ ሁኔታ ለነበሩ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል እንደነበር ጠቅሰዋል።

በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግር ሰለባ ለሆኑ የትግራይ ማህበረሰብ መድረስ የነበረበት እርዳታ በሽብር ቡድኑ መዘረፉ ተቀባይነት የሌለውና አስነዋሪ ተግባር ነው ብለዋል።

ዘራፊዎቹ ነውረኛ ድረጊታቸውን ክደው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የትግራይ ህዝብ ለችግር ተዳርጓል የሚል የተለመደ ልፈፋቸውን እንደሚቀጥሉና የህዝብ ተቆርቋሪ ለመምሰል እንደሚሞክሩም ነው የገለጹት።

በህወሃት የሽብር ቡድን የተፈጸመውን ዝርፊያ የትኛውም የዓለም ማህበረሰብ የማይደግፈው ድርጊት ነው ብለዋል።

የተፈጸመውን ድርጊት ማውገዝ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ አንዳንድ ድርጊቱን በዝምታ የሚያልፉ አካላትም እውነታው በገሃድ መውጣቱ እንደማይቀር ማወቅ አለባቸው ነው ያሉት።
1.4K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:39:03
ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አደረጉ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶችን በስፋት አብራርተዋል።

በገለጻቸውም በመንግሥት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲባል የተደረገውን የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ እና ያልተገደብ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት የተደረጉ ጥረቶችን አብራርተዋል።

አቶ ደመቀ መንግስት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሰላም አማራጭ ዐብይ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ መግባቱንም አስታውሰዋል።

መንግስት የሥስተኛ ወገን ስምምነት በተመድ ጽ/ቤት በመፈረም እንዲሁም ከዓለም ባንክ በተገኝ ድጋፍ የአድጋ ጊዜ እና የማገገሚያ ፕሮጀክት በትግራይ ክልል ተግባራዊ እንዲደረግ መስማማቱን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የህወሓት ቡድን መንግስት የወሰዳቸውን የሰላም አማራጮች ወደ ጎን በመተው ጦርነት መክፈቱን እና የሚደርሰውን እርዳታም ለጦርነት እያዋለው መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ ቡድን በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ የተጀመረውን የሰላም ጥረት በመግፋት ወደ ጦርነት መግባቱን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ይህን ድርጊት በጽኑ እንዲያወግዝ እንዲሁም ቡድኑ ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

መንግሥት በንጹኃን ዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እና ጥፋት እንዳይደርስ ቅድሚያ በመስጠት አሁንም ለሰላም አራጭ ዝግጁ ነው ያሉት ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የአገሪቱን ሉዓላዊ የግዛት አንድነት እና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
1.5K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:33:51
ስለ ጦርነት ወቅት መረጃ አሰጣጥ

በመኩሪያ መካሻ ~ ከአአዩ

1. በጦርነት ወቅት የመረጃ አሰጣጥ ጥብቅ ቁጥጥርን ይሻል።ወታደራዊ የግንባር መረጃዎች ይፋ መደረግ ያለባቸው በመከላከያ ቃል አቀባይ ብቻ ነው።
2.ሀገራዊ አጠቃላይ መረጃዎች በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ብቻ ይሰጡ።ከዚህ በፊት እንደታየው የወረዳ ኮሙኒኬሽንና የከተማ ሹም የሚሰጠው መግለጫ መኖር የለበትም።
3. ሀገር አቀፍ የዘማች ጋዜጠኞችን ቡድን በማደራጀት የዕዝ ጠገጉን የጠበቀ መረጃ ማሰራጨት።ጋዜጠኞቹ ከመከላከያ ጋር ተዳብለው(embedded) እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
4.በየሚዲያው የወታደራዊና ደህንነት ጉዳዩችን የሚከታተል የአርታኢያን ቡድን መሰየም።
5.በመንግስት ኮሙኒኬሽን በኩል ሀቅ አጣሪ፣የስነልቡና ጦርነቱን የሚመራ( ግብረ ሃይል(Ninja) በማቋቋም ሃሰተኛ ወሬዎችን፣የተዛቡና የተበከሉ መረጃዎችን በማጣራት አምካኝ ሥራ መሥራት።
1.5K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:48:27
ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከነሃሴ 16 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሾመዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኔትወርክ ኢንጂነር ባለሙያነት ጀምሮ እስከ ዲቪዥን ሃላፊነት ለ14 አመታት ያክል ተቋሙን አገልግለዋል፡፡

በ2014 ዓ/ም ተቋሙን ከለቀቁ በኋላም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ቴክኖሎጂ አማካሪ ሆነው ለአንድ አመት ሰርተዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ኢመደአ በመመለስ ከነሃሴ 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመዋል ፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን የማስተርስ ዲግሪያቸው ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ሮበርት ጎርደን ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን እና ኔትወርክ ሴኪዩሪቲ አግኝተዋል፡፡
1.5K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:04:13 ኢትዮጵያ የአበዳሪ ሀገራት ኮሚቴ የብድር ሽግሽግን በተመለከተ ላሳለፈው ውሳኔ አድናቆቷን ገለፀች
~~¿~~
የኢትዮጵያ መንግስት የአበዳሪ ሀገራት ኮሚቴ የሀገሪቱን የብድር ሽግሽግን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ በበጎ ጎን እንደሚቀበለው የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ የአበዳሪዎች ሀገራት ኮሚቴ ኢትዮጵያ የእዳ ጫናን ለማቅለል ያቀረበችውን የብድር ሽግሽግ በተመለከተ ምክክር ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የእዳ ክፍያ ጥያቄውን ይፋ ካደረገ በኋላ አበዳሪ ኮሚቴው አራት ጊዜ ስብሰባ በማድረግ ኢትዮጵያ የዕዳ ጫናን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የምትችልበትን ስትራቴጂዎች ማቅረቡ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ የዕዳ ጫናን ከከፍተኛ ወደ መካከለኛ ደረጃ ለማቃለል ባዘጋጀችው ስትራቴጂ መሰረት አስፈላጊውን የፋይናንስ ዋስትና ለመስጠት ከሚቴው ለሚያደርገው ጥረት መንግስት አድናቆቱን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አይ ኤም ኤፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለመደገፍ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በመንደፍ የሚያደርገውን ተሳትፎ አድንቋል ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአበዳሪ ሀገራት ኮሚቴውም ኢትዮጵያ በረዥም ጊዜ ሂደት ጫና ሳይበረታባት የሚጠበቅባትን የብድር ግዴታዎች መወጣት እንድትችል ለሚያደርገው የብድር ሽግሽግ አድናቆቱን መንግስት ገልጿል።
1.4K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