Get Mystery Box with random crypto!

ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወን | ዶ/ር ምህረት ደበበ

ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ ከወንዙ በወድያኛው ዳር ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።

ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ
ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምመሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?" አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?" በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም። ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን፡፡
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe