Get Mystery Box with random crypto!

አዲስነት የጊዜ ጉዳይ ሳይሆን የራስ ለውጥ ነው አዲስ የሚባለው ነገር ወይ ከመጀመሪያው ያልነበ | ዶ/ር ምህረት ደበበ

አዲስነት የጊዜ ጉዳይ ሳይሆን የራስ ለውጥ ነው

አዲስ የሚባለው ነገር ወይ ከመጀመሪያው ያልነበረ ወይም ደግሞ የነበረው እንደአዲስ ሲታደስ ነው። የጊዜ አዲስ የለውም። ለምን መሠላችሁ ሰዎች በጊዜ ውስጥ ያልፋሉ እንጂ ጊዜ በሰው ውስጥ አያልፍም። ይህ ማለት ጠዋት ስትነሡ ጊዜ ይኖራል። ጊዜ የሚኖረው እኔ ዮናስ እስካለው ብቻ ነው። እኔ ከሞትኩ ጊዜ የሚባል ነገር የለም። ይሄ እውነታ ነው።አንድ ነገር የሚኖረው እናንተ እስካላችሁ ብቻ ነው።
ስለዚህ የጊዜ አዲስ የለውም። አዲስ የሚሆንም ነገር የለም። አዲስ ከሆናችሁ አዲስ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ። እሱንም የሀሳብ ለውጥ ካመጣችሁ ነው። አዲስ የምትሆኑት የትላንታችሁን ስለምትረሱት ሳይሆን በትላንታችሁ ውስጥ መኖር ስታቆሙ ነው። እንዳንዳንዶች አዲስ የሆነ ማንነት ገንቡ ምናምን ብዬ አልሰክስም። ምክንያቱም ምንም ምትገነቡት አዲስ ማንነት ስለሌላችሁ ነው።
ሰው በዉስጡ ያለውን ማንነት ነገሮች ሲስተካከሉ እና ሀሳቡ ሲሻሻል እያስተካከለ ይጠቀመዋል እንጂ አዲስ የሚፈጥረው ምንም አይነት ማንነት የለውም።
ስለዚህ ምንም አዲስ የሚባል አመትም ሆነ ቀን የለም። ይሄ ካልተዋጠልህ ሳትወድ በግድህ በውሀ ታወራርደዋለህ።
አንድን ነገር አዲስ የሚያደርገው ያንተ መኖር ብቻ ነው።
በነገራችን ላይ የእድሜህንም ቁጥር ያወከው ሰዎች በሠጡህ የጊዜ አቆጣጠር ተጠቅመህ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። ከዛም ሰው 80 አመት ሲሞላው የመሞቻ ጊዜው እንደደረሰ ታስብ እና ሞት ሞት ይሸትሀል ከዛም ትሞታለህ።
የገጠር ሠዎችን አይተሀቸው ታውቃለህ እድሜያቸውን አያቁትም ቀኑንም አይቆጥሩም በቃ ዝም ብለው ይኖራሉ። ሚገርመው ቶሎ አለመሞታቸው ነው። ምክንያቱም አያቁማ ሰው በስንት እድሜው እንደሚሞት። ስለዚህ አያስቡም። አንተ ግን ትቆጥራለህ የቆጠርካት ላይም ከአፈር ትቀላቀላለህ።
ስለዚህ ባትጃጃሉ መልካም። በተቻላችሁ መጠን አዲስ ዘመን ስለመጣ እቅድ አታውጡ ይሄ በአል እረፈስኪያልፍ እቅድ አታውጡ። ጊዜው ይለፍ ከዛም ታወጣላችሁ። መልካም ቀን እወዳችሁዋለው
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe