Get Mystery Box with random crypto!

የጉብዝና ጊዜ ሰው ህፃን ሳለ እና በእርጅናው ገዜ የሚመራው በስሜታዊነት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ሁ | ዶ/ር ምህረት ደበበ

የጉብዝና ጊዜ
ሰው ህፃን ሳለ እና በእርጅናው ገዜ የሚመራው በስሜታዊነት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ሁለቱ የእድሜ ክልሎች ላይ ስንደርስ ከማይንዳችን ይቀልጡን መስራት የሚጀምረው ስሜታዊ የሆነው የአይምሮአችን ክፍል ስለሆነ ነው። ህፃናት ለስሜታቸው እና ለፍላጎታቸው በጣም ቅርብ ናቸው። ምክንያቱም የማገናዘብ አቅማቸው በዛ ሰአት መስራት ስለማይጀምር ነው። በእርጅና ወቅት ደግሞ ምክንያታዊ የሆነው የአይምሮ ክፍል እየደከመ ስለሚመጣ ነው።

በጉብዝናህ ጊዜ ግን ሁለቱንም የአይምሮ ክፍል መጠቀም ትችላለህ። ስሜታዊውንም ምክንያታዊውንም። በነዚህ ወቅት ላይ በስትክክል የምትጠቀመው ከሆነ እና ከነቃህበት በስተርጅናህ ጊዜ የተስተካከለ ህይወት ትመራለህ። የጉብዝና ወቅት የሚባለው የወጣትነህ ጊዜ ነው።

በዚህ የወጣትነት ጊዜ ሶስት ትላልቅ ሀይሎች አሉህ፦
ሙሉ እና በምንም ያልተያዘ ጊዜ አለህ። በዚህ የወጣትነህ ጊዜ ላይ የህይወትህን ሙሉ ፕሮግራም የምትሰራበት ነው።
ሌላኛው በምንም ያልተነካ እና ንፁህ የሆነ አቅም አለህ። ጉልበትህን የምታከማችበት እና መጠቀም የምትጀምርበት ምርጡ ጊዜህ ነው። በዚህ ጊዜ ልክ እንደጉንዳኖች በበጋው ወቅት ለክረምት የሚሆን ምግብ የምትሰበስብበት አቅም ይኖርሀል።
ውበት ይኖርሀል። የምትፈካበት የምትደምቅበት እና ለብዙዎች የምትታይበት ወቅት ነው። ውበትህ በራሱ የነገህን የምትገነባበት አንደኛው መሳሪያ ሲሆን ያለጊዜው እና ያለቦታው ካዋልከው ነገህን በፀፀት እንድትሞላው ከሚያደርጉህ ከህይወት በረከቶችህ መሀከል አንደኛው ነው።

ሌላኛው እና ዋነኛው ደግሞ አይምሮህ ሲሆን እንድታስብበት እና ከላይ የጠቀስኳቸውን የህይወት በረከቶች እንዴት መጠቀም እንዳለብህ የሚመራህ ነው። አንድ መርከብ የቱንም ያህል ግዙፍ ቢሆን የሚመራው ግን ትንሽ የሆነችው መሪ ናት። አንተም የቱንም ያህል ግዙፍ ብትሆን ሀብት ቢኖርህ ውበት ብታከማች ያለ አይምሮህ የምትኖር ከሆነ ተራ ነው የምትሆነው።

ስለዚህ በጉብዝናህ ጊዜ የተሠጡህን እነዚህን በረከቶች በጊዜው በወጣትነት ትጠብቃቸው እና በአግባቡ ትጠቀምባቸው ዘንድ ምክሬ ነው። መልካም ቀን
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe