Get Mystery Box with random crypto!

For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

የቴሌግራም ቻናል አርማ mesehaftrka — For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books F
የቴሌግራም ቻናል አርማ mesehaftrka — For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books
የሰርጥ አድራሻ: @mesehaftrka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 515
የሰርጥ መግለጫ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
በ ቻናላችን የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን እናቀርባለን
✌️ መፀሀፍቶች
📣ትረካዎች
📓አጫጭር ፅሁፎች
🎼የሙዚቃ ግጥሞች🎻
🇪🇹ቀልዶች ግጥሞች 🎊🎊💗💗🎊🎊🎊
Channel created December 2/20
ፅሁፎችን መልቀቅ ከፈለጉ ወይም ለበለጠ መረጃ @fikyt2 ያናግሩን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-14 09:11:45 ለምን???

አየሁት ህመምን የፍቅርን ክፋት
ለሌሎች መድኃኒት ለኔ ሲሆን ጥፋት
ለሌሎቹ ሀሴት ድርብርብ ያለ ፀጋ
ለኔ ግዜ እርግማን የናፍቆት አለንጋ
አየሁ ሌሎችንም....
በውቡ ዋርካ ስር በናፍቆት ሲያወሩ ፊታቸው ይደምቃል፣
የተቀመጡበት ያ የፍቅር ምድር ይባስ ውበቱ ያድጋል፣
እኔም እንደነሱ ደስታን ለማግኘት ሄድኩ መላልሼ ፣
ደንዳናውን ልቤን በፍቅር ላርሰው ቅንጣቱን ቀምሼ፣
ግና......
ብፀልይ ብሞክር ለኔ ካላደለው ልፋት ምን ያደርጋል፣
ጥንዶቹ ያስዋቡት ያ ለምለሙ ቦታ
ገና እግሬ ሲረግጠው የኔ ግዜ ይደርቃል።
#kidist
133 views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 16:55:38 የእግዜር ታናሽ እህት
።።።።።።።።።።።።።።
(ማዕዶት ያየህ)

እንዳለመታደል፣
ሽቅብ እንደመውደቅ፣ወደ ሰማይ ገደል፣
ዘንበል ወደ እግዜር ጣት፣
በማግኘት ፍስሀ ፣ማጣትን ለማጣት፣
ሰው በመሆን እቶን፣ቀን ሌት ከመቀጣት፣
መሆን ያሰኘኛል ፣
የ'ግዜር ታናሽ እህት የቀሚሱ አጣቢ፣
ከስሩ ተቀምጣ ፣
ተረት የሚነግራት፣የፍቅሩ ቃል ጠቢ።
የአምላክ ተላላኪ፣
ብር ብዬ ሄጄ፣ብር ብዬ መምጣት፣
ማዕዱን መካፈል፣ፅዋውን መጠጣት።
ሆዱን ለሚፈጀው፣ሰው አርጎ መስራቱ፣
ላይቀር በእንጨት መሳት፣ከገነት መውጣቱ፣
እኔም ከምፀፀት፣እሱም ከሚያዝንብኝ፣
በእስትንፋስ ቡራኬው፣ግብሩን ቢልክብኝ።

(@Tizur_12)

29/09/2014 ዓ.ም.
154 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 16:54:24 ጥብቅ ማሳሰቢያ
..............................

