Get Mystery Box with random crypto!

ከጦጣነት በዝግመት ተለውጠን በሁለት እግር ቆምን እንላለን እንጂ ልባችን ገና ካጎበጠበት ሊቃና እን | ማዕዶት የመጽሀፍት መደብር Maedot Books Store

ከጦጣነት በዝግመት ተለውጠን በሁለት እግር ቆምን እንላለን እንጂ ልባችን ገና ካጎበጠበት ሊቃና እንኳን አላሰበም፡፡ እንደ አራዊት መንጋ ሁሉ ኅብረተሰቤ የተገነባው በበላይ እና በበታች ሥርዓት ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ፈጽሞ እኩል ልትሆን አትችልም፡፡ ከላይ መሆን ካልቻልክ ከታች ትገኛለህ ነው፡፡ ይሄን በየቤታችን በአርጩሜና በምላስ አለንጋ ያስተምሩንና ደጅ ስንወጣ የገባርና የጭሰኛ ግንኙነት ይኖረናል፡፡

" መሐረቤን ያያችሁ "
ሙሉጌታ አለባቸው ::