Get Mystery Box with random crypto!

💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

የቴሌግራም ቻናል አርማ love_therapist — 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀
የቴሌግራም ቻናል አርማ love_therapist — 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀
የሰርጥ አድራሻ: @love_therapist
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.29K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ
✅ ጤና
✅ ስነ ልቦና
✅ ቤተሰብ
✅ ጓደኝነት
✅ የፍቅርና ወሲብ ጉዳዮች ላይ እንመካከራለን ።
የግለሰብ ችግር የማህበረሰብ ችግር ነው
የግለሰብ ጥያቄ የማህበረሰብ ጥያቄ ነው
ስለዚህ ጥያቄዎን ይዘው ይምጡና ለብዙሀን መልስ እና ማስተማሪያ ይሁኑ
ለማንኛውም ጥያቄ @therapist_100

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-27 18:07:59 ስትኖር

ጤናህን ጠብቅ

ጤናህ የመጀመሪያዉና ወሳኙ ነገር መሆኑን ተረዳ

የራስህን ልክ እወቅ

የራስህንም ሆነ የሰዎችን ልክ ማወቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰዉ መናገር ካልፈለገ እንዲናር አታስገድደዉ...መሄድ ካልፈለገ 'ለምን አልሄድክም?' ብለህ አትነዛነዝ፡፡

ለራስህ ክብር ስጥ

ሰዎች የምትፈልገዉንና ያልፈለከዉን ነገር ረግጠዉ ሊገቡ ሲሞክሩ አስቁማቸዉ ማንም ይሁኑ ምን በራስህ ላይ እንዲረማመዱ አትፍቀድ ።

ለራስህ እዉነተኛ ሁን

ሰዎችን ለማስደሰት ብለህ ተራራ አትዉጣ ድንጋይ አትቆፍር፡፡ ሰዎች በራሳቸዉ የማይረካ አይነት ባህሪ ሊያንፀባርቁ ስለሚችሉ ጊዜህን አታጥፋ ።

እራስህን ቻል

የራስህን ችግር በራስህ ፍታ፣ ቤትህን አፅዳ፣ ወጪህን በራስህ ሸፍን ብቻህን የምትኖር ከሆነ ምግብ ስራ፡፡ ‘ሚስት ቢኖረኝ እኮ...’የሚለዉን የስንፍና ምልክት አትጠቀም፡፡ ስለሚስት ሳይሆን እራስህን እንዴት ማሻሻል እንዳለብህ ተረዳ ።

ከሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብህ እወቅ

ሃሳብህን በተረጋጋና ስርአት ባለዉ መንገድ ተናገር ፣ ሰዎች ሲያወሩም ማዳመጥን ተማር

እድሎችን ተጠቀም

በወቅቱ ያልተጠቀምክበትን እድል መቼም ልትጠቀምበት አትችልምና ደፈር ብለህ ሃላፊነቶችን ዉሰድ

መዉደድን ተማር

ፍቅር መስጠትንና መቀበልን ተማር ፣ ይህ ልምድ ህይወት እንዳይሰለችህና ለሰዎች የማሰብ ባህሪን ታዳብርበታለህ ።

የሰነፍ አንደኛ አትሁን

በምትሰራዉ ስራ ይብዛም ይነስም ያለህን አቅም አሟጠህ ተጠቀምና ፍሬ አፍራ፡፡ ለራስህ ህይወት ሃላፊነቱን የሚወስደዉ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ መንግስት፣ ሀገር ምናምን እያልክ ዉስጥህ የተቀጣጠለዉን ሃይል አታጥፋዉ፡፡ ዛሬን ተነስተህ ድከም...ነገ ታርፋለህ

ገንዘብን እወቅ

ገንዘብን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብህ ከህይወትህ ልምድ፣ ካጋፈጡህ ችግሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሰዎች ተረዳ ።

