Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ምህረት ደበበ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mihret_debebe — ዶ/ር ምህረት ደበበ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mihret_debebe — ዶ/ር ምህረት ደበበ
የሰርጥ አድራሻ: @mihret_debebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.49K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ሀሳቦች ይነሳሉ፡፡
✔የሳይኮሎጂ ምክር
✔አጫጭር ታሪኮች
✔የታዋቂ ሰዎች አጫጭር አባባሎች
<<...ካመለጠ ትናንት ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል።...>>

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-25 14:54:38 ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም!
(እ.ብ.ይ.)

ማንም ሰው ከእውቀት ጋር አልተወለደም፡፡ ሰው ሲወለድ እውቀት የሚያመነጭበትን አዕምሮ ይዞ ነው የተወለደው እንጂ ጥበበኛ ሆኖ አልተወለደም፡፡ ጥበብ ከማሰብ ብዛት፣ ከምርምር፣ ከጥናት፣ ከንባብ የሚገኝ ነው፡፡ ዕውቀት በቅን አስተሳሰብ፣ በበጎ ሕሊና፣ በአዕምሮ ድካም፣ በማሰብ ሂደት፣ የተለያዩ ሃሳቦችን በማስተናገድ የሚመጣ ነው፡፡ እናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሁሉን ያወቀ የሰው ልጅ የለም፡፡ ሁሉም ዕውቀትና ጥበብ፤ ክሂልና ልዩ ሃሳብ የተገኘው በመማር፣ በልምምድና በትጋት ነው፡፡
የሰው ልጅ ሲወለድ ማሰቢያ ማሽን ተገጥሞለት ነው የተወለደው፡፡ ይሄ ማሽን የማይታክት፣ የማይደክም፣ የማይሰለች፣ በቀንም ሆነ በሌት ዕረፍት የሌለው፣ መቼም ከስራው የማይዛነፍ ነው፡፡ ሰው ጤንነት ጎድሎት ቢያብድ እንኳን አዕምሮ የእብድ ሃሳብ ከማመላለስና ከመከወን አያርፍም፡፡ አዕምሮ የረባም ሆነ ያልረባን ሃሳብን እንደግብዓት ተጠቅሞ ውጤቱን የሚሰጥ ልዩ ማሽን ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ግን ጥሩ ግብዓት መስጠት ግድ ይላል፡፡ የስንዴ እህል ወፍጮ ቤት ወስዶ የጤፍ ዱቄት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ የሰጠነውን አሳምሮ የሚሰጥ ነው ውዱ ሐብታችን (Give and take ነው ጨዋታው)፡፡ ያልሰጠነውን አይሰራም፤ የሰጠነው እንክርዳዱንም ቢሆን እህል አድርጎ አያወጣም፡፡

የአዕምሮ ጥሬ እቃ ሃሳብ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ ማሰብ ነው፡፡ ማሰብና ሃሳብ ደግሞ በአሳቢው ይወሰናል፡፡ የአዕምሮ ቁልፉ ያለው በአዕምሮው ባለቤት በግለሰቡ እጅ ላይ ነው፡፡ ይሄ ቁልፍ ነው ሰውን በሞራል፣ በስብዕና፣ በምግባር ከፍም ዝቅም የሚያደርገው፡፡ ግለሰባዊ የሃሳብ ልዩነት የመጣው የአዕምሮ ምርቱ የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ የተለያየ አዕምሮ እንደአስተሳሰቡና እንደሃሳቡ ይለያያል፡፡ የሃሳብ ልዩነቱ እንዳጠቃቀማችን ይወሰናል፡፡ አዕምሮውን በርግዶ የመክፈትም ሆነ ጠርቅሞ የመዝጋት ፈቃዱ ያለው እያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ነው፡፡ አዕምሮ እንዲያስብ ማሳሰብ ያለበት ግለሰቡ ነው፡፡ ጥልቅ አሳቢ ሰው የአዕምሮውን ቁልፍ ለመጠቀም የሚፍጨረጨር ነውና፡፡

አዕምሯዊ ብልጽግና የሃብት ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ በሃሳብ ሳይሰለጥኑ፣ በማሰብ ሳይዘምኑ፣ በቅን አስተሳሰብ ከፍ ሳይሉ ውስጣዊ ብልጽግና አይገኝም፡፡ መርማሪ ሕሊና፣ አመዛዛኝ ልቦና፣ የነቃ አዕምሮ ባለቤት መሆን የሚቻለው በሃሳብ መበልፀግ ሲቻል ነው፡፡ በማሰብ የጠለቀ፣ በሃሳብ የረቀቀ፣ በበጎ ስራ የከበረ አዕምሮ የበለፀገ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል፣ በሃሳቡ ጥልቀት የሚመካ ደግሞ በሃሳብ ይበለፅጋል፡፡ በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን የበለፀገ አዕምሮ እንጂ ስሙ ብልፅግና የሆነ ፓርቲ አይደለም፡፡ ፓርቲ የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ አባላቱ ሳይበለፅጉ የፓርቲያቸው ስም ብልጽግና ቢሆን ስምና ግብር ለየቅል ይሆናል፡፡ ስሙ ይቆየን፤ ግብሩ ይቅደመን!

