Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ምህረት ደበበ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mihret_debebe — ዶ/ር ምህረት ደበበ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mihret_debebe — ዶ/ር ምህረት ደበበ
የሰርጥ አድራሻ: @mihret_debebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.49K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ሀሳቦች ይነሳሉ፡፡
✔የሳይኮሎጂ ምክር
✔አጫጭር ታሪኮች
✔የታዋቂ ሰዎች አጫጭር አባባሎች
<<...ካመለጠ ትናንት ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል።...>>

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-01 17:14:23 ለሠው የምትሠጠው ትልቁ ስጦታ


በዘመንህ እንደዚህ እመን ፈጣሪ በጣም ከወደደህ ሰው ይሠጥሀል። ሰው ደግሞ እራሱን ይሠጥሀል። እራስን መስጠት ማለት ምን መሠላችሁ ፦ አንድን ሰው ስትወዱት የኔ የምትሉት ምንም ነገር ሳይኖር እራሳችሁን ሳትሠስቱ ትሰጡታላችሁ። አለምን የሠራት ፈጣሪ የሠው ልጆች ሁሉ በሀጥያት ሲበላሹ ዝም አላለም እራሱን በሠው አምሳል ገልጦ ክብሬን ምናምን ሳይል ወደ ምድር መጣ። ክብሩን ተወው። አየህ ለምትወደው ሰው የምትደብቀው ክብር የለህም። በምትወደው እና በሚወድህ ሰው መካከል ግንኙነታችሁ እራቁት መሆን መቻል አለበት። እራቁት የሆነ ነገረ አይደበቅም ሁሉም ነገሩ ይታያል። የህይወትህን የሆነ ክፍል እየደበክ ፍቅረኛህን ወይም ፍቅረኛሽን አፈቅረዋለው ወይም አፈቅራታለው ብትል የውሸት ነው።

ለምትወደው ሠው የምትሠጠው ስጦታ ራስን ከሆነ ይሄ ነገር በእራቁትነት ይገለጣል። አብሶ ለፍቅረኛሞች እና ለባለትዳሮች የምመክራችሁ ትልቁ ምክር ይሄ ነው ፦ በምትወዱት እና በምታፈቅሩት ሰው መሀከል የኔ የምትሉት ነገር እንዳይኖራችሁ። ታድያ ይሄ ነገር መሆን ያለበት በአንድ ሠው በኩል ባለ መዋደድ ብቻ ሳይሆን በሁለቱም አካላት መሀከል ባለው መዋደድ ላይ ይመሠረታል።

ፍቅር ማለት እራቁትነት ነው። ህፃን ልጅ እራቁቱን ሲሆን የሚደብቀው አካል የለውም። የሚገርመው ያ ህፃን ነፃነቱን የሚያገኘው እራሱ እራቁቱን ሲሆን ነው። ይሄ ብቻ አይደለም እራቁቱን በመሆኑም አያፍርም። እውነተኛ ፍቅርም ልክ እንደዚሁ ነው። እራቁቱን በመሆኑ ነፃነት ይሠማዋል። የኔ የምትሉት ሚስጥር አይኑራችሁ። አትደባበቁ።

ትልቁን ስጦታችሁን ለምተሰወዱት ሰው ስጡ። እራቁታችሁን ሁኑ። እወዳችሁዋለው መልካም ቀን ይሁንላችሁ
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.2K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-01 17:14:23
በቅንነት ሼር ያድርጉ

"ሰው ማለት እኮ የትዝታውና የትውስታው ድምር ነው። ሕይወት የመርሳትና የማስታወስ ሚዛን
ናት። መርሳት ያለብንን መርሳት ሲያቅተን ሕይወታችን ይመሳቀላል... ደግሞ ማስታወስ ያለብንን
የሕይወት ልምዶች ጠቃሚ ሰዎችና ነገሮች ከረሳን ...የእኛነታችን መለያና የስብእናችን ድንበር
ይጠፋና ሌላ ሰው እንሆናለን።" ከሌላሰው መፅሃፍ ገፅ 285 የተወሰደ።

@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.1K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 01:26:33
በአንድ ወቅት አንዱ ስብሐትን ይጠጋውና

"ጋሽ ስብሐት ጽሁፎችህ ተወዳጅነት አላቸው። በተለይ ወጣቶች በብዛት ያደንቁሃል። ለምን መጽሀፍትህን ሁሉም በነፃ የሚያገኙበትን መንገድ አናመቻችም?"