ተዝናና

ያለህን ጊዜ በሙሉ በስራና በትምህርት ብቻ ካዋልከዉ አንድ ቀን ምንም ደስ የምትሰኝበትን ትዉስታ ስላላሳለፍክ ይቆጭሃል፡፡ በመጠኑና በልኩ ተዝናና፣ አሪፍ ጊዜ ከቤተሰቦችህ፣ከጓደኞችህ ወዘተ ይኑርህ፡፡ ነገ ለልጆችህ እንዲህ ነበር ብለህ የምታወራዉን አሪፍ ትዝታ ቅረፅ ።

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:39:54 ባዶ ጩኸት

አንድ ተማሪ ሂሳብ አስተማሪው በማስተማር ላይ ሳለች አንድ ትንሽ ስህተት በመሳሳቷ በጣም ሳቀባት ።

እንዴት እንደዚህ አይነት ስህተት ትሳሳቻለሽ አኔ ካንቺ የተሻለ የሂሳብ ቀመሮችን መስራት እንደምችል ታዉቂያለሽ? ሰዎች 'ከባባድ' ናቸዉ የሚሏቸዉን መፃህፍትን ሳይቀር እንዳነበብኩ አልሰማሽም ??”

እያለ ያደረገዉንና ጥግ የደረሰ እዉቀት ባለቤት መሆኑን በድፍረት መናገር ጀመረ ፡፡

አስተማሪዋም ያወራዉን ሁሉ አዳምጣ ከጨረሰች በኋላ እንዲህ አለችዉ “ሂድና ግማሽ ዉሃ በዚህ ኮዳ ይዘህ ና!”ሔዶ ግማሽ ዉሃ አመጣ...ኮዳዉን አንስታ አወዛወዘችውና ፡፡ “ምን ተሰማህ ?” አለችዉ ።

“ የዉሀዉ ድምፅ ይሰማኛል” አላት “ጥሩ! አሁን ደግሞ ይህንን ኮዳ እስከአፉ ድረስ ሞልተኸዉ ና” አለችዉ፡፡ ሄዶ ሞልቶ ሲመጣ ኮዳዉን ተቀብላ ስታወዛዉዘዉ አየና “ አሁን ምንም ድምፅ የለዉም አላት፡፡

እሷም እንዲህ አለችው ...“እዉቀትም እንደዚሁ ነዉ፡፡ በትንሹ ወይም በግማሹ የሚያዉቁ ሰዎች ብዙ ያወራሉ... 'ካልተደመጥኩ! ፣ጆሮ ካልተሰጠኝ' ብለዉ ችግር ይፈጥራሉ...

ነገር ግን ምርጥ ጭንቅላትና የበሰለ እዉቀት ያላቸዉ ባገኙት ነገር ላይ በሙሉ 'እኔ እኔ እኔ!' እያሉ እጃቸዉን አያወጡም፡፡

ማዉራት ሲኖርባቸዉ ብቻ ጥቂት ያወራሉ፡፡ በእዉቀት እስከ ገደፉ የተሞሉ ሰዎች ጩኸት አያበዙም፡፡

ረጋ ያሉ ናቸዉ! ታዋቂዉ ፈላስፋ ፕላቶ እንዳለዉ ‘ ብልህ ሰዎች ማዉራት ያለባቸዉ ሃሳብ ስላለ ብቻ ያወራሉ ሞኞቹ ግን ማዉራት ስላለባቸዉ ያወራሉ ’”
ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.2K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:15:03 ምሬት

ምሬት ሲበዛ ሰዉ መኖር ይደክመዋል፡፡ ፍቅር ሲበዛ ደግሞ መኖር መኖር ያሰኘዋል...ነገን ይናፍቃል፡፡ በዚህ እልህ አስጨራሽ የምድር ኑሮ ይብዛም ይነስም ምሬቶቻችን አያሌ ናቸዉ፡፡

ከእንጀራና ወጥ ጀምሮ እስከ ሃገር ብዙ ነውጦች በልባችን ይከሰታሉ፡፡ ልባችን ብዙ ሲበጠበጥና ማረፍ ሲሳነዉ እዚህም እዚያም እያለ ያስቸግራል...ልብ ማስቸገር ከጀመረ ደግሞ እንደህፀን ልጅ በል ተዉ! ብለን በቀላሉ አንገታዉም፡፡