አዕምሮ የሌሎች ሐብቶች ሁሉ ምንጭ ቢሆንም ሰው ሐብት ፍለጋ ከአዕምሮው ኮብልሎ የውጪውን ዓለም ነው የሚያማትረው፡፡ ራሱን የዘነጋ መቼም ቢሆን ከአዕምሮው ጋር ተስማምቶ መኖር አይችልም፡፡ ከራሳችን ጋር መጣላት የምንጀምረው የራሳችንን ሐብት ዘንግተን ሌላ ሐብት ፍለጋ መባከን ስንጀምር ነው፡፡ ያሰብነው ዓለማዊ ሐብት በእጅ ቢገባ እንኳን ያለአዕምሮ አይደላደልም፡፡ በማሰብ ያልተዘጋጀ አዕምሮ እንግዳ ነገር ሲገጥመው መልስ ለመስጠት ደመነፍሱን ይጠቀማል፤ ስሜቱን ያስቀድማል፡፡ ሰው አይደለም ለቁሳዊ ሐብቱ ቀርቶ ለመንፈሳዊ ሐብቱ ጭምር አዕምሮውን መጠቀሙ ግድ ይለዋል፡፡ የደስታና ሐዘን፣ የእርካታና ርሃብ መሰረቱ አዕምሮ ነውና፡፡ ሰላምም ሆነ ጦርነት በዓለማችን ላይ የሚከሰተው አዕምሮን ከማሰራት እና ካለማሰራት ነው፡፡ ነገር ግን የተሰጠን ሐብት ድንቅ ቢሆንም አብዛኞቻችን የሚደነቁ ስራዎችን ያልሰራነው አዕምሯችንን ባለመበልጸጉ ነው፡፡

አዎ በዚህ ዘመን ድንቁን አዕምሮ በበቂና በብቃት የሚጠቀምበት ሰው እምብዛም ነው፡፡ ጥቂት ሰዎች በተለያየ ዘመን ተነስተው አዕምሯቸውን በሙላት ተጠቅመዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው የአለምን አካሄድ የሚቀይር ችግር ፈቺ ሃሳቦችንና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ አዕምሮን በሙላት መጠቀም ከራስ አልፎ ለዓለምም ያስተርፋል፡፡ አይደለም ለሰፊው ዓለም ቀርቶ ለአንድ ሰው እንኳን መትረፍ ደስታው ምን ያህል እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ከሁሉ ከሁሉ የአዕምሮ መክሊትህን በሙላት ተጠቀም፡፡ አምላክ የሰጠህ ተጠቅመህ እንድታተርፍበት እንጂ ቀብረህ እንድታባክነው አይደለም፡፡ አውቀህ ባትወለድም በንባብ፣ በምርምርና በማሰብ ሃይል እውቀትና ጥበብን በእጅህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን አዕምሯዊ ሀብት ደግሞ ለዓለም አስቀርተህ ወደማይቀረው መሄድ ትችላለህ፡፡ አዕምሮህን በሙላት መጠቀም ስትጀምር ከመምሰል ዓለም ወጥተህ በመሆን ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኛለህ፡፡ መሆን እንጂ መምሰልና ማስመሰል የሌለበት ህይወት የምትጎናፀፈው አዕምሮህ ሲበለፅግ ብቻ ነው፡፡ ከፓርቲህ በፊት አዕምሮህን አበልፅግ፡፡ ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም፡፡

‹‹በማሰብ ያልሰለጠነ፣
በሃሳብ ያልዘመነ፣
በሕሊና ያላደገ፣
በቅንነት ያልበለፀገ፣
መክሊቱን ቀበረ፣
አዕምሮውን ከሰረ፡፡››

ቸር የአዕምሮ ብልጽግና!
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
4.0K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 14:54:38 አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ ከሁሉ የሚልቅ ወዳጅነት ነው!
(እ.ብ.ይ.)

