Get Mystery Box with random crypto!

ነገን... የነገዉን ማሰብ በራሱ ምንም ክፋት የለዉም፡፡ ነገ መጥፎም ይሁን ደግ ነገን አልሞ መ | 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

ነገን...

የነገዉን ማሰብ በራሱ ምንም ክፋት የለዉም፡፡ ነገ መጥፎም ይሁን ደግ ነገን አልሞ መነሳቱ እንከን የማይወጣለት ነገር ነዉ፡፡ በተለይ በኛ ሀገር ባለዉ ነባራዊ የህብረተሰባችን አኗኗርና የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ነገን ማሰብ ያልተለመደ ነዉ፡፡

አሁን ባለሁበት ሁኔታ የምኖር ከሆነ ነገን እንዴት አልፋለሁ ብሎ ማሰብ እግዚአብሄርን እንደማቆስጣት እናየዋን፡፡ አዎ ነገን ሁሉን ለሚችለዉና በእጆቹ ለሰራዉ ፈጣሪ አሳልፈን መስጠት ብልህነት እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ነገን እሱ ስለሚያዉቅ ከኛ መላምት ፍፁም በማይገናኝ መልኩ የእሱ ቸርነት ያስፈልገናል፡፡ ተስፋችንም እሱ ነዉ፡፡

ግን አልመን መነሳታችንና ማቀዳችን አምላክ በሰጠን አእምሮ መጠቀማችን ጥቅሙ እንጂ ጉዳቱ አያመዝንም፡፡ ዛሬ እያየን ያለናቸዉ የራሳችን የህይወት ዉጥንቅጥ እንዳናስተዉል የሚገፋፉን ቢሆንም ወደፊት በተስፋና በሙሉ ቆራጥነት መገስጉ እጅግ ይጠቅመናል፡፡

ነገን ‘የራሱ ጉዳይ!’ ብለን ያገኘናትን የምንበትን ከሆነ፣ ‘ልሙት ልኑር የት አዉቃለዉ?’ ብለን 'ዛሬን ቸባ!' እያልን የምንደልቅና የምናስደልቅ፣ ዛሬን በቀልድና በዝባዝንኬ አሳልፈን ነገን በቁጭት ከመኖር እስኪ ቆፍጠን ብለን ህልማችንን፣ ሃሳባችንን ስጋ አልብሰን ለማየት እንነሳ!

ወሬዉ፣ ቀልዱ፣ ጭፈራዉ ሁሉ ከስራ ሲቀድሙ ይዘዉን ገደል ይከቱናል...አሁንም እየከተቱን እያየን ነዉ፡፡ ምክንያት ለመፍጠር ቅንጣት ያህል ሰበብ ብቻ በሚኖርበት በዚህ ሀገር፣ የግል ህልማችንን ለማነፅ መሄድ እንደቀረ ፋሽን ሊያስመስለን ቢሞክርም በቃ እንነሳ... የሌላዉ አጨብጫቢ ሆኖ መኖር ይበቃናል!

“ፓ እንትናን አየሃት!” እያልን የጎረቤት የሃብት ምጥቀትን እንደቃና ቲቪ ፊልም አሳምረን ከምንተርክ እንኑረዉ...ተራኪ መሆን ያማል፣ መጨረሻዉ አምስት ሳንቲም የሌለዉ ማንነት ይዞ መቅረት ነዉና ዳይ ወደስራ!!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር