Get Mystery Box with random crypto!

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ | The Niles ናይል 🇪🇹

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከነሃሴ 16 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሾመዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኔትወርክ ኢንጂነር ባለሙያነት ጀምሮ እስከ ዲቪዥን ሃላፊነት ለ14 አመታት ያክል ተቋሙን አገልግለዋል፡፡

በ2014 ዓ/ም ተቋሙን ከለቀቁ በኋላም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ቴክኖሎጂ አማካሪ ሆነው ለአንድ አመት ሰርተዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ኢመደአ በመመለስ ከነሃሴ 16/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመዋል ፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን የማስተርስ ዲግሪያቸው ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ሮበርት ጎርደን ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን እና ኔትወርክ ሴኪዩሪቲ አግኝተዋል፡፡