Get Mystery Box with random crypto!

ለምን??? አየሁት ህመምን የፍቅርን ክፋት ለሌሎች መድኃኒት ለኔ ሲሆን ጥፋት ለሌ | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

ለምን???

አየሁት ህመምን የፍቅርን ክፋት
ለሌሎች መድኃኒት ለኔ ሲሆን ጥፋት
ለሌሎቹ ሀሴት ድርብርብ ያለ ፀጋ
ለኔ ግዜ እርግማን የናፍቆት አለንጋ
አየሁ ሌሎችንም....
በውቡ ዋርካ ስር በናፍቆት ሲያወሩ ፊታቸው ይደምቃል፣
የተቀመጡበት ያ የፍቅር ምድር ይባስ ውበቱ ያድጋል፣
እኔም እንደነሱ ደስታን ለማግኘት ሄድኩ መላልሼ ፣
ደንዳናውን ልቤን በፍቅር ላርሰው ቅንጣቱን ቀምሼ፣
ግና......
ብፀልይ ብሞክር ለኔ ካላደለው ልፋት ምን ያደርጋል፣
ጥንዶቹ ያስዋቡት ያ ለምለሙ ቦታ
ገና እግሬ ሲረግጠው የኔ ግዜ ይደርቃል።
#kidist