Get Mystery Box with random crypto!

ማዕዶት የመጽሀፍት መደብር Maedot Books Store

የቴሌግራም ቻናል አርማ maedotbooks — ማዕዶት የመጽሀፍት መደብር Maedot Books Store
የቴሌግራም ቻናል አርማ maedotbooks — ማዕዶት የመጽሀፍት መደብር Maedot Books Store
የሰርጥ አድራሻ: @maedotbooks
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 851

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-15 06:39:55
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። (በነጻ)
-----
ልዩ መርሐግብር:- መጽሐፍ የማስፈረም: ከደራስያን ጋር የመተዋወቅና የመጨዋወት ልዩ ሥነስርዓት::

የመጽሐፉ ደራሲ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ:-
ሕይወት እምሻው

የተመረጠው መጽሐፍ:-ማታ ማታ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ እና ዋልያ መጻሕፍት::

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ሚያዝያ 8፡ 2014: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)
497 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 06:37:25
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ ተክለጻድቅ መኩሪያ መጽሐፍ የሆነው " ኑብያ - አክሱም - ዛጉዌ " የተሰኘው የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ ለንባብ በቃ!
402 views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-21 08:02:42
ከጦጣነት በዝግመት ተለውጠን በሁለት እግር ቆምን እንላለን እንጂ ልባችን ገና ካጎበጠበት ሊቃና እንኳን አላሰበም፡፡ እንደ አራዊት መንጋ ሁሉ ኅብረተሰቤ የተገነባው በበላይ እና በበታች ሥርዓት ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ፈጽሞ እኩል ልትሆን አትችልም፡፡ ከላይ መሆን ካልቻልክ ከታች ትገኛለህ ነው፡፡ ይሄን በየቤታችን በአርጩሜና በምላስ አለንጋ ያስተምሩንና ደጅ ስንወጣ የገባርና የጭሰኛ ግንኙነት ይኖረናል፡፡

" መሐረቤን ያያችሁ "
ሙሉጌታ አለባቸው ::
784 viewsedited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-11 11:20:51
የቪክቶር ፍራንክል " Man Search for Meaning " የተሰኘው እጅግ ዝነኛ መጽሐፉ በቴዎድሮስ አጥላው " ለምንን ፍለጋ " በሚል ርዕስ ወዳማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ ::

የሥነ - አእምሮ ሐኪሙ የቪክቶር ፍራንክል ማስታወሻ በናዚ የሞት ካምፖች ውስጥ ስለነበረው ሕይወት እና ለመንፈሳዊ ሕልውና የሚሰጠውን ትምህርት ያሳየናል ::

ፍራንክል ኦሽዊትዝን ጨምሮ በአራት የተለያዩ ካምፖች ውስጥ ለረጅም ጊዜያት ታስሯል :: ወላጆቹ ፣ ወንድሙ እና ነፍሰ ጡር ሚስቱ ኢ - ሰብአዊ ድርጊት በሚፈጸምባቸው የናዚ ካምፖች ውስጥ ህይወታቸው አልፏል።

ከራሱ ልምድ እና በኋላ ባደረጋቸው ሌሎች ጥናቶች ላይ በመመስረት፣ ፍራንክል መከራን ማስወገድ እንደማንችል ነገር ግን ችግሩን እንዴት መቋቋም እንደምንችል መምረጥ እንደምንችል ይከራከራል :: በእሱ ውስጥ ትርጉም ለማግኘት እና አዲስ ዓላማ ይዘን ወደፊት እንራመዳለን።

የፍራንክል እንዳለው " በሕይወታችን ውስጥ ቀዳሚ ፍላጎታችን ደስታ ሳይሆን በግላችን ትርጉም ያለው ሆኖ ያገኘነውን ነገር መፈለግ እና ማግኘት ነው። "

