Get Mystery Box with random crypto!

የሐሽማል መጽሐፍ ደራሲ የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ሊቀ ጠበብት ማዕበል ፈጠነ አሁን ደግሞ በሌላኛው ስራቸ | ማዕዶት የመጽሀፍት መደብር Maedot Books Store

የሐሽማል መጽሐፍ ደራሲ የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ሊቀ ጠበብት ማዕበል ፈጠነ አሁን ደግሞ በሌላኛው ስራቸው "ከርታታ ኮከቦች" መጥተዋል መልካም ንባብ ይሆንላችሁ ዘንድ ተመኘን።

ሐሽማል ከመሆናቸው በፊት የተዋነይን ውኃ መጠጣት ነበረባቸው። ሁለቱ ተማሪዎች ከውኃዋ ከተጎነጩ በኋላ ሊቁ ፋሬስ አንድ ታሪክ መዘዙ።
"እኔና ቀለሙ ተፈሪ ይችን ውኃ የጠጣን ቀን ደስታው ሊያሳብደን ደርሶ ነበር። ቀለሙ ከወሎ ሲመጣ ገና ብላቴና ነበር። ኪነ ጥበብ ከሚባል ብስል ተማሪ ጋር መጥቶ የተዋነይን የቅኔ መንገድ ቀጸለ። ከዚያ በፊት የዋድላውን የቅኔ መንገድ በደንብ ያውቀዋል። የኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መባቻ ቅዳሜ ቀን በባተበት የዓመቱ መጨረሻ ቅዳሜ ቀን ከውኃዋ አብረን ጠጣን። ክስተቷ በዚያ ቀን ነበር። ከዚያ በፊት ያችን የምሥጢር ቀን ስንጠብቅ ዓመታትን አሳልፈናል። ደጅ ጥናታችን የወግ አልነበረም። ሕይወትን ፍለጋ እንደእኛ የተንከራተተ የለም። ከርታታ ኮከቦች ነበርን። ከመጽሐፉ የተወሰደ።

ርዕስ ከርታታ ኮከቦች
ደራሲ ማዕበል ፈጠነ
የገፅ ብዛት 443
ዋጋ 233 ብር

ለማዘዝ

+251970514616