ዓለማዊው ወይም ውጫዊው ወዳጅነት እና ጓደኝነት ግላዊ ነው፡፡ ወዳጅነት ሁለት ወይም ሶስት ቢበዛ እስከአራት ድረስ የሚደርሱ ሠዎች እርስበርሳቸው የሚያቋቁሙት ፈቃዳዊ ውል ነው፡፡ ጓደኝነት ክፉንም ደጉንም፣ ሃሳቡንም ጭንቀቱንም የሚካፈሉበት መድረክ ነው፡፡

በዚህ ወዳጅነት ውስጥ ሚስጥር መጠበቅ ዋነኛው መስፈርት ነው፡፡ ‹‹አትንገር ብዬ ብነግረው፤ አትንገር ብሎ ነገረው›› የሚለው ብሂል ወዳጅነትን አፈር የሚያስግጥ፤ የሞቀ ጓደኝነት ላይ ውሃ የሚቸልስ ክህደት ነው፡፡ ወዳጅነት ሚስጥርን መጠበቅ ካልቻለ እውነተኛ ጓደኝነት አይሆንም፡፡ በዚህ ዘመን የምናየው አብዛኛው ወዳጅነት ግን እውነተኛ ጓደኝነትን የማይገልፅ ተግባቦት ብቻ ሆኗል፡፡ አንድ ሠው ወዳጅነቱን ለማስፋት ሲል ብዙ ሠዎችን ጓደኛ ያደርጋል፡፡ ለሠው ከብዙ ሠዎች ጋር መግባባቱ ክፋት ባይኖረውም የልብን የሚያዋዩት ሠው ግን አንድ አልያም ሁለት ወዳጅ ግድ ይለዋል፡፡ እውነተኛ ወዳጅ የውስጥን የሚተነፍሱለት፣ ጭንቀትንና ጥበትን ተካፍሎ አዲስ የተስፋ መንገድ የሚያሳይ፤ እንዲሁም አብሮ አዝኖ አብሮ የሚደሠት የልብ ጓደኛ ነው፡፡

አርስጣጢሊስ ‹‹ለሁሉም ጓደኛ የሆነ ለማንም ጓደኛ መሆን አይችልም፡፡›› ይለናል፡፡ እውነት አለው! ከብዙ ሠዎች ጋር በስራ፣ በጉርብትና፣ በዝምድና፣ በተለያዩ ጉዳዮች መግባባትና ማሕበራዊ ሕይወትን መካፈል ደስ የሚያሠኝ ቢሆንም ወዳጅነት ግን በጥቂት ሠዎች ብቻ የሚመሠረት ማሕበራዊ ውል ነው፡፡

የሠው ወዳጅ መልካም ቢሆንም የአዕምሮ ወዳጅ ግን ከሁሉ ይልቃል፡፡ የገዛ አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ፣ ከህሊና ጋር ጓደኛ መሆን፣ ከልቦናችን ጋር አለመጣላት ከወዳጆች ሁሉ የበለጠ ወዳጅነት ነው፡፡ አዕምሮን መቅረፅ፣ በአዕምሮ መንገድ መመላለስ፣ ሕሊናን ማርቀቅ፣ ናላን ማጫወት፣ ልቦናን ማትጋት ከሠው ልጅ የሚጠበቅ ትልቅ ተጋድሎ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተጋዳላይ የምንሆነው ከውጫዊው ሕይወታችን ጋር ነው፡፡

እርግጥ ነው ለመኖር መስራት ይጠበቅብናል፤ ሆዳችንን ለመሙላት መውጣት መውረድ ግድ ይለናል፡፡ ሆኖም ግን አዕምሮን ማስደሰት፣ ሕሊናን ማጥገብ፣ ልቦናን ማርካት እንዳለብንም መዘንጋት የለብንም፡፡ ነፍስያችን የሚደሠተው፣ መንፈሳችን ሐሴት የሚያደርገው ከአዕምሯችን ጋር ተግባብተን እውነተኛ ወዳጅ ስንሆን ብቻ ነው፡፡ የስጋ ፍላጎትን መሙላት ጊዜያዊ ደስታ ሲሠጥ የአዕምሮን ፈቃድ መሙላት ግን የማይነጥፍ ደስታን ያጎናፅፋል፡፡ በሕይወታችን ታላቁን ፍስሃ የምናገኘው ሕሊናችንን አርቅቀን ልባዊ መሻታችንን ስንሞላ ነው፡፡ ስጋ ደንድኖ ሕሊና ቢቀጥን ደስታ አይገኝም፡፡ ቦርጫችን ገፍቶ አዕምሯችን ቢራብ እውነተኛ እርካታ እውን አይሆንም፡፡ ምግባራችን፣ ተግባራችን፣ የሕይወት ምልልሳችን ትርጉም ያለው የሚሆነው ከውስጣችን ጋር ተግባብተን፣ ሕሊናችንን ስለን፣ ከአዕምሯችን ጋር ወዳጅ ስንሆን ብቻ ነው፡፡

