Get Mystery Box with random crypto!

..........//አይገልፅሽም\\ ፀሃይን አስውቤ በቃላት አርቅቄ በፅሁ | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

..........//አይገልፅሽም\\

ፀሃይን አስውቤ
በቃላት አርቅቄ በፅሁፍ ገልጫለሁ፤
ጨረቃንም ደግሞ አስውቤ ስያለሁ።
የክዋክብት ውበት ህብረትን አይቼ፤
የደመናን ስእል ለሰማኝ አውግቼ፤
የሰማይን ስፋት በአድማስ ለክቼ፤
የተፈጥሮን ውበት ስገልፅ እንዳልነበር።
ስላንቺ ለመግለፅ በከንቱ ስሞክር፤
በፊደላት ሆሄ በወረቀት በብእር።
አይምሮዬ ቃላት
ጥዑም መግለጫ አጥቶ፤
እጄ ሲሞነጭር
ሲፅፍ እንቶ ፈንቶ።
ለካስ፤ ያፈቀሩትን ሰው
ማናገር አይደለም መግለፅም ይከብዳል፤
ደግሞስ የልብ እውነት
አይምሮ እንዴት ያቃል፤
ልብ ያወቀው ውበት
በምን ይገለፃል፤
ልፅፈው ብሞክር
እንዴትስ ይፃፋል።
ቢፃፍም ልቤ ውስጥ ያለውን
በፍፁም አይመስልም፤
ላልገልፅሽ ሞክሬ
መልክ አላበላሽም፤

ምንም አይነት ጥበብ
ልቤ እንደሳለሽ ሊገልፅሽ አይችልም።

#abela_black