ልብ አሸባሪ ነዉ...በሚያየዉና በሚሰማዉ እያንዳንዱ ነገር ይሸበራል...ቀን እየገፋ ሲመጣ በህይወት የሚሰለችና ቶሎ የሚመረር ልብ በየቦታዉ እየበዛና፣ እየጨመረ፣ እየፈላ ይመጣል፡፡

የምሬት ዋናዉ መድሃኒት ብዙ ነገሮችን ማሳለፍ ይመስለኛል፡፡ ባየነዉና በሰማነዉ ነገር ሁሉ ልባችን እየተራገመና ደማችን ከፍ እያለ ከሄደ ብዙ የህይወት አቅጣጫችንን ማበላሸት እንጀምራለን፡፡

እራሳችን ያወላገድነዉን ኑሮ ደግሞ ማንም ሊያቃናልን አይችልም፡፡ አንድ ሰዉ እንደተናገረዉ “መንገድ ላይ በሚጮህብህ ዉሻ ላይ ሁሉ ድንጋይህን አትወርውር” እንዳለዉ በያንዳንዱ ቅፅበት ያለንን ማንነት አላፊ አግዳሚዉ ባወራዉ ላይ ሁሉ መሳተፍ እፈልጋለሁ ካልን ትልቅ ኪሳራ ዉስጥ እንገባለን፡፡

እንደኛ እንጀራ ለመብላት ደፋ ቀና በሚል ህዝብ መካከል ምሬቶቻችንን ብንዘረግፈዉ አዉርተን ዝንት አለም አንጨርሰዉም፣ ነገር ግን መልካሙን፣ ተስፋ የሚሰጥበትን፣ ብሩሁን ከዚህ ጨለማ ዉስጥ ሻማችንን አብርተን እንፈልግ!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.2K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:49:41 ነገን...

የነገዉን ማሰብ በራሱ ምንም ክፋት የለዉም፡፡ ነገ መጥፎም ይሁን ደግ ነገን አልሞ መነሳቱ እንከን የማይወጣለት ነገር ነዉ፡፡ በተለይ በኛ ሀገር ባለዉ ነባራዊ የህብረተሰባችን አኗኗርና የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ነገን ማሰብ ያልተለመደ ነዉ፡፡

አሁን ባለሁበት ሁኔታ የምኖር ከሆነ ነገን እንዴት አልፋለሁ ብሎ ማሰብ እግዚአብሄርን እንደማቆስጣት እናየዋን፡፡ አዎ ነገን ሁሉን ለሚችለዉና በእጆቹ ለሰራዉ ፈጣሪ አሳልፈን መስጠት ብልህነት እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ነገን እሱ ስለሚያዉቅ ከኛ መላምት ፍፁም በማይገናኝ መልኩ የእሱ ቸርነት ያስፈልገናል፡፡ ተስፋችንም እሱ ነዉ፡፡

ግን አልመን መነሳታችንና ማቀዳችን አምላክ በሰጠን አእምሮ መጠቀማችን ጥቅሙ እንጂ ጉዳቱ አያመዝንም፡፡ ዛሬ እያየን ያለናቸዉ የራሳችን የህይወት ዉጥንቅጥ እንዳናስተዉል የሚገፋፉን ቢሆንም ወደፊት በተስፋና በሙሉ ቆራጥነት መገስጉ እጅግ ይጠቅመናል፡፡

ነገን ‘የራሱ ጉዳይ!’ ብለን ያገኘናትን የምንበትን ከሆነ፣ ‘ልሙት ልኑር የት አዉቃለዉ?’ ብለን 'ዛሬን ቸባ!' እያልን የምንደልቅና የምናስደልቅ፣ ዛሬን በቀልድና በዝባዝንኬ አሳልፈን ነገን በቁጭት ከመኖር እስኪ ቆፍጠን ብለን ህልማችንን፣ ሃሳባችንን ስጋ አልብሰን ለማየት እንነሳ!