ብዙ ሠው ከራሱ ጋር ተጣልቷል፡፡ ግብ ግቡ ቀላል አይደለም፡፡ ገላጋይ የማይፈታው ነው፡፡ ገላጋዩም፣ አስታራቂው ሽማግሌም ሌላ ሳይሆን ራሱና ራሱ ብቻ ነው፡፡ ከራሱ ጋር እርቅ የማይፈፅምና ከሕሊናው ጋር ወዳጅ የማይሆን መጨረሻው አያምርም፡፡ ከአዕምሮው ጋር ፀብ የገባ ሠው ራሱንና ጨርቁን ይጥላል፡፡ በየመንገዱ የምናያቸው የአዕምሮ ሕመምተኞች ከአዕምሯቸው ጋር ጦርነት ገጥመው በሽንፈት እጅ የሠጡ ናቸው፡፡ የአዕምሮውን ሠላም ማስጠበቅ የማይችል ሠው መጨረሻው ከራሱ ጋር መጋጨት ነው፡፡ የዚህም ዋና ምክንያቱ ከአዕምሮው ጋር ወዳጅነት መፍጠር ባለመቻሉ ነው፡፡ ሕሊናውን ከመስማት ይልቅ ዓይቶ ባላየ፣ ሠምቶ ባልሠማ በመሆኑ ነው፡፡ አብዛኛው ሠው ከሌሎች ሠዎች ጋር መወዳጀትን እንጂ ከራሱ ጋር መግባባትን ይዘነጋዋል፡፡ ከራሱ ያልተግባባ ከሌላው ጋር እንዴት ይግባባል??? ከሌላው ጋር ወዳጅ ለመሆን ከራስ ጋር መወዳጀት ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ ከውጫዊ ዓለም ጋር ተግባብቶ ለመኖር ከውስጣችን ዓለም ጋር መዋሃድ ግድ ይለናል፡፡

ወዳጄ ሆይ…. አዕምሮን ወዳጅ ማድረግ ከሁሉ የሚልቅ ወዳጅነት ነው! ወዳጅ በማብዛት እውነተኛ ወዳጅነት አይገኝም፡፡ ከራስ ጋር መወዳጀት ግን ከሁሉ የሚበልጥ ዓላማ ያለው ተግባር ነው፡፡ ከራሱ ጋር ወዳጅ የሆነ ከሌላ ሠው ጋር ወዳጅ ሆኖ ፀንቶ ለመቆየት አይከብደውም፡፡ ከራሳቸው ጋር ሳይወዳጁ ወዳጅ የሚያንጋጉ ሠዎች የወዳጃቸውን ሚስጥርና ገበና አደባባይ ያወጣሉ፡፡ ወዳጅነት ልክ፣ ገደብ፣ ወሰንና ድንበር አለውና የጓደኝነት ሚዛኑን በማስተዋል እንያዝ የዛሬው መልዕክት ነው፡፡ ከራስ ጋር መግባባት፣ ከራስ ጋር እርቅ መፈፀም የመግባባትና የእርቆች ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ከአዕምሮ ጋር መወዳጀት የወዳጅነት ቁንጮ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ ቀድመህ ከራስህ ጋር ታረቅ፤ ቀጥለህ አዕምሮህን ወዳጅ አድርግ! በመጨረሻም ከዓለሙ ጋር ተስማምተህ መኖር የሚያስችልህ ዕውቀትና ልምድን ታገኛለህ! አዲዮስ!

‹‹ከሕሊናህ ጋር ተጨዋወት!
አዕምሮህን ተወዳጀው!
ጠላት አርገኸው!
እንዳይፈጅህ!
እንዳትፈጀው፡፡››

ቸር ወዳጅነት!

ቸር ጊዜ!
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
3.2K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 14:54:37 ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም!
(እ.ብ.ይ.)

ማንም ሰው ከእውቀት ጋር አልተወለደም፡፡ ሰው ሲወለድ እውቀት የሚያመነጭበትን አዕምሮ ይዞ ነው የተወለደው እንጂ ጥበበኛ ሆኖ አልተወለደም፡፡ ጥበብ ከማሰብ ብዛት፣ ከምርምር፣ ከጥናት፣ ከንባብ የሚገኝ ነው፡፡ ዕውቀት በቅን አስተሳሰብ፣ በበጎ ሕሊና፣ በአዕምሮ ድካም፣ በማሰብ ሂደት፣ የተለያዩ ሃሳቦችን በማስተናገድ የሚመጣ ነው፡፡ እናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሁሉን ያወቀ የሰው ልጅ የለም፡፡ ሁሉም ዕውቀትና ጥበብ፤ ክሂልና ልዩ ሃሳብ የተገኘው በመማር፣ በልምምድና በትጋት ነው፡፡
የሰው ልጅ ሲወለድ ማሰቢያ ማሽን ተገጥሞለት ነው የተወለደው፡፡ ይሄ ማሽን የማይታክት፣ የማይደክም፣ የማይሰለች፣ በቀንም ሆነ በሌት ዕረፍት የሌለው፣ መቼም ከስራው የማይዛነፍ ነው፡፡ ሰው ጤንነት ጎድሎት ቢያብድ እንኳን አዕምሮ የእብድ ሃሳብ ከማመላለስና ከመከወን አያርፍም፡፡ አዕምሮ የረባም ሆነ ያልረባን ሃሳብን እንደግብዓት ተጠቅሞ ውጤቱን የሚሰጥ ልዩ ማሽን ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ግን ጥሩ ግብዓት መስጠት ግድ ይላል፡፡ የስንዴ እህል ወፍጮ ቤት ወስዶ የጤፍ ዱቄት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ የሰጠነውን አሳምሮ የሚሰጥ ነው ውዱ ሐብታችን (Give and take ነው ጨዋታው)፡፡ ያልሰጠነውን አይሰራም፤ የሰጠነው እንክርዳዱንም ቢሆን እህል አድርጎ አያወጣም፡፡