ለማዘዝ

@Yonas_H
849 viewsedited  08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 16:40:45 “የቀዶ ጥገናው ክፍል AC ክፍሉን ለማቀዝቀዝ ይሞክራል። ከፍተኛ የሆነ ፀጥታ በክፍሉ ውስጥ ቢኖርም ለስለስ ያለ የአስቴር ዘፈን በቀስታ ይንቆረቆር ነበር። ብዙ አስቸጋሪ ብለን የለየናቸው የቀዶ ጥገናው ክፍሎች(steps) ቀስ በቀስ ያልፉ ጀመር።

እነሆ በከፍተኛ መመሰጥ ሆነን ስድስት ሰዓታት አለፉ። ሁሉም ነገር በሠላም የሠራን መሰለን። መደሰት ግን አልጀመርንም። ምክንያቱ ደግሞ ሁልጊዜ የዚህ ዓይነቱ ቀዶ ጥገና Bental Procedure ችግሩ ኦፕሬሽኑ ካለቀ በኋላ ደም
መፍሰስን ማቆም የሁልጊዜ ፈተና ስለሆነ ነበር። እናም አለም በደረሰበት የወቅቱ ደረጃ ሁሉንም ጨርሰን እንደተለመደው ከአንድ አስቸጋሪ ቦታ ላይ
በብዛት ደም ሲፈስ ማየት ጀመርን። የፈራነው ደረሰ። ላለመረበሽ እየሞከርን የተቻለንን ያህል ተረጋግተን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጋችንን ቀጠልን። ይሁን እንጂ አልተሳካልንም ነበር፡፡ ይባስ ብሎ ከቦታው የሚፈሰው ደም ከመጨመሩም ባሻገር ይህ ቦታ የቀኝ የልብ የደም ስር ካስገባነው ሰው ሰራሽ የደም ቧንቧ (Artificial Aortic conduit) የሚነሳበት ስለነበር ነው።
በየደቂቃው ልብ ይበልጥ ይጎዳ ጀመር፡፡ አሁን በሁላችንም ላይ መደናገጥ መታየት ጀመረ። ምንም እንኳን ልብና ሳምባን ከማሽን በሰላም አላቀን ወደ ተፈጥሮው ተመልሰን የነበረ ቢሆንም ሁሌም እንደሚደረገው ደም ማፍሰስን
ለማቆም የሚሰራውን ከዚህ በኋላ ልብ እየመታ መሆኑ ነው።
ይሄንን አስቸጋሪ ሁኔታ መቆጣጠር ተሳነን። እናም ቀዶ ጥገናውን ከጀመርን ከ7:00 ሰዓት በኋላ በጠቅላላው ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዝን
አስተዋልኩኝ። መሯሯጥ በዛ፤ እናም የዚህን ወጣት ነብስ ለማዳን አንድ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል ማድረግ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ ቡድኑን አረጋግቼ እቅዴን አንድ በአንድ አስረዳሁ። እናም እንደገና ተመልሰን ልብና ሳንባን አቆምን፡፡ የደም ዝውውርን ለማሽን በድጋሚ ሰጠን፤ እናም አደገኛ ድካም ተሠምቶኝ ስለነበር በዚህች ወሳኝ ሰዓት ራሴን እንዳልስት ብዬ እረፍት ለማድረግ ወሰንኩ፡፡ ልብሴን አወለቅኩ። ከጭንቅላቴ ላይ ሁሉንም መሳርያ አወለቅሁ። ፊቴን ታጥቤ አንድ ብርጭቆ ትኩስ ሻይ ጠጣሁ።

ጥቂት ደቂቃ ካረፍኩ በኋላ ተመልሼ ታጠብኩ፡፡ እንደገና የቀዶ ጥገና ልብሴን ለብሼና መሳሪያዎችን በሙሉ በዓይኔና በጭንቅላተረ ላይ አድርጌ ገባሁ።
እንደገና ልብን ሙሉ ለሙሉ በድን በማድረግ (On Cross Clamp) የሚደማውን ቦታ በእርጋታ መለየት ጀመርን። ቀጥሎ ቀስ በቀስ የቀኝ የደም
ቧንቧን ሳንጎዳ ችግሩን ለመፍታት ሞከርን። ጥሩ ስሜት ተሰማን፡፡