ስብሐት "በጣም ደስ ይለኛል"

ልጁ ደስታውን ከፊቱ ላይ ለመደበቅ እየታገለ፦

"በቃ ስራዎችህ የህዝብ እንዲሆኑ የሚያስፈልገውን የህግ ሰነድ አርቅቄ እመጣለሁ"

ከጥቂት ቀናት በኋላ ልጁ ከሰነዱ ጋር ወደ ስብሐት መጣ። ስብሐት ሰነዱን ተቀብሎ በሚገባ አነበብ። ሃሳቡ ሲጨመቅ ስብሐት የፃፋቸውን ሁሉም ልብወለዶች እንዲሁም ለዘመናት የከተባቸው እልፍ መጣጥፎች ባለቤትነት በፍቃዱ ለአንድ አሳታሚ ድርጅት ማስተላለፉን ይገልፃል። ልጁ የአሳታሚ ድርጅቱ ባለቤት ነው። ስብሐት በሰነዱ ላይ ያሉትን ሁሉንም መጠይቆች ሞላ። ስም አድራሻ የመሳሰሉትን። በዚህ መሐል ልጁ ምራቁ እየተዝረበረበ ነው። በአእምሮው ምንም ሳይሰራ የሚያገኘውን ገንዘብ እያሰላ ነው። ይህንን ከሰማይ የወረደለትን መና እየቆጠረ ነው። ከሰከንዶች በኋላ ያልለፋበት ብዙ ሺህ ብር ኪሱ ይገባል። ስብሐት በተረጋጋ ስሜት ሁሉንም መረጃ ሲያስገባ ከቆየ በኋላ ልክ የፊርማው ቦታ ሲደርስ ይህንን በአማርኛ ፃፈ፦

"FUCK YOU"




2.1K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 22:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 00:54:21
ብንስማማስ ???!!!

እንዲህ የሚል ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ የአይሁዳውያን ተረት አለ፡-

አንዲት በጣም የተራበች ድመት ከአንድ ሱቅ ስጋ ሰረቀች፡፡ ያንን ሌብነቷን የተመለከተ አንድ ውሻ ነበረና እኩል ካላካፈልሽኝ አጋልጥሻለሁ አላት፡፡ ድመቷ መካፈል ስላልፈለገች መጣላት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ በነበራቸው ጸብ ማንም ማሸነፍ ስላልቻለና ጸቡ ማቆሚያ ስላጣ የስጋው ሽታ ስቧት የመጣች በአካባቢው የነበረችን አንዲት ቀበሮ ጠሩና እንድትዳናኛቸው ጠየቋት፡፡

ቀበሮዋ፣ “ከምትጣሉ ስጋውን እኩል ተካፈሉ” የሚልን ቀላል ምክር ለገሰቻቸው፡፡ በምክሩ ሁለቱም በመስማማታቸው ድመት ስጋውን ለሁለት ቆርጣ ለውሻ አካፈለች፡፡ ሆኖም ውሻው፣ የተሰጠው ድርሻ አናሳ እንደሆነ በማሰብ ጸቡን አላበርድ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ቀበሮ የስጋውን መጠን በማስተካከል ሰበብ ከድመት ድርሻ ላይ ደህና አድርጎ በመቦጨቅ ዋጥ በማድረግ ውሻን አስደሰተና ለማስተካከል ሞከረ፡፡

አሁን ደግሞ ድመት የእሷ በመቀነሱ ምክንያት፣ “የውሻ ድርሻ በዝቷል” በማለት ጸቡን አላበርድ አለች፡፡ አሁንም ቀበሮ ድመትን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ከውሻው ድርሻ ላይ ጠቀም ያለ መጠን ቦጨቅ በማድረግ ዋጥ አደረገ፡፡ አሁን ደግሞ ውሻ እንደገና የእሱ ማነሱን ሲያይ የድመት በዝቷል፣ ከዚያም ቀበሮ ድርጊቱን ሲደጋግም ድመት ደግሞ የውሻ በዝቷል ሲባባሉ፣ ቀበሮ ከዚህም ከዚያም ሲቀናንስ ስጋውን ጨረሰውና ድመትና ውሻ ምንም ሳይደርሳቸው ባዶ ቀሩ ይባላል፡፡

ተጣልተን ሁሉን ከምናጣ ተስማምተን ግማሽ ማግኘቱና አብሮ መኖሩ አይሻለንም?
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.1K views🇦 🇸 🇭 🇹 🇦, 21:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-24 21:26:50 አለቅነት ወይስ አገልጋይነት?

ለመሪዎች . . .