ሸክላን ለምትሰሩ ከዚያ መቃብር ላይ
አፈር አትዝገኑ
ሲነድ ሲቃጠል፣ ሲጨስ በመኖሩ
ሲቃጠል ለሚኖር፣ ለጀበና መስሪያ
አይሆንም አፈሩ።
138 views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 16:49:41 #እባክን_ትዝታ
:
:
ትዝታን ሚያሸንፍ ትዝታን ሚበግር፤
ትዝታን ሚቀጣ ትዝታን የሚያስር፤
አንዳች በጠፋበት እስከዛሬ ደርሶ፤
በትካዜ ማንኪያ ያልጨለፈ አይኖርም ትናንትን መልሶ።
:
:
ትዝታ ረቂቅ ነው የዃሊት ይሰዳል፤
አንዳንዱን ያስቃል አንዳንዱን ያነዳል።
:
:
በሰመመን መንገድ የሰመመን ጉዞ፤
ሁለት አይነት ስሜት ሳቅና እምባን ይዞ።
:
:
እንዲ ነው ትዝታ እንዲ ነው ሰው ማሰብ፤
ትናንትን አስታውሶ ወይ መርገፍ ወይ ማበብ።
:
:
እናም እኔ ዛሬ...
ለማይቀረው እዳ ለዚ ለትዝታ፤
ተማፅኜዋለው ይውልልኝ እንደው ይህንን ውለታ።
:
:
ያሳብ ጀልባን ቀዝፈ፤
ሰመመንን ነድፈ፤
ልትውስደኝ ስትመጣ ካሳለፍኩት ማዶ፤
እንዳልብሰለሰል ውስጤ በግኖ ነዶ፤
መልካም ብቻ አሳየኝ መልካም የሆነን ሁሉ፤
እባክን ትዝታ እባክን አያሉ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
208 views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 22:32:01 በህልሞቼ ታዛ
ስር በመኖርህ አንተ
ሴትነቴ ሁሉ
በፍቅርህ ማደሪያ ስለተከተተ፣
ከእኔ እየቀደመ
አመት ነው እሚያረጅ
ዘመነ ነው የባተተ።
206 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 22:30:56 ንገሪኝ ካልከኝስ

ደረቅ፣ግትር፣ጨካኝ ልብ የለሽም አልከኝ
ድንጋይ መሆኔንም በሰዉ አስነገርከኝ
አዎ ነኝ ይግረምህ
እረግጠሀኝ ብትሄድ ምትህ እንዳይገባኝ
አንስተህ ብትጥለኝ ዉስጤን እንዳትጎዳኝ
በሚያማምር ቃላት ልቤን አረስርሰህ
ደርሰህ እንዳታደማኝ
በጥርስህ እየሳክ ልቤን እንዳትወጋኝ
አይዞሽ አይዞሽ ብለህ ሂጅ ጥፊ እንዳትለኝ
ወደድኩሽ እያልከኝ ፍቅሬን እንዳትቀማኝ
ድረሺልኝ ብለህ አልይሽ እንዳትል
በሳቅህ እኔም ስቄ
በደስታህ ቦርቄ
ሲከፋህ አልቅሼ
ስታዝን ሳይ ደሞ ማቅ አመድ ለብሼ
ስኖር እኖርና.................
ድንገት ብትቀየር
ሳቄ ጣዕሙን ያጣል
ሀዘኔ ያስቃል
ደስታዬ ያስለቅሳል
ለቅሶዬ የደስታ መገለጫ ይሆናል
እና በአጠቃላይ ትርጉሜ ይጠፋል
እናምልህ ስማኝ
እህ ብለህ አድምጠኝ
ይህ ዝርክርክ ልቤን በደምብ ስለማቀዉ
ለዛ ነዉ ደንድኜ በሩን የማልከፍተዉ
አንዳንድ ልጆች አሉ
አንኳክተዉ መሮጥን ጀግንነት ያስባሉ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
196 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 06:50:17 ባገኘውሽ ቁጥር........ናፍቀሽኛል ስልሽ
ናፍቆትሽን እንጂ አንቺን እንዳይመስልሽ

አንቺዬ
መናፈቅ መና'ፈቅ ብርቅ ሆኗል በኔ ቤት
እራቂኝ ልወቀው የናፍቆትን ስሜት
መውደድ እንደዚህ ነው በኔ ሂሳብ ስሌት።

አዎ......
ልራቅሽ................እራቂኝ
ደግሞ እንዲ ስልሽ ለሰው እዳታሚኝ

አልገባሸም ይሁን
ፍቅር ያለ ናፍቆት ባዶነት በድን ነው
ናፍቀሽኛል ልበል ብትናፍቂኝ ምነው?