የአዕምሮ ጥሬ እቃ ሃሳብ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ ማሰብ ነው፡፡ ማሰብና ሃሳብ ደግሞ በአሳቢው ይወሰናል፡፡ የአዕምሮ ቁልፉ ያለው በአዕምሮው ባለቤት በግለሰቡ እጅ ላይ ነው፡፡ ይሄ ቁልፍ ነው ሰውን በሞራል፣ በስብዕና፣ በምግባር ከፍም ዝቅም የሚያደርገው፡፡ ግለሰባዊ የሃሳብ ልዩነት የመጣው የአዕምሮ ምርቱ የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ የተለያየ አዕምሮ እንደአስተሳሰቡና እንደሃሳቡ ይለያያል፡፡ የሃሳብ ልዩነቱ እንዳጠቃቀማችን ይወሰናል፡፡ አዕምሮውን በርግዶ የመክፈትም ሆነ ጠርቅሞ የመዝጋት ፈቃዱ ያለው እያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ነው፡፡ አዕምሮ እንዲያስብ ማሳሰብ ያለበት ግለሰቡ ነው፡፡ ጥልቅ አሳቢ ሰው የአዕምሮውን ቁልፍ ለመጠቀም የሚፍጨረጨር ነውና፡፡

አዕምሯዊ ብልጽግና የሃብት ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ በሃሳብ ሳይሰለጥኑ፣ በማሰብ ሳይዘምኑ፣ በቅን አስተሳሰብ ከፍ ሳይሉ ውስጣዊ ብልጽግና አይገኝም፡፡ መርማሪ ሕሊና፣ አመዛዛኝ ልቦና፣ የነቃ አዕምሮ ባለቤት መሆን የሚቻለው በሃሳብ መበልፀግ ሲቻል ነው፡፡ በማሰብ የጠለቀ፣ በሃሳብ የረቀቀ፣ በበጎ ስራ የከበረ አዕምሮ የበለፀገ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል፣ በሃሳቡ ጥልቀት የሚመካ ደግሞ በሃሳብ ይበለፅጋል፡፡ በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን የበለፀገ አዕምሮ እንጂ ስሙ ብልፅግና የሆነ ፓርቲ አይደለም፡፡ ፓርቲ የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ አባላቱ ሳይበለፅጉ የፓርቲያቸው ስም ብልጽግና ቢሆን ስምና ግብር ለየቅል ይሆናል፡፡ ስሙ ይቆየን፤ ግብሩ ይቅደመን!

አዕምሮ የሌሎች ሐብቶች ሁሉ ምንጭ ቢሆንም ሰው ሐብት ፍለጋ ከአዕምሮው ኮብልሎ የውጪውን ዓለም ነው የሚያማትረው፡፡ ራሱን የዘነጋ መቼም ቢሆን ከአዕምሮው ጋር ተስማምቶ መኖር አይችልም፡፡ ከራሳችን ጋር መጣላት የምንጀምረው የራሳችንን ሐብት ዘንግተን ሌላ ሐብት ፍለጋ መባከን ስንጀምር ነው፡፡ ያሰብነው ዓለማዊ ሐብት በእጅ ቢገባ እንኳን ያለአዕምሮ አይደላደልም፡፡ በማሰብ ያልተዘጋጀ አዕምሮ እንግዳ ነገር ሲገጥመው መልስ ለመስጠት ደመነፍሱን ይጠቀማል፤ ስሜቱን ያስቀድማል፡፡ ሰው አይደለም ለቁሳዊ ሐብቱ ቀርቶ ለመንፈሳዊ ሐብቱ ጭምር አዕምሮውን መጠቀሙ ግድ ይለዋል፡፡ የደስታና ሐዘን፣ የእርካታና ርሃብ መሰረቱ አዕምሮ ነውና፡፡ ሰላምም ሆነ ጦርነት በዓለማችን ላይ የሚከሰተው አዕምሮን ከማሰራት እና ካለማሰራት ነው፡፡ ነገር ግን የተሰጠን ሐብት ድንቅ ቢሆንም አብዛኞቻችን የሚደነቁ ስራዎችን ያልሰራነው አዕምሯችንን ባለመበልጸጉ ነው፡፡