ወሬዉ፣ ቀልዱ፣ ጭፈራዉ ሁሉ ከስራ ሲቀድሙ ይዘዉን ገደል ይከቱናል...አሁንም እየከተቱን እያየን ነዉ፡፡ ምክንያት ለመፍጠር ቅንጣት ያህል ሰበብ ብቻ በሚኖርበት በዚህ ሀገር፣ የግል ህልማችንን ለማነፅ መሄድ እንደቀረ ፋሽን ሊያስመስለን ቢሞክርም በቃ እንነሳ... የሌላዉ አጨብጫቢ ሆኖ መኖር ይበቃናል!

“ፓ እንትናን አየሃት!” እያልን የጎረቤት የሃብት ምጥቀትን እንደቃና ቲቪ ፊልም አሳምረን ከምንተርክ እንኑረዉ...ተራኪ መሆን ያማል፣ መጨረሻዉ አምስት ሳንቲም የሌለዉ ማንነት ይዞ መቅረት ነዉና ዳይ ወደስራ!!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
1.9K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 19:49:31 የህይወት ሩጫ

ህይወት በነብርና በሚዳቆ መካከል እንዳለዉ እልህ አስጨራሽ ሩጫ ናት፡፡ ብዙ ጊዜ ሚዳቆ ሮጣ ታመልጣለች፡፡ ነብር ደርሶ የሚይዛት ከስንት አንዴ ነዉ..

ይሄ ለምን እንደሆነ ታዉቃለህ? ነብር የሚሮጠዉ ‘ለአንድ ምሳ!’ ሚዳቆ ግን ‘ለዉድ ህይወቷ’ ስለዚህ አላማ ከጊዜያዊ ፍላጎት እንደሚበልጥ ትረዳለህ፡፡

የሚዳቆ አላማ ሕይወቷን ማትረፍና ሌላ ቀንን ማየት ሲሆን የነብር ደግሞ ‘በልቶ መዘረር’ ነዉ፡፡

ከስንት አንዴ ከበላና ከጠገባ በኋላ ሚሊየን ሚዳቆ በአፍንጫዉ ስር ቢያልፉ ምን ገዶት!

ለመኖር እልህ ሲይዝህ ለመብላት መኖር ታቆማለህ ፣ ለሻይ መጠጫ ተራራ መፈንቀል ፣ የሌለዉን እንዳለ ማስመሰል ይደክምሃል...ወደ እዉነተኛዉ መንገድ የዛኔ መመለስ ትጀምራለህ፡፡ ያም ለአላማ መኖር !

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 18:48:37 የህይወት እውነታ

ሁሉንም ሰዉ ልታስደስት አትችልም፡፡ ይህ ትልቅ እዉነታ ነዉ፡፡

የሆኑ ሰዎች ቢጠሉህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የሚወዱህ እንዳሉ ሁሉ የሚጠሉህም እንደዚያዉ፡፡ ሰዎች ስላንተ ያላቸዉ አመለካከት ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡

የመሰላቸዉን ያህል ሊገምቱ ፣ ዋጋ ሊያወጡ ሊያወርዱ ፣ ወይም ሊሰቅሉ ይችላሉ፡፡

ሰዎች አንተ ላይ ባላቸዉ አመለካከት ማንነትህን ሞቅና ቀዝቀዝ እያደረክ አትኑር...

