Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ጦርነት ወቅት መረጃ አሰጣጥ በመኩሪያ መካሻ ~ ከአአዩ 1. በጦርነት ወቅት የመረጃ | The Niles ናይል 🇪🇹

ስለ ጦርነት ወቅት መረጃ አሰጣጥ

በመኩሪያ መካሻ ~ ከአአዩ

1. በጦርነት ወቅት የመረጃ አሰጣጥ ጥብቅ ቁጥጥርን ይሻል።ወታደራዊ የግንባር መረጃዎች ይፋ መደረግ ያለባቸው በመከላከያ ቃል አቀባይ ብቻ ነው።
2.ሀገራዊ አጠቃላይ መረጃዎች በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ብቻ ይሰጡ።ከዚህ በፊት እንደታየው የወረዳ ኮሙኒኬሽንና የከተማ ሹም የሚሰጠው መግለጫ መኖር የለበትም።
3. ሀገር አቀፍ የዘማች ጋዜጠኞችን ቡድን በማደራጀት የዕዝ ጠገጉን የጠበቀ መረጃ ማሰራጨት።ጋዜጠኞቹ ከመከላከያ ጋር ተዳብለው(embedded) እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
4.በየሚዲያው የወታደራዊና ደህንነት ጉዳዩችን የሚከታተል የአርታኢያን ቡድን መሰየም።
5.በመንግስት ኮሙኒኬሽን በኩል ሀቅ አጣሪ፣የስነልቡና ጦርነቱን የሚመራ( ግብረ ሃይል(Ninja) በማቋቋም ሃሰተኛ ወሬዎችን፣የተዛቡና የተበከሉ መረጃዎችን በማጣራት አምካኝ ሥራ መሥራት።