አዎ በዚህ ዘመን ድንቁን አዕምሮ በበቂና በብቃት የሚጠቀምበት ሰው እምብዛም ነው፡፡ ጥቂት ሰዎች በተለያየ ዘመን ተነስተው አዕምሯቸውን በሙላት ተጠቅመዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው የአለምን አካሄድ የሚቀይር ችግር ፈቺ ሃሳቦችንና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ አዕምሮን በሙላት መጠቀም ከራስ አልፎ ለዓለምም ያስተርፋል፡፡ አይደለም ለሰፊው ዓለም ቀርቶ ለአንድ ሰው እንኳን መትረፍ ደስታው ምን ያህል እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ከሁሉ ከሁሉ የአዕምሮ መክሊትህን በሙላት ተጠቀም፡፡ አምላክ የሰጠህ ተጠቅመህ እንድታተርፍበት እንጂ ቀብረህ እንድታባክነው አይደለም፡፡ አውቀህ ባትወለድም በንባብ፣ በምርምርና በማሰብ ሃይል እውቀትና ጥበብን በእጅህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን አዕምሯዊ ሀብት ደግሞ ለዓለም አስቀርተህ ወደማይቀረው መሄድ ትችላለህ፡፡ አዕምሮህን በሙላት መጠቀም ስትጀምር ከመምሰል ዓለም ወጥተህ በመሆን ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኛለህ፡፡ መሆን እንጂ መምሰልና ማስመሰል የሌለበት ህይወት የምትጎናፀፈው አዕምሮህ ሲበለፅግ ብቻ ነው፡፡ ከፓርቲህ በፊት አዕምሮህን አበልፅግ፡፡ ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም፡፡

‹‹በማሰብ ያልሰለጠነ፣
በሃሳብ ያልዘመነ፣
በሕሊና ያላደገ፣
በቅንነት ያልበለፀገ፣
መክሊቱን ቀበረ፣
አዕምሮውን ከሰረ፡፡››

ቸር የአዕምሮ ብልጽግና!
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.7K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-18 23:08:43 #የሆነው_ያሳዝናል

#ለስራ_ብለው_ጠርተውት_አስቀሩት

#እባካችሁን_እንድረስለት

#አቤል_አማርከኝ ይባላል!!ፀባየኛና ድምፁ የማይሰማ

ከሁሉም ጋር የሚግባባ በራይድ ስራ የሚተዳደር ታታሪ ወጣት ነው!ቅዳሜ ህዳር4 አየርጤና 5:00ሰዓት አካባቢ ከጓደኛው ጋር ሆነው አንድ ስልክ ይደወልለታል!

ደዋዩ እንደሚያውቀው ሆኖ ቢያወራውም የአቤል መልስ ግን እንዳላወቀው ያስታውቃል!!

"አንድ ቦታ ደርሰን እንምጣ ጉሽ ሆቴል አካባቢ ነን" ብለውኛል ልሂድ ብሎ ከጓደኛው መኪና ላይ ወረደ!!

ከአዲስአበባ ሲወጣ ብዙ ጊዜ የመናገር ልምድ ያለው አቤላ ከታናሽ እህቱ ጋር 8ሰዓት ላይ ተደዋውለው #ተሬ

የሚባል ቦታ እንደደረሱና ወደ ቅያስ ገብተው እንደቆሙ ያሳፈራቸውም ሰዎች ቤት ውስጥ ገብተው እስኪወጡ

እየጠበቃቸው እንደሆነና ሲመለስም እንደሚደውልላት አውርተው ስልኩ ተዘጋ!!

ከደቂቃዎች በኋላ ያላስቻላት እህት ደጋግማ ብትደውል

ሁለቱም ስልኮቹ ዝግ ሆነባትጓደኞቹን ብትጠይቃቸው

እረ እኔጃ እኛም አላወቅንም ምን ሆነ? ይሏታል

የፈለገ ቢመሽበት ለሊትም ቢሆን እንኳ እናቱ ቤት ገብቶ ያድራል እንጂ ዉጪ አድሮ የማያውቀው አቤል የት እንደገባ ምን እነደሆነ ሳያውቁ 5ቀናት ተቆጥረዋል

ጓደኞቹና ቤተሰብ ከእሁድ ለሊት ጀምረው ወደ ተባለው

ቦታ ጉዞ ጀምረው በሰዎች ትብብር #ቡታጅራ መስመር #ሱተን የሚባል ቦታ ላይ በምልክት ታግዘው በብር ተደራድረው ሲደርሱበሚገርም ሁኔታ መኪናው የኋላ ታርጋው ተፈቶ የአንድ ባለሀብት እናት ግቢ ውስጥ ተገኘ!

እንዴት ለምን ሲባሉ!የሚያስቅ መልስ ለፖሊስ ሰጥተዋል

#ግን_አልተያዙም አቤል ያለበትንም አልተናገሩም

የታወቀው ሌባ በምልክት ሲፈለግ አንድ የፈዘዘ ልጅ ይዞ ሲንቀሳቀስ አይተናል ብለው እማኞች ተናግረዋል

#ጤነኛውን_ልጅ ለገንዘብ ሲሉ ምን አድርገውት ይሆን?

