Get Mystery Box with random crypto!

ንገሪኝ ካልከኝስ ደረቅ፣ግትር፣ጨካኝ ልብ የለሽም አልከኝ ድንጋይ መሆኔንም በሰዉ አስነገርከኝ አ | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

ንገሪኝ ካልከኝስ

ደረቅ፣ግትር፣ጨካኝ ልብ የለሽም አልከኝ
ድንጋይ መሆኔንም በሰዉ አስነገርከኝ
አዎ ነኝ ይግረምህ
እረግጠሀኝ ብትሄድ ምትህ እንዳይገባኝ
አንስተህ ብትጥለኝ ዉስጤን እንዳትጎዳኝ
በሚያማምር ቃላት ልቤን አረስርሰህ
ደርሰህ እንዳታደማኝ
በጥርስህ እየሳክ ልቤን እንዳትወጋኝ
አይዞሽ አይዞሽ ብለህ ሂጅ ጥፊ እንዳትለኝ
ወደድኩሽ እያልከኝ ፍቅሬን እንዳትቀማኝ
ድረሺልኝ ብለህ አልይሽ እንዳትል
በሳቅህ እኔም ስቄ
በደስታህ ቦርቄ
ሲከፋህ አልቅሼ
ስታዝን ሳይ ደሞ ማቅ አመድ ለብሼ
ስኖር እኖርና.................
ድንገት ብትቀየር
ሳቄ ጣዕሙን ያጣል
ሀዘኔ ያስቃል
ደስታዬ ያስለቅሳል
ለቅሶዬ የደስታ መገለጫ ይሆናል
እና በአጠቃላይ ትርጉሜ ይጠፋል
እናምልህ ስማኝ
እህ ብለህ አድምጠኝ
ይህ ዝርክርክ ልቤን በደምብ ስለማቀዉ
ለዛ ነዉ ደንድኜ በሩን የማልከፍተዉ
አንዳንድ ልጆች አሉ
አንኳክተዉ መሮጥን ጀግንነት ያስባሉ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