አሁንም ቢሆን ግን ቦታው አለመድማቱን ማረጋገጥ የሚቻለው ልብ መምታት
ሲጀምርና ከማሽን ስናላቅቅ ብቻ ነው። ሁላችንም በልባችን እየፀለይን ለሁለተኛ ጊዜ በፕሮቶኮሉ መሠረት ልብና ሳንባን ከማሽን አላቀቅን ቦታውን
በጥንቃቄ መመርመር ተያያዝን። የድል ብስራት ስሜት ወረረኝ። ልብ ተመችቶት ይመታል፤ ሳንባም በጥሩ ሁኔታ ኦክስጅን ያቀብላል፤ የምናያቸው መስፈርቶች በሙሉ ፅድት ያሉና የእኛን ልብ በደስታ የሚሞሉ ነበሩ። እነሆ ቢላችንን
ካሳረፍን ከ10:00 ሰዓት በኋላ የወጣቱ ደረት ተዘጋ። ሀሉም ነገር ደስ ይል
ነበር።

ጥሩ እንቅልፍ ተኛሁ መሰል ጠዋት ትኩስነት ተሰማኝ። ቀጣዩ ቀን እሁድ ነበርና በባዶው የቦሌ መንገድ በርሬ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ። ምንም እንኳን ሌሊቱን አለመደወሉ የሚነግረኝ ጥሩ ምልክት ቢኖርም በአካል ሄጄ ይህን የ27 ዓመት
ወጣት እስካየሁ ጓጓሁ፤ በቦታው ስደርስ ከማሽን ventilator ተላቋል፤ በራሱ ይተነፍሳል፤ ምንም ደም አልፈሰሰውም። ደስ አለኝ። ነገር ግን አዕምሮው ሙሉ በሙሉ ጥርት አላለም ነበር፡፡

በዚያኑ ቀን ሁለት ሦስቴ እየተመላለስኩኝ አየሁት። ሰኞ ጠዋት እንደዚሁ በጉጉት መጥቼ ሳየው ደስ የሚል ፈገግታ እያሳየኝ እንዲህ ሲል ጠየቀኝ "
ሠራኽው አይደል" አለኝ እኔም አዎን ሁሉም መልካም ነው አልኩት "ጀግናዬ ነህ" አለኝ፡፡

እናም ሁለት ቀን ሙሉ ያጣሁትን ደስታ አሁን ግልብጥ ብሎ መጣ። የደስታ ጎርፍ አጥለቀለቀኝ ሁሉም ነገር አበቃ። አይደለም አንድ አስር ሞት መጥቶ ቢወስደኝ እኔ ጣጣ አለኝ?ቀዶ ጥገናውን በሰራን በዓመቱ ከሚኖርባት የገጠር ከተማ በጓሮው ያበቀለውን ሽንኩርት በማዳበርያ ጭኖ አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ አበረከተልኝ።”

የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ:_ በ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር


ከመፅሐፉ ትንሽ ለቅምሻ
መልካም የንባብ ጊዜ
826 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 16:40:07
622 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 17:40:57
661 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 17:40:49 " ያ ትውልድ ቅጽ ሶስት " ለንባብ በቃ ::

የኢሕአፓ መስራችና ከታጋዮቹ መካከል ለምስክርነት በሕይወት ካሉት ጥቂት ታጋዮች አንዱ የሆነው ክፍሉ ታደሰ የጻፈው " ያ - ትውልድ ቅጽ ሶስት " የተሰኘው መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ ::

መጽሐፉ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ሲሆን በተለይ ስለኢሕአፓ ምስረታና አባላት በሰፊው የሚተነትንና የሚታትት የያትውልድ ሰነድ ነው ::

መጽሐፉ በ1960 ዎቹ በኢትዮጵያ ጉልህ ድርሻ ከነበራቸው ቀደምት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሐል አንዱና ዋነኛው ስለነበረው ' ኢሕአፓ ' የሚያትት ውድ ሰነድ ነው ::