#ጓደኞቹ መድሀኒት አጠትተውብን ይሆን?ብለው በጣም

ሰግተዋል #እባካችሁን #SHARE_ሼር በማድረግ

#ምስኪኑን_እንድረስለት #እናቱ_ተጨንቃለች

"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0980185553
0968519191
0910970775
8.4K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-18 23:08:42
3.2K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 22:05:02 ሰውየው ትልቅ ሰንጋ ይገዛና ጎረቤቶቹንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ብሎም ወዳጆቹን ለመጋበዝ ይወስናል።
ስጋው መጠባበስ መዘጋጀት ሲጀምር ታናሽ ወንድሙን ይጠራውና ፦
"እስኪ ሂድና ወዳጅ ጎረቤቶቻችንን ቶሎ ጥራና ከማዕዳችን ይቋደሱ " ይለዋል።

ታናሽ ወንድሙም ወደ ውጭ ይወጣና ጩኸት ይጀምራል፦
"ኡ ኡ ኡ ድረሱልን እሳት እሳት…ድረሱልን" ማለት ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ሰዎች ከየቤቶቻቸው ወጥተው ወደ ሰውየው ቤት አመሩ። ሆኖም ከሰውየው ቤት እንደገቡ ያጋጠማቸው የተለየ ነገር ነበር። የመጣው ሰው ሁሉ እስኪበቃው ድረስ በልቶና ጠጥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ደጋሹ ወንድም ታናሽ ወንድሙን ጠራውና ፦" ዛሬ ከመጡት ሰዎች ብዙም የማውቃቸው ሰዎች የሉም ፤ ከዚህ በፊትም አይቻቸው አላውቅም፤ የት አሉ ወዳጆቻችንና ጓደኞቻችን !?" ሲል ጠየቀው።

ወንድሙም፦ "እነዚህ ሰዎች እኮ ቤታችን እሳት አለ ብዬ ስጠራቸው የመጡ ሰዎች እንጂ ድግስ አለ ብዬ ጠርቻቸው አይደለም ፤ የዚህ አይነቱ ሰው እኮ ነው ክብርና እንክብካቤ የሚያስፈልገው" ሲል መልስ ሰጠው።

በቸገረህ ጊዜ ከጎንህ የማይቆምን ሰው ወዳጅ ወይም ጓደኛ አድርጎ መያዝ ጉዳት ነው። እውነተኛ ወዳጅ በቸገረህና በተጨነቅክ ጊዜ ከጎንህ የቆመ ሰው ነው።
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
3.5K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 21:39:04 ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል፡፡ ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ከመስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው:ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ " በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ...

በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው!

ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ። ወሰዱለት። ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ።

"ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት።

"ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር" ስትል በመገረም መለሰችለት፡፡

ልብ የሚነካ ነገር.. ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው። ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ የተጨነቀ አምሮአቸውን እረፍት እንስጠው::
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
3.1K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 21:31:35 ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ ከወንዙ በወድያኛው ዳር ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።

ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ
ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምመሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?" አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?" በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም። ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን፡፡
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.5K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-01 17:14:23 የጉብዝና ጊዜ
ሰው ህፃን ሳለ እና በእርጅናው ገዜ የሚመራው በስሜታዊነት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ሁለቱ የእድሜ ክልሎች ላይ ስንደርስ ከማይንዳችን ይቀልጡን መስራት የሚጀምረው ስሜታዊ የሆነው የአይምሮአችን ክፍል ስለሆነ ነው። ህፃናት ለስሜታቸው እና ለፍላጎታቸው በጣም ቅርብ ናቸው። ምክንያቱም የማገናዘብ አቅማቸው በዛ ሰአት መስራት ስለማይጀምር ነው። በእርጅና ወቅት ደግሞ ምክንያታዊ የሆነው የአይምሮ ክፍል እየደከመ ስለሚመጣ ነው።

በጉብዝናህ ጊዜ ግን ሁለቱንም የአይምሮ ክፍል መጠቀም ትችላለህ። ስሜታዊውንም ምክንያታዊውንም። በነዚህ ወቅት ላይ በስትክክል የምትጠቀመው ከሆነ እና ከነቃህበት በስተርጅናህ ጊዜ የተስተካከለ ህይወት ትመራለህ። የጉብዝና ወቅት የሚባለው የወጣትነህ ጊዜ ነው።