አንቺዬ
ልሂድ ልሽሽ በቃ ናፍቄሽ እንድታይ
ከምድር ልቦናሽ ልራቅ እንደ ሰማይ
ናፍቆት ብዬ ባልኩት ዘላለም ልሰቃይ።

በረከት
244 views03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 13:03:10 አንቺ የኔ አለም
የፊትሽ ወዝ ጠፍቶ
ሀዘንሽ በርትቶ
አንቺን ሲያሸንፍሽ
እህህህ እንደማለት
በጥርስሽ አሸነፍሽ።

አይንሽ ደም ቢመስልም
ከንፈርሽም ቢደርቁ
ጥርስሽ እያበራ ሀዘንሽን ደበቁ

ኑሪልኝ እንድኖርልሽ!

ዮኒ
ኣታን
231 views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 09:05:20 #የለም
:
:
ከተቸረኝ ገላ አካሌ ላይ ካሉት፣
እንቅጩን ልናገር አሁን ቆይ ማን ይሙት፣
ከስሜት ህዋሴ ምረጥ ብባል እንደው፣
ልክ እንደ ብሌኔ ይኖር የምወደው?
የለም
214 views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 18:23:24 የፍቅር መድረሻው!
(አኑ)

ሂድ ስትለው መጣ፣
ውረድ ሲባል ወጣ፣
ውጣ ሲባል ሲወርድ፣
አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣
ከራሱ ተጣልቶ፣
ከራሱ ተኳርፎ፣
ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ

(ያቺ ሴት)

የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች
በፍቅሩ የከነፈች፣
ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት!
እሱም የሚያፈቅራት
ከጎና ማይጠፋ
ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት!
አንድ'ዜ በሀይቅ
አንድ'ዜ በየብሱ
አንድ'ዜ በአየር
ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር።

(ዛሬ)

ተጣልተው
ተኳርፈው
ደግሞም ተለያየተው
አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው
ጎጆውን አፍርሰው
ተነጣጥለው አሉ
ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ።

(እሱ)

ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ
ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ
( ሁለት ነው ያዘዘው)
አንደኛው ለራሱ
ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ
እርግጥ ነው የለችም
በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ
(እንዲኽ ነው ሀሳቡ)

ትዕዛዙ እስኪመጣ
ጋዜጣ ያነባል
የጋዜጣው ርዕስ
ጥያቄ ይጠይቃል

(ጥያቄው)
ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል?
ከርዕሱ በታች
የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣

(እዚህ ጋር)

ቄሱም ሆነ ሼኹ
የፃፉትን ፅህፈት፣
የሰበኩት ስብከት፣
ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት!

(እውነቱ)

የቄሱም የሼኹም
የኣላህም የእግዜሩም
ቃሎች ሲመረመር
ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል
ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል)

ሳይጠጣው ተነሳ
ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ
ሚጓዝበት መንገድ
ማይሽር ፣ የማይጠፋ
ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ።
እርምጃው ፈጠነ
ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል
ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣
በሯን ደበደበ፣
እየሮጠች ወጣች፣
የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል
የምትለው ጠፋት
ፍርሀት ነብሷን ዋጣት


ሱ...

ተንበርክኳል
እግሯ ስር ተገኝቷል
በስስት ፣ በፍቅር
ሽቅብ አይኗን ያያል
ይቅርታ የሚል ቃል
ከአንደበቱ ይፈልቃል




አለቀሰች
አይኗን እንባ ወረሰው፣
አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣

ተነሳ አቀፈቹ
ሲያያት ሳመቹ









አለች
እየሳቀች

ጋዜጣውን አየ

ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣

ይኽን አስታውሶ
ፊቱን ብርሀን ሞላው።
265 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