ራስህን ሆነህ በሕይወትህ ትልቅ ዋጋ ለምትሰጣቸዉ ሰዎች ብቻ የሚጠበቅብህን መስዋእትነት ክፈል ፡፡

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 06:59:29


ኢድ ሙባረክ ! መልካም በዓል !
@Love_Therapist

1.8K views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 16:29:14 አትጨናነቅ

አእምሮአችን ከሚገባዉ በላይ የሚያስበዉ አቅጣጫ መስጠት ሲያቅተን ነዉ፡፡

ለምሳሌ ዝግጅቱ ምናለ ከነገ ወዲያ ቢሆን?...እቤት ልሂድ አልሂድ...? ሰዉየዉ እንደተባለዉ ባይሆንስ? ደሞዝ ነገ ባይወጣ ጉዴ ፈላ!' ወዘተ... አይነት ሃሳቦች እራሳችንን የበለጠ እንዲጨነቅ ያደርጋሉ

አእምሮአችንን አቅጣጫ ከሰጠነዉ በትክክል መስራት ይጀምራል፡፡ ስለዚህ በትንሽ በትልቁ ማሰባችንን እንቀንሳለን ማለት ነዉ፡፡

ምሳሌ፡ 'ነገ ቢሳካም ባይሳካም አሪፍ ይሆናል...ጠዋት እቤት እሄዳለሁ...ሰዉየዉን ምንም ይሁን ምን ነገ አየዋለሁ...ደሞዝ ነገ ካልወጣ ሌላ አማራጭ እጠቀማለሁ' ወዘተ...

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 04:02:36
..... ተነስቷል .....

እንኳን አደረሳችሁ ፣ መልካም ፋሲካ ፣ መልካም በዓል

@love_therapist @love_therapist
1.8K viewsedited  01:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 15:57:21 ምቀኛም የባሰ

በህይወት ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ሰዎች አንዳንዴ ከመሬት ተነስተዉ ይጠሉሃል! (እደግመዋለሁ) ከመሬት ተነስተዉ ይጠሉሃል፡፡

በጣም ምርጥ ፀባይ ሊኖርህ ይችላል፡፡ ለሰዎች አሳቢና ቸርም ልትሆን ትችላለህ፣ በክፉ ጊዜ እንኳን ለወዳጅ ለጠላትህም የምትደርስ አይነት ባህሪ ሊኖርህ ይችላል፡፡

ማወቅ ያለብህ ነገር የሆነ የሰዉ ሁል ጊዜ ስላንተ መልካምነት ሲወራ ያስጠላዋል፣ አይደላዉም፣ ይደብረዋል፣ ራስ ምታቱ ይነሳል፡፡

ይሔ ሰው ከምቀኞች ግሩፕ ዉስጥ እንዳትቀላቅለዉ፡፡ ምቀኛ ማለት በምትሰራዉ መልካም ነገር ቀንቶ ክፉ የሚያስብ ነዉ፡፡ ምቀኛ ለማፍራት ቢያንስ የተሻለ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል፡፡

እነዚህ ሰዎች ግን የምትሰራዉ ነገር በሙሉ አይመቻቸዉም፡፡ ብትስቅም ብታለቅስም አይደላቸዉም፡፡

ብቻ አንተነትህ ከነአካቴዉ በዚህ ምድር ላይ በመፈጠሩ ይጠሉታል፡፡ ምቀኞች ከምታደርገዉ ነገር ቅናት ሲይዛቸዉ እነዚህ ልዩ ሰዎች ግን ከማንነትህ ጋር ቅናት ይይዛቸዋል! ምናለ ባልተፈጠረ! ዉሃ ሆኖ በቀረ! ይላሉ፡፡

የእነዚህ ሰዎች መሰረታዊ ችግር አንተን ሆነዉ ባለመገኘታቸዉ ብቻ ነዉ! አንተን ቢሆኑ ደስ ባላቸዉ ግን አንተን መሆን አይችሉም! ስለዚህ እነዚህን ሰዎች ጠንቀቅ በላቸዉ፡፡

ለምሳሌ ምቀኛህ “ቪዛዉ አልተሳካለትም እሰይ! የታባቱ እዚቹ አፈር መስሎ ይኖራታል!” ሲልህ ያኛው የባሰው ሰው ግን “ምነዉ በሞተ! በጣም እኮ ነዉ የሚያስጠላኝ...እንኳን ቪዛ መኖርም ባይሳካለት የምረካም አይመስለኝ!” ይልሃል !

ከእንደዚህ አይነቱ ይሰውረን

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር
2.0K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