በዚህ የወጣትነት ጊዜ ሶስት ትላልቅ ሀይሎች አሉህ፦
ሙሉ እና በምንም ያልተያዘ ጊዜ አለህ። በዚህ የወጣትነህ ጊዜ ላይ የህይወትህን ሙሉ ፕሮግራም የምትሰራበት ነው።
ሌላኛው በምንም ያልተነካ እና ንፁህ የሆነ አቅም አለህ። ጉልበትህን የምታከማችበት እና መጠቀም የምትጀምርበት ምርጡ ጊዜህ ነው። በዚህ ጊዜ ልክ እንደጉንዳኖች በበጋው ወቅት ለክረምት የሚሆን ምግብ የምትሰበስብበት አቅም ይኖርሀል።
ውበት ይኖርሀል። የምትፈካበት የምትደምቅበት እና ለብዙዎች የምትታይበት ወቅት ነው። ውበትህ በራሱ የነገህን የምትገነባበት አንደኛው መሳሪያ ሲሆን ያለጊዜው እና ያለቦታው ካዋልከው ነገህን በፀፀት እንድትሞላው ከሚያደርጉህ ከህይወት በረከቶችህ መሀከል አንደኛው ነው።

ሌላኛው እና ዋነኛው ደግሞ አይምሮህ ሲሆን እንድታስብበት እና ከላይ የጠቀስኳቸውን የህይወት በረከቶች እንዴት መጠቀም እንዳለብህ የሚመራህ ነው። አንድ መርከብ የቱንም ያህል ግዙፍ ቢሆን የሚመራው ግን ትንሽ የሆነችው መሪ ናት። አንተም የቱንም ያህል ግዙፍ ብትሆን ሀብት ቢኖርህ ውበት ብታከማች ያለ አይምሮህ የምትኖር ከሆነ ተራ ነው የምትሆነው።

ስለዚህ በጉብዝናህ ጊዜ የተሠጡህን እነዚህን በረከቶች በጊዜው በወጣትነት ትጠብቃቸው እና በአግባቡ ትጠቀምባቸው ዘንድ ምክሬ ነው። መልካም ቀን
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.8K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-01 17:14:23 አዲስነት የጊዜ ጉዳይ ሳይሆን የራስ ለውጥ ነው

አዲስ የሚባለው ነገር ወይ ከመጀመሪያው ያልነበረ ወይም ደግሞ የነበረው እንደአዲስ ሲታደስ ነው። የጊዜ አዲስ የለውም። ለምን መሠላችሁ ሰዎች በጊዜ ውስጥ ያልፋሉ እንጂ ጊዜ በሰው ውስጥ አያልፍም። ይህ ማለት ጠዋት ስትነሡ ጊዜ ይኖራል። ጊዜ የሚኖረው እኔ ዮናስ እስካለው ብቻ ነው። እኔ ከሞትኩ ጊዜ የሚባል ነገር የለም። ይሄ እውነታ ነው።አንድ ነገር የሚኖረው እናንተ እስካላችሁ ብቻ ነው።
ስለዚህ የጊዜ አዲስ የለውም። አዲስ የሚሆንም ነገር የለም። አዲስ ከሆናችሁ አዲስ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ። እሱንም የሀሳብ ለውጥ ካመጣችሁ ነው። አዲስ የምትሆኑት የትላንታችሁን ስለምትረሱት ሳይሆን በትላንታችሁ ውስጥ መኖር ስታቆሙ ነው። እንዳንዳንዶች አዲስ የሆነ ማንነት ገንቡ ምናምን ብዬ አልሰክስም። ምክንያቱም ምንም ምትገነቡት አዲስ ማንነት ስለሌላችሁ ነው።
ሰው በዉስጡ ያለውን ማንነት ነገሮች ሲስተካከሉ እና ሀሳቡ ሲሻሻል እያስተካከለ ይጠቀመዋል እንጂ አዲስ የሚፈጥረው ምንም አይነት ማንነት የለውም።
ስለዚህ ምንም አዲስ የሚባል አመትም ሆነ ቀን የለም። ይሄ ካልተዋጠልህ ሳትወድ በግድህ በውሀ ታወራርደዋለህ።
አንድን ነገር አዲስ የሚያደርገው ያንተ መኖር ብቻ ነው።
በነገራችን ላይ የእድሜህንም ቁጥር ያወከው ሰዎች በሠጡህ የጊዜ አቆጣጠር ተጠቅመህ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። ከዛም ሰው 80 አመት ሲሞላው የመሞቻ ጊዜው እንደደረሰ ታስብ እና ሞት ሞት ይሸትሀል ከዛም ትሞታለህ።
የገጠር ሠዎችን አይተሀቸው ታውቃለህ እድሜያቸውን አያቁትም ቀኑንም አይቆጥሩም በቃ ዝም ብለው ይኖራሉ። ሚገርመው ቶሎ አለመሞታቸው ነው። ምክንያቱም አያቁማ ሰው በስንት እድሜው እንደሚሞት። ስለዚህ አያስቡም። አንተ ግን ትቆጥራለህ የቆጠርካት ላይም ከአፈር ትቀላቀላለህ።
ስለዚህ ባትጃጃሉ መልካም። በተቻላችሁ መጠን አዲስ ዘመን ስለመጣ እቅድ አታውጡ ይሄ በአል እረፈስኪያልፍ እቅድ አታውጡ። ጊዜው ይለፍ ከዛም ታወጣላችሁ። መልካም ቀን እወዳችሁዋለው
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.4K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