መጽሐፉ የተጻፈው የኢሕአፓ ፓርቲ መስራችና ከታጋዮቹ መካከል ለምስክርነት በሕይወት ካሉት ጥቂት ታጋዮች አንዱ የሆነው ክፍሉ ታደሰ ነው ::

መጽሐፉ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ሲሆን በተለይ ስለኢሕአፓ ምስረታና አባላት በሰፊው የሚተነትንና የሚታትት ሰነድ ነው ::


መጽሐፉ በመደብራችን እየተሸጠ ነው ::

ለማዘዝ 0970514616
650 viewsedited  14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-02 08:51:46
የሐሽማል መጽሐፍ ደራሲ የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ሊቀ ጠበብት ማዕበል ፈጠነ አሁን ደግሞ በሌላኛው ስራቸው "ከርታታ ኮከቦች" መጥተዋል መልካም ንባብ ይሆንላችሁ ዘንድ ተመኘን።

ሐሽማል ከመሆናቸው በፊት የተዋነይን ውኃ መጠጣት ነበረባቸው። ሁለቱ ተማሪዎች ከውኃዋ ከተጎነጩ በኋላ ሊቁ ፋሬስ አንድ ታሪክ መዘዙ።
"እኔና ቀለሙ ተፈሪ ይችን ውኃ የጠጣን ቀን ደስታው ሊያሳብደን ደርሶ ነበር። ቀለሙ ከወሎ ሲመጣ ገና ብላቴና ነበር። ኪነ ጥበብ ከሚባል ብስል ተማሪ ጋር መጥቶ የተዋነይን የቅኔ መንገድ ቀጸለ። ከዚያ በፊት የዋድላውን የቅኔ መንገድ በደንብ ያውቀዋል። የኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መባቻ ቅዳሜ ቀን በባተበት የዓመቱ መጨረሻ ቅዳሜ ቀን ከውኃዋ አብረን ጠጣን። ክስተቷ በዚያ ቀን ነበር። ከዚያ በፊት ያችን የምሥጢር ቀን ስንጠብቅ ዓመታትን አሳልፈናል። ደጅ ጥናታችን የወግ አልነበረም። ሕይወትን ፍለጋ እንደእኛ የተንከራተተ የለም። ከርታታ ኮከቦች ነበርን። ከመጽሐፉ የተወሰደ።

ርዕስ ከርታታ ኮከቦች
ደራሲ ማዕበል ፈጠነ
የገፅ ብዛት 443
ዋጋ 233 ብር

ለማዘዝ

+251970514616
799 viewsedited  05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 11:33:18
" መንገደኛ የተሰኘውን መጽሐፍ አንብቤ ተደንቄአለሁ፡፡ መጽሐፉ የጥልቅ ጥናት ውጤት ከመሆኑ ባሻገር በተዋበ ግልፅ ቋንቋ የቀረበ እጅግ አስፈላጊ ስራ ነው፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስለሚሰደዱ ሰዎች የደቡብ አፍሪካ ዜጋ ያልሆነ ሰው ምርምርና ጥናት አድርጎ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡ መጽሐፉ የስደተኞቹን ቅድመ-ስደት ሕይወት ይዳስሳል፤ ከደቡብ አፍሪካ ደርሰው የሚጋፈጧቸውን የኑሮ ተግዳሮቶችም ወለል አድርጎ ያሳያል፡፡ ከዚያም አልፎ የደቡባዊ አፍሪካ አገሮችን የፖለቲካና ማሕበራዊ ጭብጦችን ይነካካል፡፡ ወደፊት የስደት ጉዳይን በተመለከተ ሊደረግ የሚገባውን የጥናት አቅጣጫም ይጠቁማል፡፡ "

ዶክተር ጌታቸው ተድላ፤ የገጠር ልማት ባለሙያና ደራሲ

ለማዘዝ @Yonas_H
832 viewsedited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