የአንዲት አነስተኛ ከተማ ከንቲባ በአካባቢው በነበረ አንድ ጉባኤ ከተሳተፉ በኋላ በነበረው የምሳ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ የተዘጋጀው የዶሮ ምሳ በሰው ቁጥር ልክ በመሆኑ ከአንድ ዶሮ በላይ መውሰድ አይቻልም ነበረና ምሳ ጨላፊዋ ለእያንዳንዱ ተጋባዥ አንድ አንድ ዶሮ በመጨለፍ በየሳህኑ ላይ ታደርጋለች፡፡

ከንቲባው፣ “ተጨማሪ ዶሮ ሳህኔ ላይ አድርጊ” አሏት፣ ኮራ በማለት፡፡ አስተናጋጇም፣ “ይቅርታ፣ ለአንድ ሰው አንድ ዶሮ ብቻ ስለተዘጋጀ መውሰድ የሚፈቀደውም ያንንው ብቻ ነው” አለቻቸው፣ በትህትና፡፡ ከንቲባው ደጋግመው ፍላጎታቸውን ትእዛዝና ጥያቄ በተቀላቀለበት ድምጽ ቢነግሯትም እሷ ግን ደጋግማ ያንኑ መልስ ነገረቻቸው፡፡

በመጨረሻም፣ “ለመሆኑ ማን እንደሆንኩኝ ታውቂያለሽ? የዚህ አካባቢ አለቃ እኮ ነኝ” አሏት፣ አሁንም ኮራ ባለ ድምጽ፡፡ ምግብ አቅራቢዋም የነበራትን አክብሮትና ትህትና ሳትለቅ፣ “ልክ ነው፣ እርሶ የዚህች ከተማ አለቃ ነዎት፣ እኔ ደግሞ የዚህ የዶሮ ምሳ ዝግጅትና አቅርቦት ባለአደራ ነኝ፡፡ ስለዚህ የሚፈቀደው አንድ ነው” አለቻቸው፡፡

ከንቲባው ከዚህ በፊት በነበራቸው “የአገልጋይነት አመራር” (Servant Leadership) ስልጠና ላይ የሰሟቸውና እስካሁን ብዙም ያልተጠቀሙባቸው መርሆች ትዝ አላቸውና ዝም አሉ፡፡

ከመርሆቹ ዋና ዋናዎቹ እነዚህ ነበሩ፡-

1. አገልጋይ መሪ (Servant Leader) ከራሱ በፊት የሚመራውን ሕዝብ ያስቀድማል፡፡

2. አገልጋይ መሪ (Servant Leader) ስልጣኑን በሄደበት ሁሉ ካለአግባብ አይጠቀምም፡፡

3. አገልጋይ መሪ (Servant Leader) ባለው ስልጣን ተጠቅሞ ከሕግ በላይ ለመሆን አይሞክርም፡፡

Leadership or servitude?

For leaders. . .

The mayor of a small town is attending a luncheon after attending a local congregation. The prepared chicken lunch was so large that no one could take more than one chicken, and the chef would chop one chicken for each guest and put it on each plate.

"Put more chicken on my plate," the mayor said proudly. The hostess said politely, "Sorry, only one chicken is prepared for one, and that's the only one allowed." The mayor repeatedly told her in a mixed voice, but she kept telling him the same thing over and over again.

Finally, he said, “Do you know who I am? I'm the boss of this area, ”she said proudly. The waiter did not lose her respect and humility, saying, “That's right, you are the mayor of this city, and I am in charge of the preparation and delivery of this chicken lunch. So one thing is allowed. ”

The mayor remembered the principles he had heard in his previous "Servant Leadership" training, which he had not yet used, and remained silent.

Here are some of the key points:

1. The Servant Leader puts the people before him.

2. The Servant Leader does not abuse his authority wherever he goes.

3. Servant Leader does not use his authority to try to be above the law.

Leaders fall - Have a good server leadership era!

መሪዎች፡- መልካም የአገልጋይ መሪነት ዘመን ይሁንላችሁ!
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
2.1K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-24 21:26:27 መገፋትን ለጥቅም ማዋል!
(“የመገፋት ሕመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

በጓደኝነት፣ በቤተሰብ፣ በፍቅር ግንኑነትና በመሳሰሉት ማሕበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ የመገፋትን፣ የመገለልንና ያለመፈለግን ልምምድ በምትቀምስበት ጊዜ የሁኔታውን መልካም ጎን ለማየትና ወደፊት ለመዝለቅ የሚከተሉትን ሃሳቦች እንደመነሻ መጠቀም ትችላለህ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መገፋትህ ከእነዚያ ከሚገፉህ አላስፈላጊ ሰዎችና ሁኔታዎች የምትለይበትና የምትጠቀምበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ አንዱ ሰው ስለገፋህ ሌላ የተሻለ ሰው፣ አንዱ ተቋም ስላገለለህ ሌላ የተሻለ ተቋም . . . የምታገኝበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማስታወስ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ በመገፋት ውስጥ በተደጋጋሚ ስታልፍ ምናልባት ካለአግባብ የምትገፋበት አጉል ባህሪይ ሊኖርህ ስሚችል ራስህን እንድትጠይቅና ያንን አጉል ባህሪይ ለመለወጥ የምትችልበትን መንገድ መጀመር፡፡

አዎን! የመገፋትን ልምምድ ወደመልካም መለወጥ ይቻላል!
@mihret_debebe
@mihret_debebe
@mihret_debebe
1.9K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